መዝገብ

Day: June 10, 2019

ምርጫ ቦርድ ከጠየቀው በጀት አንድ ቢሊዮን ብር ተቀነሰበት

ቦርዱ እቅዱን ዳግመኛ ሊፈትሽ እንደሚችል አስታውቋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ካቀረበው 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ ውስጥ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮኑ ብቻ ይሁንታ ማግኘቱ ተገለፀ። ቦርዱ በውጪ አገር አጥኚዎች…

10ኛው ክልል ሐምሌ 11 ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል

ራሱን የሲዳማ የለውጥ አራማጆች ብሎ የሚጠራው የሲዳማ ተወላጅ ምሁራንን ያቀፈው ቡድን በመጪው ሐምሌ 11/ 2011 የሲዳማ ክልልን በይፋ እንዲመሰረት ቀን እንደቆረጠ እና በዚህ ላይም ከደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሚሊዮን ማቲዮስ ጋር ውይይት ማድረጉን አዲስ ለማለዳ አስታወቀ። አራማጆቹ አዲሱ ክልል ሲቋቋም…

የዛሚ ሬዲዮ ንብረት በፍርድ ቤት ታገደ

ባለፈው ሰኞ፣ ግንቦት 26/2010 በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ የንግድ ችሎት የናሁ ቴሌቪዥን እናት ድርጅት በሆነው ጎልደን ኮፊ ሮስተሪ አመልካችነት በዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ ላይ በቀረበው አቤቱታ መሰረት የሬዲዮ ጣቢው እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ እግድ ማውጣቱ ታወቀ። በተጨማሪም በድርጅቱ ተመዝግበው…

መሪዎች አርዓያነታቸውን ያሳዩ!

በቅርቡ በመላው የሙስሊም ማኅበረሰብ የተከበረውን ኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀደም ብለው ባቀረቡት ጥሪ መነሻነት ከክርስቲያኖች ጋር በመሆን ሕዝብ ሙስሊሙ በዐሉን በሚያከብርበትና በሚሰግድበትን አዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥና ዙሪያውን በኅብረት ጽዳት አካሒደዋል። ይሔ የጽዳት ክንውን ወትሮ…

ዐቃቢ ሕግ በሐሰት ለሜቴክ መስክረዋል ያላቸው ግለሰቦች ላይ የመሠረተውን ክስ አቋረጠ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውሃ የሚያርፍበትን ቦታ የደን ምንጣሮ ሥራ ለመሥራት ከኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር በ2006 ውል ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ማኅበራት የሥራ ክፍያ እንዳይከፈል የሐሰት ምስክርነት ሰጥተዋል በተባሉ ባለሞያዎች ላይ ተመስርቶ ነበረው ክስ እንዲቋረጥ ተወሰነ። የወንጀል ክሱ…

ለልማት ተነሺዎች የማኅበራዊ ትስስርና ሥነ ልቦና ካሳ ሊከፈል ነው

ለገጠር መሬት አማካኝ ገቢ 10 ዓመት ተባዝቶ የሚሰጠው ካሳ ከፍተኛ ገቢ በ15 ተባዝቶ እንዲሰጥ በረቂቁ ላይ ቀርቧል በከተሞችና በገጠር ኢትዮጵያ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚፈናቀሉ ዜጎች ከመኖሪያ ይዞታቸው በሚፈናቀሉበት ወቅት ከነበሩበት አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ ሲዛወሩ ለሚደርስባቸው ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ካሳ…

የንግድ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተጠየቀ

መንግሥት ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በዘረጋው የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ላይ በ2009 እና በ2010 በጀት ዓመት ተግባሩን በሚገባ ባልተወጡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ። ባንኩ በአዋጅ በተሰጠው ኀላፊነት መሰረት ፈንዱ በሕጋዊ መንገድ ለተጠቃሚዎች መተላለፉን መቆጣጠር እና…

ኢሚግሬሽን ሕገወጥ የፓስፖርት ተግባር ላይ የተገኙ ሠራተኞቹን ለሕግ አሳልፎ ሰጠ

ግማሽ ሚሊዮን ፓስፖርት ወደ አገር ውስጥ መግባት ጀምሯል በቅርቡ እንደ አዲስ የተዋቀረው የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ በመሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሕገወጥ በሆነ መልኩ የፓስፖርት እደላ ሥራ ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ሰዎች ለሕግ አሳልፎ መስጠቱ ታወቀ። ላለፉት 9 ወራት…

በአዲስ አበባ 5ሺሕ ሕገወጥ ቤቶች እንደሚፈርሱ ተረጋገጠ

በአዲስ አበባ ከተማ በዐሥሩም ክፍለ ከተሞች በጠቅላላው 5 ሺሕ የሚደርሱ ሕገ ወጥ መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ የማጣራት ሥራዎችን ጨርሶ በመጪዎቹ ሳምንታት ወደ ተግባር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት አስታወቀ። ከሕገ ወጥ ግንባታው በስተጀርባ በስውር ተሳትፈዋል የተባሉ ባለሀብቶች፣ የፖለቲካ ሹመኞች፣ እንዲሁም በክፍለ…

ባልተገኘንበት ሜዳ

“ሲቄ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል ‹አለንጋ› የሚል ትርጉም አለው። በገዳ ትውፊታዊ አስተዳደር ውስጥ በባሏ ጥቃት የደረሰባት ሚስት፣ ከሌሎች ሴቶች ጋር በመሆን ባሏ ላይ የካሣ ውሳኔ የምታሳልፍበት ስርዓት ሲቄ ይባላል። የአንድነት፣ የሰላምና የፍቅር የምትባል አገራችን፤ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰው አክባሪና ትኹት የምንባል እኛ…

የሕፃናት ማቆያ ጉዳይ

የሕፃናት ማቆያ ለሴት ሠራተኞች የሥራ ላይ ውጤታማነት የሚጫወተውን ሚና ከፍተኛነት የጠቀሱት ቤተልሔም ነጋሽ, በአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተጀመረው የሕፃናት ማቆያ ስፍራዎች ማዘጋጀት የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባ መሆኑን ገልጸው ብዙ ርቀት መጓዝ እንደሚቀር ግን የአገራት ልምዶችን በማጣቀሻነት አቅርበዋል።   አዲስ ዓመት…

በመተከል ዞን አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት ስድስት ሰዎች ተገደሉ

በጃዊ ታስረው የነበሩ አመራሮች ተለቀዋል ተባለ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ቆታ ቀበሌ አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች መቁሰላቸው ታወቀ። በፀጥታ ስጋት ምክንያት ባለፈው እሁድ፣ ግንቦት 25/2011 ምሽት 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ ንብረታቸውን ይዘው…

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃን ሳያክሙ እንዳይጠጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የዝናብ ወቅት መምጣቱን ተከትሎ በተለይም በጎርፍ ምክንያት የመጠጥ ውሃ መስመሮች መበከል ሊያጋጥማቸው ስለሚችል ኅብረተሰቡ ለመጠጥ የሚጠቀመውን ውሃ ማከሚያ በኬሚካሎች በማከም ወይም አፍልቶ እንዲጠቀም የኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አሳሰበ። ከውሃ መበከልና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ እና አዲስ…

ንግድ ባንክ በ28 ሺሕ ሠራተኞቹ ክስ ሊመሰረትበት ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ከድርጅቱ ጋር ባላቸው የኅብረት ስምምነት መሰረት የሥራ ሰዓት እየተከበረ አይደለም እና የድርጅቱ የሥራ እርከን ደረጃዎች እየተጣሱ ነው በሚል ክስ ለመመስረት ዝግጅት መጠናቀቁ ታወቀ። የሠራተኞች ማኅበሩ ባሳለፍነው ሳምንት ጠበቃ የቀጠረ ሲሆን በቅርቡም በባንኩ ላይ ክስ ይመሰረታል ተብሎ…

የሲዳማ ክልል መሆን እና ይዞ የሚመጣው መዘዝ

የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ለመግባት ግፊቶች በበረቱበት በዚህ ወቅት፣ የሲዳማ ክልል መሆን በሐዋሳ ዕጣ ፈንታ ምን አንድምታ ያመጣል? ጌዲኦ ከደቡብ ክልል ጋር የሚኖራት የወሰን ግንኙነት ስለሚቋረጥ የጌዲኦስ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ከሀብት ክፍፍል ጋር በተያያዘ…

የሲዳማ ሕዝብ ጩኸት ‘ሞግዚት’ ፍለጋ አይደለም!!

የሲዳማ በክልል ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን ጠልፎ የራስ ፍላጎትን ለማስፈጸም የኦሮሞ ልኂቃን በኦነግና በኦዲፒ በኩል እንዲሁም የትግራይ ልኂቃን በሕወሓት በኩል እያሴሩ ነው ሲሉ ግዛቸው አበበ ይከሳሉ፤ እንደማሳያ የሚያነሷቸውን ነጥቦችም አካተዋል።   2011 አዲስ ዓመት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በሲዳማ ውስጥ…

የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል የ50 ዓመት ጉዞ

ከማለዳ እስከ ረፋድ የማለዳዋ ፀሐይ ምድርን ልታሞቅ በምሥራቅ ስታጮልቅ ከወፎች ጋር አብረው እየዘመሩ ወደ ሥራቸው የሚያቀኑ የአትክልት ተራ ነጋዴዎችን፣ እቃ ጫኝና አውራጆችን እንዲሁም የአይሱዙ ሹፌሮችን በማለዳ በሯን ከፍታ የምትቀበለው, ለጎዳና ተዳዳሪዎች ቤት የሆነችው፣ መዝናናት ላማረው አገርኛ ፊልሞችን የሚያሳዩትን ሲኒማ አምፔር፣…

አዲስ – አዳማ የፍጥነት መንገድ በእንስሳት ምክንያት የሚደርሰው አደጋ አሳሳቢ ሆኗል

ከአዲስ አበባ አዳማ ድረስ የተዘረጋው የፍጥነት መንገድ በሚያቋርጣቸው አካባቢዎች እንስሳት ወደ ዋና መንገድ በመግባት አደጋ እንዲደርስ ምክንያት መሆናቸውን የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። አሽከርካሪዎች ጨምረው እንደገለፁትም፤ መንገዱ በፍጥነት የሚነዳበት በመሆኑ እና እንስሳት መንገድ ላይ በሚያቋርጡበት ጊዜ ላለመግጨት በሚደረገው ጥረት…

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለመግባባት ተፈጠረ

መደበኛ የቀጠና ኹለት ሙሉ በፖሊስ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገላቸው በኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ነባር አማኞች እና ከአዲሱ አመራር የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር አለመግባባት ውስጥ እንደገቡ ታወቀ። ምንጮች ለአዲስ ማለዳ እንደገለፁት በቤተ ክርስቲያኗ የተፈጠረው አለመግባባት በ2006…

ለውጥንቅጡ ፖለቲካችን መፍትሔ

የኢትዮጵያ የኅልውና ሥጋትና የሕዝብ ሰላም ማጣት ችግር ዋና መንስኤ ዘርና ፖለቲካ መቀላቀላቸው ነው የሚሉት መላኩ አዳል, ከዚህ ችግር መውጫ መንገዱ ሕገ መንግሥትን በማሻሻል ርዕዮትን መሰረት ያደረገ ፖለቲካን ማካሔድና ፌደራላዊውን አወቃቀር ማስተካከል ነው ሲሉ ምክረ ሐሳባቸውን አቅርበዋል።   ዘርና ፖለቲካ ወይም…

‘አባታዊ ስርዓት’ የሴቶችና ወንዶች አፍ መፍቻ ቋንቋ

የስርዓተ ፆታ እኩልነት እንዲሰፍን የሚሠሩ ሰዎች የሚገጥማቸው አንዱ ፈተና በፆታዊ መድልዖው ውስጥ ተጠቂ የሆኑት ሴቶች ሳይቀሩ አድሏዊውን ስርዓት ጥብቅና የሚቆሙለት መሆኑ ነው። ሕሊና ብርሃኑ በነባራዊው ዓለም ውስጥ ገዢ የሆነው ‘አባታዊ ስርዓት’ ወንዶቹን ብቻ ሳይሆን ሴቶችንም ተገዢ እንዲሆኑለት አድርጎ ነው የሚቀርጻቸው…

“አውታር” ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ትንሣኤ!?

በኢትዮጵያ በርካታ የሥነ ጥበብ በተለይም ደግሞ በሙዚቃው ዘርፍ የተሰለፉ ግለሰቦች እንቅልፋቸውን ሰውተው ለሕዝብ የሚያቀርቧቸው የሙዚቃ ሥራዎች በተለያዩ ምክንያቶች መና ቀርቶባቸው አንገታቸውን የደፉበት ያለፉትን ዓመታት አሁን ተረት ለማድረግ እየተሠራ ይመስላል። በተደጋጋሚ ለቁጥር የሚያዳግቱ ኢትዮጵያዊያን የሙዚቃ ሰዎች አደባባይ በመውጣት ስለቅጂ እና ተዛማጅ…

10ቱ ብዙ ሕዝብ የከፋ ድኅነት ውስጥ ያለባቸው የአፍሪካ አገራት

ምንጭ፡-አይ ኤም ኤፍ 2019 (እ.ኤ.አ.) ያለፈው ዓመት ዓለም በታሪኳ ዝቅተኛ የሚበል የከፋ ድኅነት ውስጥ ያሉ ሰዎች ቁጥር ያሰመዘገበችበት እንደነበር የወርልድ ባንክ ሪፖርት ያሳያል። ነገር ግን 68.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉብት ዓመት በመሆኑ ይህ ስኬት ላይ የራሱን ጥላ ማጥለቱንም…

ኢሳት እና ኢትዮ 360°

ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ያዝ ለቀቅ እያለ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች መከራከሪያ ሆኖ የሰነበተው በኢሳት ጋዜጠኞች መካከል እንዲሁም በጋዜጠኞቹና በቦርዱ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ሲሆን በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል። የተባረሩትና ራሳቸውን ያገለሉ ጋዜጠኞች በኅብረት ኢትዮ 3600 የሚባል የፌስቡክና የዩቲዩብ ሚዲያ መጀመራቸውን በዘመቻ…

ዐሥሩ የተሳሳቱ ጤና ነክ መረጃዎች

በዘመናችን የመረጃ እጥረት አለመኖሩ እርግጥ ቢሆንም, የሚሠራጭ መረጃ ሁሉ ግን ትክክል አለመሆኑን ለማሳየት ዶክተር ሰላም ታደሰ በተለይ ከጤና ጋር በተያያዘ የሚሰራጩትን መረጃዎች ሳያጣሩ ከመጠቀም በፊት ትክክለኝነታቸው መታወቅ አለባቸው ሲሉ መታረም ያለባቸውን ልምዶች ጠቁመዋል።   መረጃን ማግኘት ከማንኛውን ጊዜ አሁን ቀላል…

በኢትዮጵያ አዲስ የኮሚኒኬሽንና የብሮድካስት ሳተላይት ሊገነባ ነው

በኢትዮጵያ አዲስ የኮሚውኒኬሽንና ብሮድካስት ሳተላይት ለመገንባት ከቻይና መንግሥት ጋር ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱ በተለይም የብሮድካስት ዘርፉን ለማዘመን ያገለግላል ሲል የኢኖቬሽን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ ገልጿል። ሚኒስቴሩ አያይዞ እንደገለፀውም ተጨማሪ የሥራ ዕድል መፍጠርና ለተጨማሪ ገቢ ማስገኛ እንዲውልም ሌላው የግንባታው ዓላማ መሆኑን…

በጅጅጋ ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ “ኢ-ፍትሓዊነት” ተቃውሞ አስነሳ

በሐምሌ 2010 በሶማሌ ክልል በጅጅጋ ከተማ በተነሳው ኹከትና ብጥብጥ ምክንያት ቤት ንብረታቸውን እንዲሁም የተለያዩ የንግድ ሥራዎቻቸውን ላጡ ሰዎች በክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በኩል የሚሰጠው ድጋፍ በትውውቅ እየታደለ ነው ሲሉ 400 የሚጠጉ ነዋሪዎች ቅሬታ ማቅረባቸው ተሰማ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የአደጋ…

ኤጀንሲው ለማረሚያ ቤቶች በ5 ሚልዮን ብር መጻሕፍት ሊገዛ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ በክረምት የንባብ ባሕልን ለማዳበር በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት “በመጽሐፍ እንታረም” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ፣ ሸዋሮቢት፣ ድሬ ዳዋ፣ ባሌ ሮቤና ወላይታ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ታራሚዎች ልገሳ ለማድረግ ግዢ ሊፈፅም ነው። በማረሚያ ቤቶች…

ሱዳን ከአፍሪካ ኅብረት ታገደች

የአፍሪካ ኅብረት ሱዳንን ከአባልነት ከሐሙስ፣ ግንቦት 29 ጀምሮ አገደ። በዋና ከተማዋ ካርቱም ወታደራዊው መንግሥት በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃ የብዙ ሰዎችን መገደል ተከትሎ ነው ኅበረቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው። ተቃውሞውን የሚያስተባብሩት የተቃዋሚ የመብት ተሟጋቾች እንደሚገልፁት በሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ በተወሰደ እርምጃ 108 መገደላቸውን…

ንግድ ባንክ የትራፊክ ቅጣት መሰብሰብ ሊጀመር ነው

የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ከሰኔ 5/2011 ጀምሮ የትራፊክ ቅጣት ክፍያ ስርዓትን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ተፈጻሚ ለማድረግ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ። ከዚህ ቀደም በዘጠኙ የኤጀንሲው የክፍያ ማዕከላት በተጨማሪ በ ‹ለሁሉ› የቅጣት መሰብሰቢያ ማዕከላት ሲሰበሰብ የነበረው የቅጣት ገንዘብ በድንገት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com