መዝገብ

Category: የእለት ዜና

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ህዳር 3/2012

1 በኢትዮጵያ ከ 1900 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የቴክኖ ሞባይል አምራች ድርጅት አስታወቀ።ድርጅቱ በትኩረት ከሚሠራባቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት ባሻገር በአገሪቱ ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን በኢትዮጵያ የቴክኖ ሞባይል ድርጅት የገበያ ልማት ሥራ አስኪያጅ ሐሳኒ ሞሀመድ ገልጸዋል።በአሁኑ ወቅት በጎሮ አይሲቲ…

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር በተያዘዉ በጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡን አሰታወቀ። ‹‹ግዴታዬ እወጣለሁ፤ መብቴን እጠይቃለሁ›› በሚለው የታክስ ንቅናቄ መርህ እና ‹‹አገሬን እወዳለሁ፤ ግዴታዬን እወጣለሁ!›› እያሉ የአገራችን ታዋቂ ድምጻውያን ባዜሙት ቀስቃሽ መልዕክት ግብር ከፋዮች ብቻ ሳይሆኑ መላው…

በድሬደዋ ከተማ በድጋሚ ግጭት ተቀሰቀሰ

በድሬደዋ ከተማ እንደገና ግጭት በመቀስቀሱ ምክንያት ህዳር 2/2012 ለሊት ተኩስ እንደነበር የአዲስ ማለዳ ምንጮች ገልጸዋል።በተለይም በቀፊራ እና ገንደሐራ አከባቢዎች ላይ ከፍተኛ ተኩስ መሰማቱንም ተናግረዋል። በዩንቨርሲቲዉ ዉስጥ ከትላንት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት ከግቢው መውጣት እንዳልቻሉ ተማሪዎች የገለጹ ሲሆን የግጭቱ መነሻ ጥቅምት 29/2012…

የወረታ ወደብና ተርሚናል የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቀቀ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጎንደር በወረታ ከተማ በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት እየተገነባ  የሚገኘው የወረታ ወደብና ተርሚናል የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቀቀ ። በኹለት ምዕራፍ ግንባታው የሚካሄደው ይህ ወደብና ተርሚናል በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ 3 ሔክታር የለማ ሲሆን የመጋዘን፣ የቢሮዎች፣የጉምሩክ…

ሜቴክ 41 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በማትረፍ ከልማት ድርጅቶች ቀዳሚ ተርታ ላይ ተቀመጠ

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የመንግሥት የልማት ድርጀት ሆነው በአምራች ዘርፍ ከተሰማሩት አምስት ድርጅቶች ውስጥ ኢንጅነሪንግ እና ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) 41 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በማትረፍ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ። ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር…

የኅዳሴው ግድብ የኮርቻ ግድቡ የአርማታ ሙሊት ስራ ተጠናቀቀ

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ታወቀ። ቀደም ሲል ከ14 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የድንጋይ ጥቅጥቅ ሙሊት ስራ መከናወኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክትል ስራ አስኪያጅ በላቸው ካሳ ገልጸዋል። ከኮርቻ ግድቡ…

አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አማኑኤል ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት። ጌትነት ተስፋየ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይን ተቀጥራ በምትሰራበት ቤት ውስጥ በመግባት አፏን በማፈን እና በቢላ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 2/2012

1- አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በአዲሱ ሕብረ-ብሔራዊ ፓርቲ ተዋህዶ ለመሥራት የወሰነ ሲሆን “ኢትዮጵያዊነትን ከማንነት ጋር አስተሳስሮ የሚያስኬድና የእውነተኛ ፌዴራሊዝም መተግበሪያ መሆኑን በመገንዘብ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአዲሱ አገራዊ ሕብረ ብሔራዊ ፓርቲ ተዋህዶ ለመታገል ወስኗል” ሲሉ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የአማራ ክልል ኢንደስትሪ…

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በወልዲያ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጥቅምት 29/2012 በወልዲያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመዉን የግድያ ወንጀል እና ድብደባ አወገዘ። ኦፌኮ ‹‹የነገን ወጣት ትውልድ በመግደል ደም በማፍሰስ እና ሕዝብን አጋጭቶ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረገው ሩጫ ይቁም!›› ሲል ባወጣው መግለጫ፤ ‹‹በሕገ ወጦች የተፈጸመውን የተማሪዎች ድብደባ እና…

የገቢዎች ሚኒስቴር በጥቅምት ወር ብቻ 32 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግብር መሰብሰቡን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር በጥቅምት ወር ብቻ 32 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግብር በመሰብሰብ የእቅዱን 97 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካቱን አስታወቀ። ይህ አፈፃፀም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። የገቢዎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በቅንነት፤…

“የመንግሥት አካላት ዓለማቀፋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ እጠይቃለሁኝ” የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት የዓለም ማህበረሰብ ትኩረት በመሆኑ አገራዊና ዓለማቀፋዊ እርምጃ እንዲወሰዱ ጥሪ አደርጋለሁኝ ብሏል የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ  ዛሬ ባወጣው መግለጫ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች አንዱ የሌላዉ ጠላት አንደሆነ በማስመሰል ላለፋት 28 ዓመታት በህዝብ ላይ የተጫነዉ የዘር ፖለቲካ ዉጤት የሆነዉ ጽንፈኝነት…

ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የኮሪያ ዘማቾች መርጃ ማዕከል ገነባች

በ1940ዎቹ በኮሪያ ልሳነ ምድር ይተካሄደውን ጦርነት ተከትሎወደ ስፍራው በማቅናት ከደቡብ ኮሪያ ጦር ጎን ለተዋደቁት የኢትዮጵያ የእግረኛ ጦር መርጃ የሚውል የዕርዳታ ማዕከል በደቡብ ኮሪያ መንግስት ድጋፍ ተገንብቶ ተመረቀ። መርጃ ማዕከሉ በ700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ እና ባለኹለት ፎቅ እንደሆነም ታውቋል። በደቡብ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ሕዳር 1/2012

1-ከሰባት ወር በፊት በጊቤ ሸለቆ የሞቱት ከ30 በላይ ጉማሬዎች በአካባቢዉ ነዋሪዎች ተመርዘው መገደላቸው በጥናት ተረጋገጠ። ሚያዝያ ወር 2011 ዓ.ም በጊቤ ሸለቆ ከ30 በላይ የሚሆኑ ጉማሬዎች መሞታቸዉን ያስታወሰው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢዉ ነዋሪዎች ተመርዘዉ እንደተገደሉ በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል። በተጨማሪም በካፍታ ሽራሮ ብሔራዊ…

“መዉሊድም ቢሆን እናገለግላችኋለን” ብሎ ያወጣዉ ማስታወቂያ የአገላለጽ ስህተት ነው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ

በገቢዎች ሚኒስቴር ድረ ገጽ ላይ ጥቅምት 29/2012 ግብር ከፋዮችን ከቅጣት ለማዳን “መዉሊድም ቢሆን እናገለግላችኋለን” ብሎ የወጣዉ ማስታወቂያ የአገላለጽ ስህተት ነው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ ። የበዓሉ ቀን መሥሪያ ቤቱ ዝግ እንደነበር በድረ ገጹ ያስታወቀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፤ ነገር ግን…

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኹለት ተማሪዎችን ሕይወት በቀጠፈው በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ። በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር መግለጫ መሰረት፣ በግጭቱ ላይ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሔደባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በተረጋጋ ሁኔታ ላይ…

የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ምርመራ መጠናቀቁ የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ አስታወቀ

የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ‹‹ታስቦበት፣ ክህደት የተፈጸመበትና ለስልጣን ጥም የታሰበ ነው›› ሲሉ የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር የወንጀል ምርመራ መጠናቀቁን ባሳወቁበት ወቅት ተናገሩ። በተፈፀመው ጥቃት  ሰለባ የሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች መካከል የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት አምባቸው መኮንን(…

ኢትዮጵያዊው በአሜሪካ የሚስቱን እና የልጁን ህይወት ቀጠፎ ራሱን አጠፋ

ዮናታን ተድላ የተባለ እና በአሜሪካ ኒውዮርክ ግዛት የሚኖር የ46 ዓመት ጎልማሳ ከትዳር አጋሩ ጋር በነበረው አለመግባባት የተነሳ ባለቤቱን እና ልጁን ገድሎ ራሱን አጠፋ። ጄኒፈር ሼቸልቲን ከተባለች ባለቤቱ ጋር ለዓመታት አብረው እንደኖሩ እና አባይነሽ የተባለች የዓመስት ዓመት ልጅ ማፍራታቸውንም ለማወቅ ተችሏል።…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 28/2012

1-የትዊተር መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃክ ዶርሴይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የአፍሪካ አገራትን በዚህ የህዳር ወር እንደሚጎበኙ ተናግረዋል።ጉብኝታቸውንም በናይጄሪያ የጀመሩ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ በማምራት ከሥራ ፈጣሪዎች ጋር እንደሚወያዩም በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።ከኢትዮጵያውያኑ የቴክኖሎጂ የሥራ ፈጣሪ…

ቻይና ከፍተኛውን አምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን አስተዋወቀች

ቻይና ውስን ከሆኑ አገራት ውጪ እምብዛም ያልተለመደውን  እና ቀሪዎቹ ዓለማት ያልደረሱበትን የአምስተኛ ትውልድ የኔትወርክ ቴክኖሎጂን በዓይነቱ ከፍተኛ ተባለውን ይፋ አድርጋለች። በቻይና የሚገኙ ሦስት የኔትወርክ አገልገሎት ሰጪ ድርጅቶች በጋራ ገመድ አልባውን እና ቀጣዩን ትውልድ ቴክኖሎጂ የሆነውን 5ጂ ወይም አምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን…

በድሬዳዋ ለደረሰው ግጭት የተሳሳቱ መረጃዎች ዋነኛ ምክንያት ናቸው

በቅርቡ በድሬዳዋ ተከስቶ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ላደረሰው ግጭት መነሻ በዋነኛነት ተሳሳቱ ምረጃዎች ወደ ግለሰቦች መድረሳቸው መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ። ምክር ቤቱ 43ኛ መደበኛ ጉባዔውን ያካሔደ ሲሆን በጉባዔውም ላይ ከተማዋን ሰላም በሚመለከት ሰፊ ውይይት ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።…

አዲስ አበባ እና ዋሽንግተን የእህትማማች ከተሞች ፊርማ ይፈራረማሉ

አዲስ አበባ እና የአሜሪካዋ ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ግንኙኑታቸውን ለማጠንከር የእህትማማች ከተሞች ስምምነት እንደሚፈራረሙ ታወቀ። ጥቅምት 29/2012 ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገቡት የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር በቆይታቸው የኹለቱን ከተሞች ወዳጅነት ላቅ ወዳለ ደረጃ የሚያደርሰውን የእህትማማች ከተሞችን ስምምነት እንደሚፈራረሙ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 27/2012

1-የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት ባለፉት አስር ወራት 67ሽሕ 400 ትኬቶችን መሸጡን አስታውቆ፤ ሽያጩም በብር ሲሰላ 200 ሚሊዮን ብር እንደሚሆን አስታውቋል። (ኢትዮ ኤፍ ኤም) …………………………………………………………….. 2-የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከሕዳር 12-15/2012 ለሚካሄደው የፖሊዮ ቅድመ መከላከል ዘመቻ የክትባት መድኃኒቶችን እያሠራጨ…

በዘመቻ ሙሴ ተሳታፊ የነበሩት ጆርጅ ገትልማን በ80 ዓመታቸው አረፉ

በፈረንጆች 1980ዎቹ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ቤተ እስራኤላዊያንን ለመውሰድ በተደረገው እና ‹‹ዘመቻ ሙሴ›› የሚል ስያሜ በተሰጠው እንቅስቃሴ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው እና በጀግንነታቸው በእስራኤላዊያን ዘንድ የሚዘከሩት ጆርጅ ገትልማን በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ጠንካራ የንግድ ሰው እየተባሉ የሚሞካሹት ጆርጅ በዘመቻ ሙሴ ወቅት…

የገናሌ ዳዋ ሶስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በኹለት ወር ውስጥ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተገለጸ

የገናሌ ዳዋ ቁጥር ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በኹለት ወራት ውስጥ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገልጸዋል። 451 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የኃይል ማመንጫው ግድብ ውሃ ሙሊት ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ዋና ዋና የሙከራ ስራው…

መንግስት በቅርቡ 900ሽሕ ፓስፖርት ይረከባል

በአገር ውስጥ የሚታየውን ፓስፖርት እና የጉዞ ሰነድ እጥረት ተከትሎ መንግስት ለፈረንሳዩ ኩባንያ እንዲያትም የሰጠውን ፓስፖርት በቅርቡ እንደሚረከብ አስታወቀ። ከፈረንሳዩ ኦቨር ቱር ከተባለ ኩባንያ ጋር 1 ሚሊዮን ፓስፖርቶችን እንዲያትም ውል በተገባው መሰረት እስካሁን 100 ሽሕ የሚሆኑትን ብቻ መንግሥት መረከቡን የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 26/2012

1- የጸረ ተባይ መርጫ አውሮፕላን ተደጋጋሚ ብልሽት እያጋጠመው መሆኑ አንበጣን ለመከላከል እንቅፋት እንደሆነበት የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የእድገት ደረጃውን ጨርሶ እንቁላል ለመጣል በሚያስችለው ደረጃ የደረሰውን አንበጣ ለመከላከል የሚከናወነውን ሥራ ፈታኝ ካደረጉት መካከል አንበጣው ያረፈባቸው አካባቢዎች በአውሮፕላን ርጭት ለማድረግ አመቺ አለመሆናቸውም ጭምር…

በደቡብ አፍሪካ ሕክምና ለተከለከለችው ኢትዮጵያዊቷ የኩላሊት ታማሚ የገቢ ማሰባሰቢያ ሊደረግ ነዉ

በደቡብ አፍሪካ የኩላሊት ሕክምና እንዳታደርግ ለተከለከለችው ኢትዮጵያዊቷ ዓለም ኤርሴሎ፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሦስት ቀን ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ጀምረዋል። ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላት ኢትዮጵያዊቷ ዓለም በደረሰባት የኩላሊት ሕመም በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበረግ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ስታገኝ የነበረ ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ዜግነትም…

የሚዲያ ተቋማት በፖሊሲ ደረጃ ጠንካራ የይለፍ ቃል ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቆመ

የጋዜጠኝነት ምሕዳር ወደ ሳይበር እየተቀየረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የመገናኛ ብዙኃን በፖሊሲ ደረጃ ጠንካራ ይለፍ ቃል ፣ ጠንካራ ባለሙያ እና መመስጠሪያ እንዲኖራቸው እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተካሔደ በሚገኘው የሳይበር ደኅንነት ማስጨበጫ ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን የግንዛቤ…

የኢትዮጵያን የጦር ኃይል በማጠናከር ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ውይይት ተካሔደ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ዕዝ አዣዥ ከሆኑት ከጀነራል ስቴፈን ታውንሴንድ ጋር ዛሬ በቢሯቸው ውይይት ያደረጉ ሲሆን በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ወታደራዊ ኃይልን ከማጠናከር አንጻር የነበረውን የረዥም ጊዜ የትብብር ግንኙነት በማስታወስ፣ የአገሪቱን ጦር ሠራዊት አቅም ለመገንባት የአጭር…

የሶማሌ ክልል ፓርቲዎች አብሮ ለመሥራት ውይይት አደረጉ

በሶማሌ ክልል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት ጥቅምት 25/2012 ውይይት ማድረጋቸው ታወቀ። ድርጅቶቹ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ውይይት በቀጣይ በጋራ የሚሠሩባቸውን ጉዳዮች በጹሑፍ የሚያዘጋጁ አምስት አባላት መሰየማቸውን የሶማሌ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ አስታውቋል።…

This site is protected by wp-copyrightpro.com