መዝገብ

Category: ወፍ በረር ዜና

የካፒታል መሣሪያዎችን በኪራይ የሚያቀርብ ድርጅት ወደ ሥራ ገባ

ኢትዮ ሊዝ የተሰኘ ግዙፍ የገንዘብ አቅም የሚጠይቁ ማሽነሪዎችን በራሱ ገንዘብ እየገዛ ለተቋማት በኪራይ ውል የሚያቅረብ በግል ባለሀብቶች የሚመራ ድርጅት ተቋቁሞ ወደ ሥራ ሊገባ ነው። ኤ ኤ ኤፍ ሲ ከተሰኘ የአሜሪካን የገንዘብ ድርጅት በተገኘ 14 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ወደ ሥራ የገባ…

ኢትዮ አሜሪካን ዶክተርስ ግሩፕ የ4.6 ሚሊየን ብር ሕክምና በነፃ እየሰጠ ነው

ኢትዮ አሚሪካን ዶክተርስ ግሩፕ የተሰኘ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ የሐኪሞች ቡድን የመገጣጠሚያ እና ተያያዥ የጡንቻ ችግሮች ላሉባቸው 23 ታካሚዎች ነፃ የሕክምና ዕርዳታ ከአቤት ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከሐምሌ 30/2011 ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል። በዶክትር ክብረት ከበደ የሚመራ የሐኪሞች ቡድን ላለፉት ኹለት ሳምንታት ችግሩ…

የሥራ ፈጠራን የሚያስተባብር ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋመ

ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒንስትሩ የሚመራ እና የሥራ ፈጠራን የሚያስተባብር ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቋመች። ብሔራዊ ኮሚቴው ዘላቂ የሥራ ዕድሎች የመፍጠር ጥረትን የማረጋገጥ ኀላፊነት እንደተጣለበት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የዘጠኙ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ…

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የኀይል አቅርቦት ከግማሽ በታች ነው ተባለ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንነሐሴ 2/2011 ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት የኀይል አቅርቦት ችግር እንዳለበት የኀይል አቅርቦት ችግሩ ፓርኮቹ በሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዳይሠሩ እክል እንደፈጠረ ገልጿል። በሥራ ላይ ለሚገኙ ፓርኮች ከተጠየቅው 306 ሜጋ ዋት ኀይል ውስጥ እየቀረበ ያለው 145 ሜጋ ዋት…

በኹለት ወር ውስጥ የ5 ሺሕ መኪኖች ፍጥነት ይገደባል

የፌደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገውን የፍጥነት መገደቢያ ማሽን እስከ መስከረም መጨረሻ ለ5 ሺሕ የንግድ መኪኖች እንደሚገጥም አስታወቀ። ባለሥልጣኑ ባሳለፍነው ሳምንት የመጀመሪያ ዙር የፍጥነት መገደቢያ ለናሙና በ10 መኪኞች ላይ የገጠመ ሲሆን ፍቃድ በተሰጣቸው 4 ኩባንያዎች አማካኝነት በአገሪቱ ለሚገኙ መኪኖች እንደሚገቡ…

አዲስ አበባ ከአፍሪካ ከተሞች የውድ ሆቴሎች ባለቤት ሆናለች

መዲናችን አዲስ አበባ በአፍሪካ ካሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ለአንድ አዳር ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፈልባቸው ሆቴሎች ያሉባት ከተማ በመሆን ቀዳሚ ሆናለች። የአፍሪካ የንግድ ማኅበረሰብ በድረ ገፁ እንዳስነበበው፤ ከሐምሌ 2010 እስከ ሰኔ 2011 ባለው የጊዜ ገደብ 163 ነጥብ 7 ዶላር (4 ሺሕ 759…

አዲስ አበባ ከአፍሪካ ከተሞች የውድ ሆቴሎች ባለቤት ሆናለች

መዲናችን አዲስ አበባ በአፍሪካ ካሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ለአንድ አዳር ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፈልባቸው ሆቴሎች ያሉባት ከተማ በመሆን ቀዳሚ ሆናለች። የአፍሪካ የንግድ ማኅበረሰብ በድረ ገፁ እንዳስነበበው፤ ከሐምሌ 2010 እስከ ሰኔ 2011 ባለው የጊዜ ገደብ 163 ነጥብ 7 ዶላር (4 ሺሕ 759…

1 ሺሕ 5 መቶ ሔክታር መሬት ለአልሚዎች ሊሰጥ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ 1 ሺሕ 5 መቶ ሔክታር መሬት በግሉ ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚ ድርጅቶች ሊሰጥ እንደሆነ ታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የ2011 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንደገለፁት የከተማዋ ነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር…

የወርቅ ንግድ ከ430 ሚሊዮን ወደ 32 ሚሊዮን ዶላር አሽቆለቆለ

በ2006 አካባቢ ከወጪ ንግድ ከቡና ንግድ ቀጥሎ 430 ሚሊዮን ዶላር ይገኝበት የነበረው የወርቅ ንግድ ባለፈው ዓመት ወደ 32 ሚሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉ ታወቀ። ወርቅ፣ ኦፓል፣ ሳፋየር፣ ታንታለም፣ እምነበረድ እና የመሳሰሉትን ለውጭ አገር የምታቀርበው ኢትዮጵያ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚሆኑ ሌሎችንም ማዕድናት ታመርታለች።…

በየመን 15 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞቱ

ከጅቡቲ ወደ የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ 15 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው እንዳለፈ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ከሞቱት ኢትዮጵያውያን አንዳንዶቹ በረሃብ እና በውሃ ጥም፣ የተቀሩት ደግሞ በውሃ ውስጥ ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን ከአደጋው የተረፉት እንደተናገሩ ድርጅቱ ረቡዕ፣ ሐምሌ 24 ማታ…

ብሔራዊ አልኮል ፋብሪካ 850 ሚሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ

የብሔራዊ አልኮል ፋብሪካ በ2011 በጀት ዓመት ካመረታቸው 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር አልኮል መጠጦች እና 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሊትር ንፁሕ አልኮል 850 ሚሊዮን ብር ማግኘቱን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል። ፋብሪካው በ2011 በጀት ዓመት ያገነው ገቢ አሳካዋለሁ…

በአፋር ክልል በተነሳ አውሎ ንፋስ ከ70 በላይ ሰዎች ቆሰሉ

ሐምሌ 24/2011 በአፋር ክልል በአሳኢታ ከተማ በተነሳ አውሎ ንፋስ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸው የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 5 ሰዎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ መላካቸውንም ለማወቅ ተችሏል። ንፋሱ “ቦራውሊ” የሚባለው የስደተኞች ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣…

በሐዋሳ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ ሐዋሳ ጨምሮ በሲዳማ ዞን በተለያዩ ከተሞች ሰሞኑን በደረሰው ደም አፋሳሽ ግጭት የተጠረጠሩ ዘጠኝ ሰዎች ዓርብ፣ ሐምሌ 26 ፍርድ ቤት ቀረቡ። በግጭትና ግድያው ተጠርጥረው ከተያዙና ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ፣…

ሦስት ፓርቲዎች የምርጫ ረቂቅ ሕግ ውይይትን ረግጠው ወጡ

በኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ ውይይትን ከተሳተፉት መካከል የሦስቱ ፓርቲ ተወካዮች ረግጠው መውጣታቸውን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድረ ገጽ ላይ የወጣው መረጃ አስታውቋል። ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ምርጫና የፖለቲካ…

ደኢሕዴን ከፍተኛ ባለሥልጣኖቹን አገደ

የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ገዢ ፓርቲ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) የሲዳማ ዞን አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ከኀላፊነታቸው አገደ። በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ የታለፉ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት መኖራቸውንም አዲስ ማለዳ ከክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። ከታገዱት ባለስልጣናት…

ሐሰተኛ ምስክሮችና ሰነዶች በፍትሕ አሰጣጥ ሒደቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው

ለፍርድ ቤቶች የሚቀርቡ ሐሰተኛ ምስክሮችና ሰነዶች የወልና የግለሰብ መሬቶችን በማይገባቸው ሰዎች እጅ እንዲያዙ እያደረጉ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት አስታወቁ። የ2011 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ለክልሉ ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ያቀረበው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣…

ቴዲ አፍሮ እና ደራርቱ ቱሉ በአሜሪካ ተሸለሙ

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ መሸለማቸው ታወቀ። ሐምሌ 13/2011 በዋሽንግተን ዲሲ የአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት ቴዎድሮስ ካሳሁንን በአፍሪካ ወጣቶች ላይ ላበረከተው መልካም አርዓያነት የዕውቅና ሽልማት ሰጥቶታል። በዚሁ ወቅትም የጽሕፈት ቤቱ ዋና…

ዛይ ራይድ ለ200 ሴቶች ታክሲ ገዝቶ ሊሰጥ ነው

በአዲስ አበባ የታክሲ ትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት ከሚሰጡት ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዛይ ራይድ 200 መቶ ሴቶች ከባንክ ብድር በማመቻቸት ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎችን ገዝቶ ሊሰጥ እንደሆነ አስታወቀ። ኩባንያው ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመነጋገር ሰርተው መለወጥ ለሚፈልጉ ሴት አሽከርካሪዎች የመኪኖችን ዋጋ 70…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በታሪክ ከፍተኛውን የመንገደኛ ቁጥር አስተናገደ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሐምሌ 10/2011 በታሪኩ ከፍተኛ ያለውን የመንገደኞች ቁጥር ማስተናገዱን አስታወቀ። በዚሁ ቀን 310 በረራዎችን ከመላው ዓለም ወደ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ እና ከቦሌ አየር ማረፊያ ወደ ተለያዩ አየር መንገዱ መዳረሻዎች ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል። ከተደረጉት 310…

ዘመቻ ሙሴ በፊልም ሊመጣ ነው

ኢትዮጵያ በእርስ በርስ ጦርነት በምትታመስበት ወቅት በርካታ ቤተ እስራኤላዊያንን ከሱዳን ወደ እስራኤል ለማሻገር የተደረገው ዘመቻ በአሜሪካው የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ሥመ ጥሩ ኩባንያ ‹ኔት ፊሊክስ› ተሠርቶ መጠናቀቁ ከወደ አሜሪካ ተሰምቷል። ‹ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት› በሚል ርዕስ የተሠራው ፊልሙ፤ የጌዲዮን ራፍ ድርሰት ሲሆን…

በመቀሌ ዙርያ የእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ከ400 በላይ ቤቶችን አፈረሰ

በመቀሌ ዙርያ የእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ከ400 በላይ “ሕገ-ወጥ ናቸው” ያላቸውን ቤቶች ማፍረሱ ታወቀ። “ከኻያ ዓመት በፊትም ሆነ በቅርቡ የተሠሩ ቤቶች በአንድ ላይ መፍረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የእንደርታ አካባቢ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ እንደገለጹት፣ የወረዳው አስተዳደር በልዩ ኀይል እና በፖሊስ ታጅቦ ነው…

በአገር ዐቀፍ ደረጃ ከሚተከለው ችግኝ ግማሹ በአማራ ክልል ውስጥ ይተከላል

በሐምሌ 22/2011 በአገር ዐቀፍ ደረጃ እንዲተከል ዕቅድ ከተያዘለት 2 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ውስጥ 100 ሚሊዮን የሚሆነው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ እንደሆነ ታወቀ። የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ጌታቸው እንግዳየሁ ከአማራ ብዙኀን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ…

በአሜሪካን የኢትዮጵያን መንግሥት የሚቃወሙና የሚደግፉ ሰልፎች ተካሔዱ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ‹‹ኢንተርናሺናል ድራይቭ›› በተሰኘው ጎዳና ላይ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚያወግዙ እና የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሒደዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚመራውን መንግሥት የተቃወሙት ሰልፈኞቹ መንግሥት በአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አመራሮችና ደጋፊዎች ላይ የሚወስደውን…

ምፅዋን ከኢትዮጵያ የሚያገናኘው መንገድ በመጠናቀቅ ላይ ነው

ከኤርትራ ወደብ ከተማ ምፅዋ በመነሳት እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ የሚዘልቀው መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው። የመንገድ ግንባታው ከዚህ ቀደም የነበረውን የገጠር ጠጠር መንገድ የማሻሻል ሥራ ሲሆን በርካታ ኪሎ ሜትሮችንና ከተማዎችን እንደሚያቋርጥ ታውቋል። በኹለቱ አገራት የሚኖረውን የንግድ እና ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች…

አዴፓ ለሕወሓት መግለጫ ምላሽ ሰጠ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በማካሔድ ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 ሕወሐት ለሰጠው መግለጫ ምላሽ ሰጥቷል። በመግለጫው አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ሕወሓትን ተጠያቂ አድርጓል፤ የሕወሐትን መግለጫም የአማራን ሕዝብ ሕልውናና ክብር የማይመጥን ብሎታል። ሕወሓት በሰጠው መግለጫ…

የአብን ሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ በድጋሚ ታሰሩ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሥራ አስፈፃሚ አባል እና የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ክርስቲያን ታደለ ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 በድጋሚ መታሰራቸው ታወቀ። ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከዚህ ቀደም በቁጥር ሥር የዋሉትን የንቅናቄውን አባላት ለመጠየቅ በሔዱበት በሥፍራው በነበሩ የደኅንነት አባላት ተይዘው…

በሶማሌ ክልል ለተፈናቃዮች የሥነ አዕምሮና ልቦና ድጋፍ አገልግሎት እየተደረገ ነው

በሶማሌ ክልል ከዚህ ቀደም ተከስቶ በነበረው ግጭት ከቀያቸው ተፈናቅለው ለነበሩ ወገኖች የሥነ አዕምሮና የሥነ ልቦና ድጋፍ አገልግሎት ከክልሉ በሰለጠኑ ባለሙያዎች አማካይነት በኮሎጂ የተፈናቃዮች ካምፕ እየተሰጠ መሆኑን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል። ተፈናቃይና ተመላሽ ወገኖች በሚገኙባቸው ወረዳዎች ወረርሽኞች እንዳይከሰቱም የቅድመ…

57 የምግብ ምርት ዓይነቶችን ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ተከለከለ

የኢትዮጵያ ምግብ መድኀኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን 57 የተለያዩ ዓይነት የምግብ ምርቶችን ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ። ባለሥልጣኑ የገበያ ጥናት ባደረበት ወቅት ምርቶቹ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜያቸው በትክክል ያልተጻፈ፣ የተመረቱበት ጊዜ ያልተጠቀሰ፣ እንዲሁም አምራች ድርጅቶቻቸው ያልታወቁ መሆናቸውን ካረጋጋጠ በኋላ ነው ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው…

“ባለአደራ ምክር ቤት” ረቡዕ የሰጠው መግለጫ ባልታወቁ ሰዎች ተበተነ

የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) አመራሮች ረቡዕ፣ ሐምሌ 3/2011 በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ በመስጠት ላይ ሳሉ 7 በሚሆኑ ማንነታቸው ባልታወቁ ወጣቶች በተፈጠረ ኹከት ሊቋረጥ ችሏል። ኹከት ለመፍጠር መግለጫ ወደሚሰጥበት ቦታ ጎራ ያሉት ወጣቶቹ ባንዲራና ስለታማ መሣሪያ ይዘው እንደነበረም ለማወቅ…

ለውጪ ገበያ የሚቀርብ ከ58 ሺሕ ኪ.ግ በላይ ቡና ተዘረፈ

በያዝነው ዓመት ወደ ውጪ በመላክ ላይ የነበረ ከ58 ሺሕ ኪሎ ግራም በላይ ቡና በመንገድ ላይ መዘረፉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ አስታወቀ። እነዚህ ቡናዎች የተዘረፉት ከአምስት ድርጅቶች ብቻ መሆኑንም ገልጿል። ባለቤትነቱ የአቦሀ ትሬዲንግ የሆነ 6 ሺሕ 360 ኪሎ ግራም…

This site is protected by wp-copyrightpro.com