መዝገብ

Category: ትንታኔ

የላዳ ታክሲዎች እጣ ፋንታ

ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ነው የስድስት ልጆችም አባትም ናቸው ካሳሁን ማንደፍሮ፤ የሚተዳደሩት በታክሲ ሥራ ነው ። የላዳ ታክሲ ማለታችን ነው። አዲስ ማለዳም ካሳሁንን ሥራ እና ሕይወት እንዴት ነው? ብላ የጥያቄዎቿን መጀመሪያ አደረገች። ካሳሁን ማደፍሮም በቁጭት እና በምሬት ‹‹ሥራው በጣም ተበላሽቷል…

እምቦጭን በአንድ ወር ዘመቻ

የእምቦጭ አረም የጣና ሐይቅ ላይ መታየት ከጀመረበት 2004 ጀምሮ እምቦጭን ለማጥፋት የተደረጉ በርካታ እንቅስቃሴዎችእንደነበሩ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ ውጤታማነታቸው እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ሐይቁን ግን በጥቂቱም ቢሆን በነብስ እንዲቆይ ያደረገው ነበር። ይህን መጤ አረም ግን ከዚህ ቀደሙ በተለየ ሁኔታ ለአንድ…

የበረሃ አንበጣ አስከፊ ጉዳት ከአርሶ አደር ማሳ

ተሾመ ላቀው ወጣት አርሶ አደር እና የሦስት ልጆት አባት ነው። ተሾመ ኗሪነቱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ ጀብ ውሃ ቀበሌ ነው። አዲስ ማለዳ በአማራ ክለል በተወሰኑ ወረዳዎች ተከስቶ የአርሶ አደሩን ሰብል በከፍተኛ ሁኔታ አያወደመ የሚገኘውን የበረሃ አንበጣ…

የምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት አሃዞች ሲፈተሹ

እንግዲህ የ2013 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ ልዩ ስብሰባ በሳምንቱ መጀመሪያ ተካሂዷል።ስድስተኛ የሆነ የፓርላማ ዓመት ስብሰባ ሲካሄድ ያሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ማለትም በዘመነ ኢሃዴግ ከዛም ብልፅግና ሀገሪቱ መተዳደር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ።ከመደበኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ…

መንግሥት በአምበጣ መከላከል ላይ ምን ድረስ ሄዷል?

መንግስት ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት እያሳየ ያለበት ሁኔታ መሻሻል ቢኖረው በየዘርፉ ትክክክለኛውን አቅጣጫ ማስቀመጥ መለመድ አለበት በማለት መንግስት ተዘናግቷል የሚሉት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት መስከረም አበራ ናቸው ፡፡አሁን ላይ እንደዚህ ከመራገቡ በፊት በአንበጣ ዙርያ ተደጋጋሚ ጥቄዎች እና ቅሬታዎች ጥቆማዎች ሲነሱ መንግስት…

የኮቪድ-19 መከላከያ መመሪያ ሲፈተሸ

ዓለም የተፈተነችበት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች ከግስጋሴያቸው የገታ ብርቱ ቀበኛ፣ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ግንኙነቶች እንዲሁም ማህበራዊ መስተጋብሮችን በእጅጉ ገድቦ ቁጥጥር ስር ያዋለ ውረርሽኝ ነው። በአገረ ቻይና ውሃን ግዛት በወርሃ ታህሳስ 2012 መከሰቱ በግልጽ ለዓለም ህዝብ ይፋ ሆነ። ባልተገመተ እና ከአውሎ ንፋስ…

በመረጃ የመጥለቅለቅ አደጋን በኃላፊነትና በተዓማኒነት መጋፈጥ

ከመንግሥትና ከሕዝብ መካከል ሆኖ እንደ ዐይን ደግሞም እንደ ጆሮ የሚያገለግለው የብዙኀን መገናኛ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ተገኝቷል። እንደውም የሚፈተንበት ጊዜ ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱ ደግሞ ሁሉም ያሻውን በአጭር ፍጥነት ለብዙዎች ማድረስ የሚችልበት አውድ በተፈጠረበት ዘመን፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ የሆነውን ነገር…

90 ዓመታት የአልበገር ባይነት ጉዞ

አገር በዜጎች ይገነባል። ዜጎቿ በየትኛውም አስተሳሰብ ደረጃ እና ንቃተ ሕሊና ቢሆኑ ለአገር ግንባታ እና ለአገር ማቆም ሁሉም እኩል ባለቤትነት እና ደርሻ ይኖራቸዋል። በዜጎች መፈቃቀድ እና መደጋገፍ ላቅ ሲልም መወቃቀስ አገር ከዘመመችበት ትቃናለች፤ ከወደቀችበት ትነሳለች፤ በከፍታም ላይ ከሆነች ከፍ ብላ ልዕልናዋን…

 የዋስትና መብት መነፈግ በህግ ባለሙያዎች እይታ

የሰሞነኛው የአገራችን የፍርድ ቤት ውሎን በተመለከተ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው እንግዳ መሳይ ክስተቶች መካከል ዳኞች ግራ ቀኙን ተመልክተው  ተከሳሽ ተጠርጥሮ የተያዘበትን ጉዳይ ካመዛዘኑ ፍርድ ቤት የሚሰጧቸው የዋስትና መብቶች ተፈፃሚነት በፖሊስ መደነቃቀፉ ነው፡፡ ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የሰጣቸውን የዋስትና መብት ተጠቅመው የተጠየቁትን የዋስትና ማስያዣ…

የጎርፍ መጥለቅለቅና የተጎጅዎች ድጋፍ እጥረት

በኢትዮጵያ በዘንድሮው ክረምት ዝናብ በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመጣሉ በተለይም በአፋር፣ በጋንቤላ እንዲሁም በአማራ ክልል በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በርካታ የግብርና ስብል ልማቶች ወድመዋል። ጎርፍ መጥለቅለቅ ባጋጠመባቸው አንዳንድ ቦታዎች እስካሁን ድረስ መሰረታዊ አስቸኳይ እርዳታ እየተደረገ አለመሆኑን ተጎጅዎችና ተፈናቃዮች…

የዲዛይን ችግር የሚያንገላታው የአማራ ብልፅግና ፓርቲ

ብልጽግና ፓርቲ ኢሕአዴግን መተካቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደተሻለ መስመር ይወስዳል የሚል ተስፋ ሰጥቶ እንደነበር በማውሳት የሚጀምሩት መስከረም አበራ፤ የቀደሙ ፓርቲዎች ሥማቸውን ብቻ ሳይሆን በተግባርም እንደሚቀየሩ ይጠበቅ ነበር ብለዋል። በአንጻሩ ይልቁንም የቀድሞው ብአዴን አሁን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቀውንም ሆነ ቃል የገባውን ለውጥ…

የፈረቃ ትምህርት እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች

በአገራችን ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ጉዳይ በሚመለከት መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ከማወጅ ጀምሮ ረጅም መንገዶችን ተጉዟል። ይህ የሆነበትም ምክንያት የአኗኗራችን ዘዬ እና የበሽታው ፀባይ በእጅጉ የማይጣጣም በመሆኑ ከፍተኛ ዕልቂት በአደጉት አገራት ላይ እንዳደረሰው እኛም ጋር እንዳያደርስ ለማድረግ በመታሰቡ እና ከአደጉት…

የዐቢይ መንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Abiynomics) “ስኬቶች”

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ዓለም የተለያዩ ችግሮችን በስፋት አስተናዳለች። የምጣኔ ሀብት ጉዳይም በዚህ የፈተና ወጀብ ውስጥ የተገኘ ሲሆን፣ በዚህም ካደጉ አገራት ይልቁ ጫናው በደሃና አዳጊ አገራት ላይ ሊበረታ እንደሚችል ገና በማለዳው ነበር ሲተነበይ የነበረው። ሽመልስ አረአያ (ዶ/ር) ይህን የኢትዮጵያን…

2013 ተስፋና ስጋት

የ2013 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የተለያዩ ሰዎችን ያነጋገረችው አዲስ ማለዳ ዕይታቸውን እና መልካም ምኞታቸውን እንደሚከተለው ተቀብላለች። ኡስታዝ አቡበከር መሃመድ የእስልምና ሃይማኖት መምህር ኡስታስ አቡበከር ከአዲስ ማለዳ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንኳን አደረሳችሁ…

‹ታሪክ›ን መሣሪያ ያደረገ የፖለቲካ አካሄድና ያስከተላቸው ችግሮች

በኢትዮጵያ አሁን ላይ የሚታዩ የፖለቲካ አሰላለፎች የኋላ ‹ታሪክ›ን መሰረት ያደረጉ ይመስላሉ። አንዳንዶችም እንወክልሀለን ያሉትን ሕዝብ ለማሳመንና መሪውን ለመጨበጥ፣ ተከታይ ሕዝብ በመስመራቸው ለማዥጎድጎድ ታሪክን ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ይህንን ሀቅ የሚሳዩም እልፍ አእላፍ ማስረጃዎች አሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው የቀደሙ ታሪኮችን በተዛባና በተጋነነ መንገድ…

ወቅታዊውን ሀገራዊ ሁኔታ የዳሰሰው ሪፖርት

የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጣ በወራት ጊዜ ውስጥ በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የተስተዋለው ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ከቃላት ጦርነት አልፎ ወደ ግጭት የማምራት እድሉ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው።የሃይማኖት አባቶችን ያካተተው የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን ተቀራርቦ መነጋገር ይቻል…

የሰሞኑ የወላይታ ዞን ኹነት እና የደቡብ ክልል ቀጣይ ፈተናዎች

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለዘመናት ሲንከባለሉ ከቆዩ የረዥም ጊዜ በርካታ ጥያቄዎች መካከል የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎች ግንባር ቀደም ከሚባሉት ውስጥ ናቸው።በተለይም ከመጀመሪያው ጥናት ተደርጎባቸው እልባት ያላገኙ ጥያቄዎች ለዘመናት ሲንከባለሉ በመቆየታቸው አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ችግር አፈታት ስልት ውስብስብ እንዳደረገው…

በትግራይ ክልል የተካሄው ወታደራዊ ትርኢት ለምን አስፈለገ?

‹‹በወጣቶች የደም ግብር ታጅቦ የሰልጣን ዘመንን የማራዘሙ የህውሃቶች እኩይ ተግባር ነው።›› ፈንቅል ከሰሞኑ ከወደ ትግራይ ክልል፤ መሃል አገር በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሊትን በመመርኮዝ ‹‹ድምጻችን ለግድባችን›› በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ እና ሌሎች ኢትዮጵያ ክፍሎች አገር በተደሰተበት ወቅት አንድ ጉዳይ…

እህትን ለመጠበቅ…ትክክለኛው ጊዜ

የቤት ውስጥ ጥቃት ከኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ብቻ 20 በመቶ ጨምሯል፤ የተባበሩት መንግሥታት። ‹አድርጉልኝ!› ‹ለውጡልኝ› ‹አሻሽሉልኝ› ‹ችግር አለና እወቁልኝ› ይህና ይህን መሰል ጥሪ አስቀድሞ ይመለከታቸዋል ላላቸው አካላት ያቀረበ ሰው፣ ምላሽ ካላገኘ ውሳኔዎችንና እርምጃዎች በእጁና በፈቃዱ ላይ ለማኖር…

የማይነጥፉ የሚመስሉ እምባዎች

ስፍራው የካ ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ልዩ ስሙ ኮተቤ መሳለሚያ አካባቢ። አዲስ ማለዳ በአንዲት አነስተኛ ጊቢ ውስጥ በወጉ መራራቅ እንኳን በማይቻልበት እና ከሰሞኑ በጥቂትም ቢሆን ሲያካፋ በነበረው ሰማይ የተነሳ ከፊል አረንጓዴ መልበስ የጀመረ ምስኪን ጊቢ ውስጥ ተገኝታለች።…

“ጣና” ትኩረት የተነፈገው ሕመምተኛ-እንደ አረል ሐይቅ

በዓለማችን በልዩ ልዩ ምክንያቶች ባለፉት 60 እና 50 ዓመታት ብቻ በሰው ልጅ ለተፈጥሮ በማይስማማ ተግባርና በአካባቢያዊ የአየርን ብረት ለውጥ ምክንያት በርካታ የውኃ አካላት እንዳልነበር ሆነዋል። ከእነዚህ ውሰጥ በስፋቱ ከዓለም 4 ደረጃ ላይ የሚገኘው በቀድሞዋ ሶቬየት ኅብረት ይገኝ የነበረው አረል ሐይቅ…

በዘመነ ኮሮና – መልክ ያጣው ትምህርት አሰጣጥ

ኤርሚያስ በለጠ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነው። ከአዲስ ማለዳ ጋር ባደረገው ቆይታ ዘንድሮ (2012) ተመራቂ እንደሆነና ልምምድ (apparent) ላይ እንደነበር ጠቅሷል። ከዛም ጎን ለጎን የመመረቂያ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ከጓደኞቹ ጋር እየተዘጋጀ እንደነበር አስታውሶ፤ ይሁን እንጂ መጋቢት…

ምርምርና ፈጠራን ያነሳሳው ኮቪድ 19

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (AASTU) የቴክኖሎጂ ለውጦችና ሽግግሮችን የማድረግ እቅዱን ይፋ ያደረገው ከወራት በፊት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ወር ላይ ነበር። እነዚህም ለውጦች የማኅበረሰቡን ሕይወት በበጎ ጎን የሚቀይሩ እንደሚሆኑ አጽንኦት መስጠቱንም የተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። በዛው ጊዜ…

“ጅብ የማያውቁት አገር ሔዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ“ (የምክር ቤት አባል ተስፋየ ዳባ) “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ዥግራ ናት ይሏታል“ (የምክር ቤት አባል ገብረእግዚአብሔር አርአያ)

“ጅብ የማያውቁት አገር ሔዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ“ (የምክር ቤት አባል ተስፋየ ዳባ) “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ዥግራ ናት ይሏታል“ (የምክር ቤት አባል ገብረእግዚአብሔር አርአያ) በአገር አቀፍ ደረጃ በየአምስት ዓመቱ እንዲካሔድ በሕገ መንግሥቱ የተቀመተው አገራዊ ምርጫ በዚህ ዓመት ነሐሴ /2012 እንዲካሔድ ቀን…

ዓለም አቀፋዊ የኮሮና መረጃዎች

ቬትናም በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበባት እና ስርጭቱ በአጭር የተቀጨባት አገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኹለት መቶ ሽ በላይ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአገረ ቬትናም ቢከሰትም ምንም አይነት ሞት አልተዘገበም። ቬትናም ከቻይና ውጭ ያሉ አገራት ቫይረሱ በተዛመተ ወቅት ቀዳሚ…

አዲስ አበባን – ‹ምድራዊ ገነት› የማድረግ ጉዞ

የከተማ ግብርና ባልተለመደባቸው አካባቢዎች ቃሉ ራሱ አሻሚ ይመስላል። ከተሜነትን ከግብርና መላቀቅ ተደርጎ በሚታሰብበት ሁኔታም ‹የከተማ ግብርና› አበባን ወይም ለጊቢ ውበት ዛፍን ከመትከል የዘለለ አድርጎ ማሰብ የሚችል ጥቂት አይደለም። በእርግጥ በአዲስ አበባ የጓሮ አትክልት የብዙ ቤተሰብን የምግብ ፍጆታ በተወሰነ መልኩ ይሸፍንና…

ፈትፋች የበዛበት የወረርሽኙ ውሳኔ፡ በአገራት እና በኢትዮጵያ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከሰት ተከትሎ የተለያዩ አገሮች ጊዜያቸውን ቆፍጠን ብለው ወረርሽኙን በሙሉ ኃይል ከመዋጋት ይልቅ የአስጊነት ደረጃው ላይ ጥርጣሬ በማሳደር የጤና ባለሙያዎች ምክሮችን ለመተግበር ዳተኛ ሲሆኑ ታይተዋል። ፖለቲከኞች በየትኛውም አገራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴያቸው ውስጥ ፖለቲካቸውን ማራመድ ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ተግባራት…

ድህረ-ዘመናዊነት፡ ቀጣዩ የሃይማኖቶች ጉባኤ የቤት ሥራ

ያለፉት ኹለት ዓመታት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወገን በፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች በሚሰጡ አጥፊ አጀንዳዎች ሕይወቱን ያጣባቸው፣ ደህንነቱን የተነጠቀባቸው እና ያፈራውን ንብረት ያጣባቸው ነበሩ። ባለፈው አንድ ዓመት የታየው አዲስ ጉዳይ ደግሞ ግጭቶች ኃይማኖታዊ መልክ እንዲይዙ እየተደረጉ መሄዳቸው ነው። አብዛኛውን ሕዝብም በግጭቶቹ ተሳታፊ…

የሕክምና ባለሙያዎች እንግልት

ሰሚራ አሕመድ ትባላለች (ሥሟ የተቀየረ) በአንድ የመንግሥት ሆስፒታል ውስጥ በከፍተኛ ነርስ ሙያ እንደምትሠራ ትናገራለች። ሰሚራ በቅርቡ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ብሎም በአገራችን ኢትዮጵያ የተሰራጨውን የኮሮና ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከወትሮው በተለየ መልኩ የሥራ ጫና በዝቶባታል። ሕዝብን እና አገርን ለማገልገል በገባችበት የሙያ…

የኮቪድ 19 ዳፋ – በኢትዮጵያ

ዓለም ዐቀፉ ወረርሽኝ ኮሮና ኮቪድ19 በተለያዩ የዓለም አገራት በተለይም ደግሞ በምጣኔ ሀብት ደርጅተዋል በተባሉ አገራት ላይ ቁጣ ሽመሉን አጠንክሮ ቀጥሏል። ይህንንም ተከትሎ ችግሩ በስፋት የተከሰተባቸው የዓለም አገራት በርካታ እንቅስቃሴዎቻቸውን እና የዕለት ተዕለት ክንውኖቻቸውን እንዲገቱ ተገደዋል። በተለይ ደግሞ ታላላቅ አየር መንገዶች…

This site is protected by wp-copyrightpro.com