መዝገብ

Category: አቦል ዜና

ተክለ ብርሃን አምባዬ በ73 ሚሊዮን ብር ግብር ስወራ ተከሰሰ

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽንን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ ተቋራጮችን በግብር ስወራ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በስምንተኛ እና ዐስረኛ ወንጀል ችሎቶች ክስ መሰረተ። በኢትዮጵያ ካሉ የደረጃ አንድ ተቋራጮች መካከል እንዲሁም ከፍተኛ አቅም ካላቸው መካከል የሆነው ተክለ ብርሃን አምባዬ…

ለማ መገርሳ የኢሕአዴግን ውሕደት ተቃወሙ

የመከላከያ ሚኒስትር፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር እንዲሁም የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለማ መገርሳ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሚቀነቀነውን የመደመር ፍልስፍና እንደዚሁም የብልፅግና ፓርቲ አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ላይ እንደማይስማሙ ገለጹ። ለማ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የኦሮምኛ ፕሮግራም ጋር ባካሔዱት…

ከመመሪያ በታች ያሉ ሕጎች እንዳይኖሩ የሚከለክል አዋጅ ተረቀቀ

የአስተዳደር መመሪያዎችና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት በመሔድ የሚከሰሱበትን ሥነስርዓት ይደነግጋል የፌዴራል የአስተዳደር ተቋማት ማኑዋል፤ ጋይድላይን፤ ሰርኩላር እና ደብዳቤን እንዳይጠቀሙ የሚያደርገው አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ቀረበ። መመሪያ ማለት ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ሥልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም የሚወጣና…

በ 300 ሚሊዮን ብር የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ሊገነቡ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 12 ገጠራማ እና ከዋና የኤሌክትሪክ መስመሮች ርቀው የሚገኙ ከተሞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ መጀመሩን እና በስድስት ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ገለፀ። ፕሮጀክቶቹ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል…

የመኪና ማስዋቢያ ምርቶችን አመሳስሎ ያስመጣው ድርጅት ተቀጣ

የመኪና ውስጣዊ አካላትን ማስዋቢያ የቅባት ምርቶችን አመሳስሎ ወደ አገር ውስጥ ያስገባው አዲስ አሊ መኪና ዕቃዎች አስመጪ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር በመፈፀም በሸማቾች ጥበቃ እና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን በተመሠረተበት ክስ የባለሥልጣኑ አስተዳደራዊ ችሎት ከዓመታዊ ገቢው ላይ ዐስር በመቶ ቅጣት ጣለበት። በተባበሩት…

ያለአግባብ ተሰቅሎ የቆየው የሰሊጥ ዋጋ በግማሽ ቀነሰ

በአገር ውስጥ ገበያ የሰሊጥ ዋጋ በግማሽ የቀነሰ ሲሆን በግብይት ሰንሰለቱ የመንግሥት የመቆጣጠር ብቃት ማነስ ዋጋው ባልተገባ ሁኔታ ንሮ ለመቆየቱ በዋነኛ ምክንያትነት ተጠቅሷል። ላኪዎች የሰሊጥ ምርትን ከአገር ውስጥ ገበያ ዋጋ በላይ በመግዛት ለዓለም አቀፉ ገበያ ባነሰ ዋጋ የሚያቀርቡበት ከስርዓት የወጣ ግብይት፣…

ከጨርቃ ጨርቅ የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ የ 17 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳየ

የጨርቃ ጨርቅ እና የስፌት ምርቶችን ወደ ተለያዩ አገራት በመላክ ባለፉት ሦስት ወራት ከ 52 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ 17 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱ ይፋ ተደረገ። የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች፣ ያለቀላቸው አልባሳት፣ ድር እና…

አጓትን ከሌሎች ምግቦች ጋር በመቀላቀል የምግብ ይዘትን ለማሻሻል እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ

የወተት ተረፈ ምርት የሆነውን አጓት ከተለያዩ ምግቦች ጋር በመቀላቀል ኅብረተሰቡ የተሻለ የፕሮቲን ይዘት ያላቸውን ምግቦች እንዲያዘወትር ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ስጋና ወተት አንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የወተት ተረፈ ምርት የሆነው አጓት፣ አይብ ከተመረተ በኋላ የሚቀር ሲሆን በኅብረተሰቡ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ…

የአማራ የስለላ እና ደኅንነት ድርጅት በሚል የተቋቋመ ሕገ ወጥ የስለላ ቡድን ነበር ተባለ

ባሳለፍነው ሳምንት ኅዳር 12/ 2012 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከ ሰኔ 15/2011 ጥቃት ጋር ተያይዞ ከተከሰሱት 13 ግለሰቦች ውስጥ ዘጠኝ ተከሳሾች ከክልሉ መደበኛ የፀጥታ መዋቅር ውጪ የአማራ የስለላ እና ደኅንነት ድርጅት (አሳድ) በሚል ቡድን በማቋቋማቸው ክስ ተመስርቶባቸዋል።…

የጥበቃ ሥራውን ሽፋን በማድረግ ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

አሕመድ ናጁ ሙክታር በተባለ የመኪና አስመጪ ድርጅት በጥበቃነት ይሠራ የነበረው መላኩ ሹመይ ሳሙን የአሠሪውን ቶዮታ ሪቮሉሽን ድብል ጋቢና መኪና በመስረቅ ክስ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ጥቅምት 26/2012 በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው የ6 ዓመት ከ6 ወር እስራት…

ከመመሪያ በታች ያሉ ሕጎች እንዳይኖሩ የሚከለክል አዋጅ ተረቀቀ

• የአስተዳደር መመሪያዎችና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት በመሔድ የሚከሰሱበትን ሥነስርዓት ይደነግጋል የፌዴራል የአስተዳደር ተቋማት ማኑዋል፤ ጋይድላይን፤ ሰርኩላር እና ደብዳቤን እንዳይጠቀሙ የሚያደርገው አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ቀረበ። መመሪያ ማለት ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው የውክልና ሥልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም…

ከአዋሽ ቁልቢ የሚወሰደው መንገድ ሊታደስ ነው

የኢትዮጲያ መንገዶች ባለሥልጣን በኦሮሚያ ክልል ከአዋሽ መኢሶ እንዲሁም ከአዋሽ ቁልቢ ድሬዳዋ ያሉት ኹለት መንገዶች እንደሚታደሱ ገለፀ። የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን እንደገለጸው፤ መንገዶቹ ለትራንስፖርት አመቺ ያልሆኑ በመሆናቸው መልሶ የመገንባት እንዲሁም የተሻሉ መስመሮችን የመዘርጋት እቅድ አለው። ባለሥልጣኑ አክሎም ባወጣው የጨረታ ማስታወቂያ የአገር ውስጥ…

በመቀሌ ከተማ ስድስት መቶ ሰዎች የሚሳተፉበት የፌደራሊዝም ጉባኤ ሊካሔድ ነው

ከወራት በፊት መቀሌ ከተማ የተቋቋመውን እና በዋናነትን የፌዴራል ስርአቱን ከአህዳዊ ስርአት ለመታደግ በሚል የተደረገው ጉባኤ ቀጣይ የሆነ የምክክር መድረክ በመጪው ሳምንት ማክሰኞ በመቀሌ ከተማ ስድስት መቶ ሰዎች በተገኙበት ሊካሔድ ነው፡፡ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከምሁራን እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት አምስት ሰዎች ከመላው…

ወደ መኖሪያ ቀበሌዎች የገቡት አምስት አንበሶች ጉዳት አደረሱ

የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለሥልጣን ጉዳዩን አስተባብሏል ከአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በመውጣት በፓርኩ አካባቢ በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ የገቡት አምስት ጥቁር አንበሶች በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን እና የከፋ ጉዳት እንዳያደርሱ እንዲሁም አንበሶቹ ላይም ጉዳት እንዳይደርስ ስጋት አድሮብኛል ሲል ፓርኩ…

የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ዋጋ እስከ 20 ብር ሊቀንስ ይችላል ተባለ

ከቀረጥ ነጻ እንዲሆን ተጠይቋል የወር አበባ የንጽህና መጠበቂያ ለረጅም አመታት ቀረጥ ሲጣልበት ከነበረው የቅንጦት እቃዎች ዝርዝር በመውጣት በመድኃኒት ጤና አገልግሎት ዘርፍ እንዲካተት የጤና ሚኒስቴር በወሰነው መሰረት የህግ ማእቀፍ ተዘጋጅቶ ወደተግባር ሲገባ በአንድ እሽግ ምርት ላይ እስከግማሽ ድረስ የዋጋ ቅናሽ ሊያሳይ…

በአምቦ ውሃ እና ኮካ ኮላ ላይ ተጥሎ የነበረው ቅጣት ውድቅ ተደረገ

የሸማቾች ጥበቃ እና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት አምቦ ውሃ እና ኮካ ኮላ ውህደት ፈፅመዋል በማለት ከዓመታዊ ገቢያቸው ላይ አምስት በመቶ እንዲቀጡ አስተላልፎት የነበረውን ወሳኔ ውድቅ በማድረግ ድርጀቶቹን በነፃ አሰናበተ። የባለሥልጣኑ ዐቃቤያን ሕግ ከጥር 2009 ጀምሮ የኹለቱ ድርጅቶች የሥራ…

ለአዲስ አበባ ከተማ 7.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት የሚያቀርቡ አራት ድርጅቶች ተመረጡ

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ለከተማዋ ሰባት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሊትር የፓልም ዘይት የሚያቀርቡ አራት ድርጅቶችን መርጦ ለንግድ ሚኒስቴር መላኩን እና ከዚህ ቀደም በጨረታ ሂደቱ ላይ ውዝግብ አስነስቶ የነበረው ጌታስ ኢንተርናሽናልም በሌላ አቅራቢ እንዲተካ መደረጉን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ፡፡…

ያለአግባብ የውጭ አገር ዜጎችን በሚቀጥሩ አምራቾች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ

በኢንዱስትሪ መንደሮች ውስጥ በአገር ውስጥ ዜጎች መሰራት እየተቻሉ ከህግ ውጪ ያለአግባብ የውጭ ዜጎችን ቀጥረው ለሚያሰሩ አምራቾች ላይ የቅጥርን ሁኔታ በመፈተሽ እርምጃ እንደሚወስድ እና ለዚህም የሚረዳውን ጥናት ማጠናቀቁን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ ሕዳር…

በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 27 ሺሕ ተፈናቃዮች ለወራት ያለ እርዳታ ቆይተዋል ተባለ

በአማራ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሉ ከ27 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች ምግብን ጨምሮ ምንም ዓይነት ድጋፍ ሳያገኙ ለወራት መቆየታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት (ኦቻ) ኅዳር 7/2012 ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ። በሪፖርቱ ላይ እንደተመለከተው፣ ተፈናቃዮቹ ድጋፍ እንዳያገኙ የኹለቱ ክልልች…

የኤሌክትሪክ አገልግሎት በራሱ ወጪ ለባቡር ፕሮጀከቶች ኃይል እንደማያቀርብ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር የአዋሽ-ወልዲያ-ሀራ ገበያ ለተዘረጋው የባቡር ሃዲድ የኀይል ማቅረቢያ መስመሮች ዝርጋታ ወጪን የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ካልሸፈነ በራሱ ወጪ ኀይል እንደማያቀርብ አስታወቀ። የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዋሽ-ወልዲያ-ሀራ ገበያ 392 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የባቡር መስመር…

የጎዳና ተዳዳሪዎቹን ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ ተቀጣ

• የሦስት ሰዎችን ሕይወት በተመሳሳይ አጥፍተዋል የተባሉት ግለሰብ አንድ ሰው ላይ ሙከራ አድርገዋል በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ኸለት ልዩ ሥሙ አሜን ሆስፒታል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሚሊዮን ዘሪሁን የተባለ የጎዳና ተዳዳሪ በሌላ ጎዳና ተዳዳሪ ላይ በበቀል ስሜት በመነሳሳት በፈፀመው…

በሶስት ወራት ከ 62 ሺህ በላይ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ለወንጀል መፈጸሚያነት ለማዋል የታሰቡ ልዩ ልዩ ጠመንጃዎች ፤ ጥይቶች ፤ ሽጉጦች ፤ ቦንቦች እንዲሁም የቡድን መሳሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ ከተያዙት የጦር መሳሪያዎችም ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው የጥይት ብዛት ሲሆን 52 ሺህ እንድ መቶ…

የቡና እና ቅመማ ቅመም የወጪ ንግድ የ25 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳየ

ኢትዮጵያ በ2012 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት ወደ 10 ዋና ዋና የቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ተቀባይ አገራት 103 ሺሕ ቶን ምርቷን በመላክ 288 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር የ35 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱ…

በያዝነው ወር በአዲስ አበባ የ20 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት በ2012 ግንባታቸውን ከሚያስጀምራቸው 150 ቤቶች ውስጥ ኹለተኛውን ዙር በ40 ቢሊዮን ብር ገደማ የ20 ሺሕ ቤቶችን ግንባታ በኅዳር ወር መጨረሻ እንደሚያስጀምር ታወቀ። በመላው ከተማዋ በሚገኙ ክፍለ ከተማዎች 300 ሄክታር መሬት ቦታ ለግንባታው እየተመቻቸ…

የፌደራል ድጎማ እና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ኮሚሽን ሊቋቋም ነው

በክልሎች እና በፌዴራል መንግሥት መካከል ያለውን የጋራ ገቢዎችን እንዲሁም የፌዴራል መንግሥቱ ለክልሎች የሚያደርገውን ድጎማ የሚያስተዳድር አዲስ ኮሚሽን ሊቋቋም ነው። ኮሚሽኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጥናት ላይ ተመሥርቶ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርብለት ሲሆን ራሱን የቻለ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ሆኖ የሚቋቋም ነው። እንዲሁም የክልሎችን…

ልማት ባንክ በሩብ ዓመቱ 213 ሚሊዮን ብር አተረፈ

የተበላሸ የብድር መጠን ከ39 በመቶ ወደ 33 በመቶ ዝቅ ብሏል በ2011 በጀት ዓመት ኪሳራ ውስጥ ገብቶ የነበረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2012 የበጀት ዓመት የመጀመሪያው ሦስት ወራት ከኪሳራ በመውጣት 213.77 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ገለጸ። ለትርፉ መጨመርም በባንኩ የተወሰዱ ልዩ ልዩ እርምጃዎች…

የህፃናቱን የንፅህና ክብር የተጋፋው ግለሰብ ተፈረደበት

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ የመድረሳ ቁርአን ቤት ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነት የመሰለ እና ለንጽህና ክብር ተቃራኒ የሆነ ድርጊትን በሦስት ሴት ህፃናት ላይ የፈፀመው ግለሰብ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርቦ ጥፋተኛ ተባለ። ግለሰቡ የግል…

በሳምንቱ በ13 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የፀጥታ ችግር ተከሰተ

የተወሰኑ ተማሪዎች በረሃብ ራሳቸውን መሳታቸውን ሰምተናል ቅዳሜ፤ ጥቅምት 29/2012 በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተ ግጭት የኹለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በመላው አገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ ጥቃት ሲሰነዘር እና የትምህርት ስርዓቱም ተቋርጦ ሰንብቷል። ይህንን ተከትሎ ከሰኞ ኅዳር አንድ እስከ አርብ ኅዳር አምስት ባሉት…

ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚደረግ የሸቀጦች ንግድ መቀዛቀዙ ተገለፀ

በሐረር እና በድሬዳዋ ከተሞች በተፈጠረው ግጭት ላለፉት ሦስት ቀናት ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሸቀጣ ሸቀጦችን ለመላክ ችግር እንዳጋጠመ በአዲስ አባባ የሚገኙ ነጋዴዎች ተናገሩ። ሸቀጦቹን ወደ አካባቢው ከመላክም በተጨማሪ ከ ጅቡቲ ወደ አዲስ አባባ የሚመጡ እቃዎችን ለማጓጓዝ ባለው ከፍተኛ ውጥረት ምክንያት…

በየዓመቱ መድኀኒት በተላመዱ በሽታዎች ምክንያት የ35 ሺሕ ሰዎች ሕይወት ያልፋል

በኢትዮጵያ የፀረ ተዋህስያን መድኀኒቶች በጀርሞች መለመድ ወይንም አልበገር ባይነት ምክንያት በየሰዓቱ የአራት ሰዎች ሕይወት እንደሚያልፍ ይፋ ሆነ። ችግሩ በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ 35 ሺሕ በላይ ሰዎች በዓመት ለሞት እንደሚዳረጉ ተገልጿል። የፀረ ተዋህስያን መድኀኒቶች…

This site is protected by wp-copyrightpro.com