መዝገብ

Category: ወቅታዊ

አዳዲሶቹ ጥምረቶች – እጅ ከምን

ሕወሓት መራሹ ኢሕአዴግ በሕዝብ ተቃውሞ ከፊት ተሰላፊውን ቡደን ቀይሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ከቀድሞ በተለዩ የፖሊስ እና የፖለቲካ ለውጦች አገር ማስተዳደር ከጀመረ ዓመት ከመንፈቅ አለፈው። ይህ ለውጥ ካስተናገዳቸው አዳዲስ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው ደግሞ ከዚህ ቀደም በዐይነ ቁራኛ ሲታዩ ከሰነበቱት፤…

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምክር ቤት ውሎ አንድምታዎች

ፕሬዝዳት ሳሕለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የ2012 የመክፈቻ ጉባኤ ላይ ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ በተወካዮች ምክር ቤቱ በጥቅምት 11/2012 የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአባላቱ የተነሱ ጥያቄዎች ላይ መልስ ሰጥተዋል። ይጀመራል ተብሎ ከተያዘለት ቀጠሮ ከአንድ ሰዓት ተኩል…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ – በደኅንነቱ ዋዜማ

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከወትሮው በተለየ አዲስ ስርዓት ይዞ እንደሚካሔድ ከተሰማ ቀናት አልፈዋል። ይህም ክለቦች ራሳቸውን ማስተዳደራቸውና ይህንንም በተመለከተ ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር መፋታታቸው ነው። ታድያ ባለሙያዎችና እግር ኳስ ጉዳይ ተንታኞች ሲናገሩ፤ ለውጡን በአግባቡ መምራት የሚችል አቅምና የክለቦች እርስ በእርስ…

ዝክረ ኤልያስ መልካ ሥም – ሥራ – ምግባር ከመቃብር በላይ

አንድን ክስተት መግቢያችን እናድርግ፤ በአንድ የኩላሊት እጥበት ማዕከል ውስጥ ነው። ለኩላሊት እጥበት በማዕከሉ ከተገኙ ሕሙማን መካከል አንድ ሰው ተከታዩን አደረገ። ቢጂአይ ኢትዮጵያ ታከምበት ብሎ ካኖረለት አንድ መቶ ሺሕ ብር ላይ ቀንሶ ለአንድ የኩላሊት እጥበት ታካሚ የዐሥር እጥበት ሒሳብ ከፈለ። በነገሩ…

ጉዞ ዓድዋ በዓድዋ ጉዞ ዋዜማ

ከ124 ዓመታት በፊት ጥቅምት 2/1888 ነበር የዓድዋ ጉዞ ጥሪ የተደረገው፤ አዋጅም የተሰማው። በዚህ የዳግማዊ አጼ ምኒልክ አዋጅ የጀመረው የዓድዋ ጉዞ ዛሬ ድረስ ዓለም የማይረሳውና የኢትዮጵያንም ሥም አድምቆ ያስመዘገበው ድል መዳረሻው ሆኗል። የሚያስማሙ ታሪኮች፣ ሐሳቦችና ጉዳዮች የተዘነጉ በሚመስልበት በአሁኑ ጊዜ እንደ…

ውዝግብ ያልተለየው የፖለቲካ ፓርቲዎችና ምርጫ ሕግ

አዲሱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ነሃሴ 18/2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ከ50 የማያንሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በተለይ የፓርቲዎች መመስረቻ ሕጉን ክፉኛ ሲቃወሙት ይደመጣል። “ሰሚ አላገኘንም እንጂ ፓርላማው እንዳያፀድቀው ቀድመን አቤት ብለን ነበር”…

በመንግሥት ትኩረት መነፈግ ዋጋ እየከፈለ ያለው አካል ጉዳተኝነት

በብሔራዊ ዐይነ ሥውራን ማኅበር ሥር በሚተዳደረው የወላይታ ዐይነ ሥውራን ትምህርት ቤት በማኅበሩ ድጋፍ ትምህርቱን ተከታትሎ፣ በዘንድሮ ዓመትም በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመምህራን ማሠልጠኛ ፕሮግራም በዲፕሎማ የተመርቀው ዐይነ ሥውሩ ድረስ ሁናቸው፣ ከሌሎች ተመራቂዎች ጋር ሥልጠና ወስዶ የሥራ ቦታ ለመመደብ ዕጣ የወጣለት…

በ2011 ቁጥሮች በሕይወት ዙሪያ ምን ይላሉ?

በሰው ልጅ ሕይወት ልደት፣ ጋብቻና ሞት ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ኩነቶች ሲሆኑ ፍቺና ጉዲፈቻ ደግሞ በመካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ ክስተቶች ናቸው። ታድያ እነዚህን ወሳኝ የሕይወት ክስተቶች ግለሰቦች በፎቶ ለማስቀረት፣ በመቅረጸ ምስል ለማቆየት ይጥራሉ፤ ትዝታን ለማቆየት። መንግሥት ደግሞ የኩነቶቹን ምዝገባ በእጅጉ ይፈልጋቸዋል፤ በአገሪቱ…

የጀነራሎቹ ስንብት

ቅዳሜ፣ ሰኔ 15/2011 ለኢትዮጵያ መልካም ቀን አልነበረም። ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መናገሻ ከሆነችው ባሕር ዳር እስከ ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ሰሚን የሚያደነዝዝ ዜና በአገሩ ናኘ። ሰባት የአማራ ክልል ቁንጮ ባለሥልጣናት ስለ ክልሉ መፃኢ እና ነባራዊ ሁኔታ እየመከሩ ባሉበት ወቅት ባመኑትና…

የመጨረሻው ስንብት

“አንድ ቀን ልዑሌን አገኘዋለሁ፤ አባቴ ግን ሁል ጊዜም ንጉሤ ነው” የሚል ጥቅስ ያረፈበት እና መዓዛ አምባቸው መኮንን ከአባቷ ጎን የሚታዩበት ምሥል አዲስ አበባ፣ ብሥራተ ገብርኤል አካባቢ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሳሎን ቤት መግቢያ በግራ በኩል አነስ ባለች ፍሬም ቢቀመጥም ከሩቁ ዓይን…

የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል የ50 ዓመት ጉዞ

ከማለዳ እስከ ረፋድ የማለዳዋ ፀሐይ ምድርን ልታሞቅ በምሥራቅ ስታጮልቅ ከወፎች ጋር አብረው እየዘመሩ ወደ ሥራቸው የሚያቀኑ የአትክልት ተራ ነጋዴዎችን፣ እቃ ጫኝና አውራጆችን እንዲሁም የአይሱዙ ሹፌሮችን በማለዳ በሯን ከፍታ የምትቀበለው, ለጎዳና ተዳዳሪዎች ቤት የሆነችው፣ መዝናናት ላማረው አገርኛ ፊልሞችን የሚያሳዩትን ሲኒማ አምፔር፣…

ውስብስቡ የአፋር-ሶማሌ ግንኙነትና የሦስቱ ቀበሌዎች ዕጣ ፈንታ

የምሥራቃዊ ኢትዮጵያ ኹለቱ ክልሎች አፋርና ሶማሌ ውጥረት ውስጥ የገቡ ይመስላሉ። ምክንያታቸው ደግሞ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከአራት ዓመታት በፊት በታኅሣሥ 2007 ላይ ሦስት በሶማሌ ክልል ይተዳደሩ የነበሩ ቀበሌዎችን ወደ አፋር ክልል እንዲዛወሩ መፍቀዳቸው እና…

አወዛጋቢው የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ ጉዳይ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋን ምርጫ ለዘንድሮ አስተላልፎ ነበር። ይሁን እና ዓመቱ ቢጋመስም በ2011 ይካሔዳል ስለተባለው የኹለቱ ከተሞች ምርጫን በተመለከተ ከምርጫ ቦርድ በኩል የተሰማ ነገር የለም። በጉዳዩ ላይ አዲስ ማለዳ ካነጋገረቻቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች…

የሕክምና ባለሙያዎቹ አብዮት

ክቡር የሆነው ሰው ልጅ ሕይወት በምድር ላይ በበርካታ እክሎች ሳቢያ መጓዝ ካለበት ርቀት ወይም መቆየት ካለበት ጊዜ አስቀድሞ ሊገታ ይችላል። ታዲያ ከእነዚህ እክሎች መካከል በሽታ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል – በተለይ ደግሞ በአዳጊ አገራት ላይ። በጤና ላይ በሚያጋጥም ሳንካ እንደየማኅበረሰቡ የንቃተ…

የሥጋ ነገር

በተለምዶ ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው አንድነት ሥጋ ቤት በተቆጣጣሪነት የምታገለግለው ምዕራፍ ትዕግስቱ የሥጋ ተመጋቢ ደንበኞች የሥጋ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ትናገራለች። በተለይም በቡድን የሚመጡ ጓደኛሞች በጋራ እስከ አራት ኪሎ ጥሬ ሥጋ በአንድ ማዕድ መመገብ እንደተለመደ ታስረዳለች። በአዲስ…

ከአውሮፕላን አደጋው ባሻገር

መጋቢት 1/2011 ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ በመነሳት 149 መንገደኞችንና 8 የአየር መንገዱን ሠራተኞች አሳፍሮ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ የነበረው ቦይንግ 737-ማክስ 8 አውሮፕላን ከተነሳ ከስድስት ደቂቃ በኋላ መከስከሱ ይታወሳል። የአውሮፕላኑን አብራሪ፣ ረዳቱና ሌሎች ሠረተኞችን እንዲሁም ተጓዦችን…

˝በሰብኣዊነት መቆመሩ እስከመቼ?

የአገሪቱ መመሰቃቀል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ፣ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት የወሰዳቸው የፖለቲካ ማሻሻያ እርምጃዎች በብዙኀኑ ዘንድ በአዎንታ መወሰዳቸው የሚታወቅ ነው። ይሁንና በዚያው ልክ ከአንድ ዓመት የማይሻገር ዕድሜ ያስቆጠረውን እና አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች አሁንም…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሪር ቀናት

ኮሞሮስ፣ ሕንድ ውቅያኖስ በወርሃ ጥቅምት፣ ከወሩም በ13ኛው ቀን 1989 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 767-200 ER ወይም በቅፅል ስሙ ‹‹ዙሉ›› የበረራ ቁጥር ኢቲ 961 አፍንጫውን ወደ ፀሐይ መውጫ አዙሮ ነፋሻውን የጥቅምት ወር ከአደይ አበባ መአዛ ጋር እየተነፈሰ ግዳጁን ይጠብቃል።…

የፖለቲከኞቹ ውይይት ትርፍ ምን ይሆን?

በኢትዮጵያ ነገ በለስ ከቀናቸው ሥልጣን ለመጨበጥ በሚል የተደራጁት የፖለቲካ ማኅበራት ብዛት ከ100 ዘሏል። ቁጥራቸው የበረከተው እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች አካሔዳቸውን መስመር ለማስያዝና የጋራ ግንዛቤ ለመጨበጥ መምከር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ባሳለፍነው ሐሙስ፣ ብሐራዊ መግባባትና ዕርቀ ሰላም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅድመ ጉባኤ ኹለተኛው የምክክር መድረክ…

መንግሥት የሕዝብን ድጋፍ እያጣ ነው ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለፁ

መንግሥት ከወራት በፊት የነበረውን የሕዝብ ድጋፍ እያጣ ነው ሲሉ፣ የአገር ውስጥና በውጪ አገር የሚገኙ የፖለቲካ ማኅበራት የመሰረቱት ብሔራዊ መግባባትና ዕርቀ ሠላም ዓለም ዐቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ። በሕዝብ ሁለንተናዊ ትግል ከኢሕአዴግ ማሕጸን የወጣው የለውጥ ኃይል፣ በጅምሩ በሕዝብ ያገኘውን ስሜታዊና ወቅታዊ ድጋፍ…

የኤርትራው ልዑክ እና የሦስቱ ከተሞች ምርጫ

ከሰሞኑ 55 አባላትን የያዘው የኤርትራው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት (‘ፐብሊክ ዲፕሎማሲ’) ልዑክ የኢትዮጵያንና ኤርትራን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግና ሕዝባዊ ሥር ለማስያዝ በሚል በኢትዮጵያ አራት ከተሞች መዘዋወሩ ይታወሳል። ይፋዊ ጉብኝቱንና ባሕላዊ ትርዒት ማቅረቡን የካቲት 8/2011 ከባሕር ዳር የጀመረው ልዑኩ በአዳማና ሐዋሳ…

የሕወሓት 44ኛ የምስረታ ዓመት ጉራማይሌ አከባበር

‹‹ሕገ መንግሥቱ እየተጣሰ ትዕግሥት የሚባል ነገር አይሠራም›› -ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ‹‹የሕውሓት አመራሮች ከትግሉ ዓላማና ግብ ውጭ በመራመድ አገሪቱን ለችግር ዳርገዋታል›› -አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) 44ኛ ዓመት የምስረታ በዓል፣ የካቲት 11/ 2011 በመቀሌ የሰማዕታት ሀውልት…

‘ቤት የራባቸው’ የአዲስ አበባ ቦታዎች

በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 9 ለሪል እስቴት ግንባታ የተሰጠና እስካሁን ቤት ሳይገነባበት ያለ 92 ሺ 721 ካሬ ሜትር ቦታ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿ ቤት አልባ የሆኑባት አዲስ አበባ “ጣሪያ የነካውን የቤት ፍላጎት ያቃልሉልኛል” በሚል የቤት አልሚ ኩባንያዎች (‘ሪል ኢስቴት’) ልማትን ከተዋወቀች ዐሥርት…

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለኛ ቅንጦት ወይስ የሀብት ብክነት?

የአዳማ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲዎች በከፍተኛ ወጪ የተቋቋሙ ነገር ግን የታለመላቸውን ግብ ያልመቱ ተቋማት ናቸው እየተባሉ ይታማሉ። ይህንን ከግንዛቤ ያስገቡት አንድነት በለጠ ዩንቨርስቲዎቹ የሀብት ብክነት ናቸው፣ በቅድሚያ በየዩኒቨርሲቲው ያሉትን የቴክኖሎጂ ዲፓርትመንቶች ማጠናከር ያስፈልጋል ይላሉ።   መንግሥት ለተፈጥሮ ሳይንስ…

የኮሚሽኖቹ አባላት ሹመት

‹‹በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለው ቂም ካልፀዳ ጠንካራ ፖለቲካ መገንባት አይቻልም›› ይህ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን እንዲሁም የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ማክሰኞ፣ ጥር 28/2011 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከጸደቀ በኋላ ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበራቸው አጭር ቆይታ…

የትግራይ መንግሥት ምላሽ ሕጋዊ አንድምታ

የማንነት እና አስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን መቋቋም ዛሬም በፌደራሉ መንግሥትና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መካከል አንዱ ላለመሥማማት መንሥኤ እንደሆነ ነው። ቀድሞውኑም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል ተወካዮች ሙሉ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረውና በአብላጫ ድምፅ የፀደቀው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ሕገ መንግሥታዊ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የምክር ቤት ውሎ “ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሠርቶ ያልታሰረ የለም”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አርብ፣ ጥር 24 በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በንግግራቸው ለመዳሰስ የሞከሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚዲያ አካላትም ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ዴሞክራሲ፣ ፖለቲካና ሰብኣዊ መብት የዲሞክራሲ ስርዓት…

ሥሙ የከበደው የአፍሪካ ኅብረት

አዲስ አበባ አውጥታ ልትተፋቸው የማትችላቸውን የጎዳና አዳሪዎች መንገድ ላይ እንዳይታዩባት ከምትሸሽግባቸው ጊዜያት አንዱ የአፍሪክ ኅብረት የመሪዎቸ ጉባኤ ነው። ይህ ተግባሯ በነዋሪው ዘንድ ብዙ ትችት ቢያሰነዝርባትም የአዲስ አበባ አስተዳደር ግን ‹‹ገጽታዬ ይበላሽብኛል›› በሚል የኅብረቱ አባል አገራት መሪዎቸ ከቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን…

የኹለቱ ርዕሰ መስተዳድሮች መግለጫ፤ “በሕዝብ መሳለቅ?“

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራና ትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ሰላማዊ ፉክክር የሚስተናገድበትን እግር ኳስ ሳይቀር እስከ መረበሽ መድረሱ ይታወሳል። በአማራ ክልል ያለ የእግር ኳስ ቡድን ወደ ትግራይ አቅንቶ ለመጫወት እንዲሁም በተቃራኒው የትግራዩ ወደ አማራ ለመምጣት እስከ መፍራት ተደርሶ መደበኛ መርሐ…

አዲሱ የምጣኔ ሀብት መርሃ ግብር ምን ያመጣ ይሆን?

በኬሚካል ማስመጣት ንግድ ላይ የተሰማራዉ ፍሬዘር አበበ በአስመጪነት ዘርፍ ከተሰማራበት ጊዜ አንስቶ ያለምንም እንቅፋት ሥራ የሠራበት ጊዜ አልነበረም። ከተጓተቱ የአሠራር ሒደቶች አንስቶ እስከ የጉምሩክ የአሠራር መርዘም ድረስ ትልቅ እንቅፋት እንደሆነበት ይገልፃል። ይህም፤ ለተጨማሪ ወጪ እንደዳረገዉና አንዳንዴም ኪሳራ ላይ እንደሚወድቅ ይናገራል።…

This site is protected by wp-copyrightpro.com