መዝገብ

Category: ሲቄ

ስለማን ትሠራላችሁ?

የሴቶችና የሕጻናት ጉዳይ ሲነሳ በተለይም የሴቶች መብት ጉዳይ ረዕስ በሚሆንበት መድረክ ብዙዎች ሲናገሩ እንሰማለን። አንዳንዴ ደግሞ ብዙ ሴቶች ተደፈሩ፣ ተጠለፉ፣ ያለእድሜ ተዳሩ፣ ተገደሉ ሲባል የሚጮኽና አለን የሚለው ይበዛል። ከተጎዱ ሴቶች ይልቅም የ‹ተቆርቋሪ ነን› ባዩን እንባ አብዝተን እናያለን። ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች…

ጉዞ ወደ ድል!

ድህነትን በተከፋችና ባዘነች እናት፣ በተጎሳቆለ አባት እንዲሁም በታረዘ ሕጻን መስለው ያስቀምጡታል። ከዚህ ቀደም በሲቄ አምድ እንዳነሳነው ሁሉ እናት በአገር ትመሰላለችና የአገርን ሐዘን በእናት ውስጥ እናያለን። አባት የቤቱ ምሰሶ ይባላልና ዋስትና ማጣትም በአባት መከፋት ውስጥ ይነበባል። ልጅ ወራሽና ተቀባይ ነውና በመታረዙ…

ሴት እና አገር

በኢትዮጵያ ለእናት የተለየ ፍቅር አለ። በየአገሩም እያንዳንዱ ማኅበረሰብ በተለየ የሚያከብረውና ቅድሚያ የሚሰጠው አገልግሎት እንዳለው ሁሉ ነው፣ በኢትዮጵያም እናትነት ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የሆነው። በተጓዳኝ በአንዳንድ አገራት ለአባትነት፣ በአንዳንዶቹ ለእህትነት ወይም ለወንድምነት ትልቅ ስፍራ ይሰጣል። ይህ የሚታወቀው እንዴት ነው? የተለያዩ ማሳያዎች ይኖራሉ።…

ያልተመዘገበውስ?

ባለፉት ቀናት በድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች ሰላም ማጣቶች ተስተውለዋል። በዚህም ምክንያት መገመት እንደሚቻለው ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል በመንግሥት በኩል ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል አንዱ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ነው። ታድያ ኢንተርኔት ቢኖር ኖሮ፣ ሰሞኑን በሴቶች ጉዳይ ላይ መነጋሪያ ይሆን…

ደኅንነት ለሁሉም!

ከሰሞኑ በሚያሳዝን ሁኔታ በክፉ ሰዎች ድርጊት ሕይወቱን የተነጠቀው ሀጫሉ ሁንዴሳ በከፍተኛ ሁኔታ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በተለይም የግድያው ሁኔታና ከዛም አልፎ የቀብር ስነስርዓቱን በማስተጓጎል በኩል የታዩ ድርጊቶች የብዙዎችን ልብ የሰበሩ ናቸው። በእነዚህ ተከታታይ ድርጊቶችም የሌሎችም በርካታ ሰዎች ክቡር ሕይወት አልፏል። ይህም…

ምልሰት – ወደ አባቶች ቀን

ብዙዎች ‹ፍቅር የለም!› ብለው እንደሚያስቡ እንገምታለን። ይህ ነገር ጥናት የተደረገበት አይመስለኝም። ግን በዙሪያችን ደምቀው የምናያቸውና ጎልተው የምንሰማቸው ጉዳዮች የፍቅርን አለመኖር ሲነግሩን በጥቅሉ እንደሌለ እንዲሰማን ይሆናል። በሚያሳዝን ሁኔታ ደግሞ ፍቅር የሚገኝባቸው ስፍራዎች፣ ኅብረቶችና ልቦች አሙቁልኝ ስለማይወዱ ድምጻቸው አይሰማም። ይህም ተደምሮ ፍቅር…

የሩቁ አጥር

በብዙ ስርዓቶች ውስጥ አጥሮች የሚታጠሩት በሩቅ ነው። ይህም የሰው ልጅ ለስርዓት ተገዢ እንዲሆንና ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚያሳየው የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ውስጥ ግዴታውን ተወጥቶ መብቱንም አስከብሮና የማንንም መብት ሳይነካ እንዲኖር ለማስቻል ነው። በሃይማኖት ስርዓት ይህ በስፋት ተጠቅሶ የሚገኝ ሐሳብ ነው። በቅርብ…

ዝም ለማይሉ!

የኪነጥበብ ባለሞያዎች ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ትልቅ ድርሻ ሊጫወቱ ይችላል። ምንም እንኳ በበቂ ሁኔታ ባይሆንም፣ በአገራችን የተለያየ ጊዜ ይህን ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ታዝበናል። በተፈለገ ጊዜ ጥበባዊ ሥራቸውን ከማቅረብ ተቆጥበውና ሰስተው ባያውቁም፣ ከዛም በላይ እውቅናቸው፣ ዝና እና ተጽእኖ የመፍጠር አቅማቸው የበለጠ ለውጥ…

መች…መች…መች?

ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች፣ በዜግነት አሜሪካዊ ሆነውም በአሜሪካ በሚደርስባቸው መከራ የተሰማቸውን ምሬት ለመረዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው። ሰልችተዋል፣ ተማርረዋል። ነጻነት ማጣት፣ ተወልደው ባደጉበት አገር ላይ በፍርሃት መንቀሳቀስ፣ ከነጭ አሜሪካውያን በተለየ በየድርጊታቸው ተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መገደድ…ብዙ ብዙ ነገር አሰልችቷቸዋል።…

የየዘመኑ ሴት!

ተፈጥሮ በሰው ልጅ ላይ እጇን ካነሳችባቸው ጊዜያት አንጻር የሰው ልጅ እርስ በእርሱ የተጋጨበት ጊዜ የሚበዛ ይመስለኛል። ለሥልጣን የሚደረግ ወንድም በወንድሙ የሚነሳበት ትግል፣ አንዱ መንግሥት በሌላው ላይ ለመሠልጠን የሚያደርገው ፍልሚያ፣ አንዱ አገር ከሌላው አገር ለአንዳች ጥቅም ሲል የሚያደርገው ወረራ እና አንዱ…

ያለ እድሜ ጋብቻ = አስገድዶ መድፈር

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ እስከ አሁን በመንግሥት በጎ ሥራዎች ታይተዋል። ወረርሽኙ በጤና ላይ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ሕይወት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመረዳት፣ የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎችንም ወስዷል። ይህ መልካም ሆኖ ሳለ አካሄዶቹ በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖሩ ሴቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ…

ደም ይፈለጋል! ያስፈልጋል!

የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በየዘርፉ ቀላል የማይባሉ በርካታ ቀውሶችን አስከትሏል። ይህም ያደጉ አገራት ወይም ደሃ አገራት ብሎ ሳያደላ፣ ሳይለይ ሁሉንም በእኩል ነው ያጠቃው። ታድያ በየዘርፉ ጽኑ መሠረት ላይ እንገኛለን ያሉ አገራት እንዲህ ከተናወጡ፣ የእኛዋ አፍሪካ እንደምን ትሆን? እንደሚታወሰው ቫይረሱ…

‹ሙያን መማር…ጾም ላለማደር›

በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቀላል የማይባሉ ሰዎች በየቤታቸው እንዲቀመጡ ተገደዋል። ቫይረሱም ስርጭቱና የያዛቸው ሰዎች ቁጥር ከእለት እለት እየጨመሩ መሆኑ ሰዎች ያለማንም ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ በራቸውን እንዲዘጉና ችግሩ እስኪያልፍ እንዲቆዩ ግድ ብሏቸዋል። ታድያ ቤት ሆነን ምን እየሠራን ነው? አንዳንዶች ለንባብ…

ልጅን ለብቻ ማሳደግ በዘመነ ኮሮና

ይህን ዘገባ ኒዮርክ ታይምስ አስነበበው። ስለ 35 ዓመቷ ሾሻና ቼርሶን እና የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስላደረሰባት ጫና ነው። ሾሻና ባለቤቷ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2019 መጀመሪያ አካባቢ ሕይወቱ አልፏል። ያኔ ልጇ ገና አንድ ዓመቷን መያዟ ነበር። ኑሮ ቀላል አልሆነላትም። ይሁንና ዓመት…

ሕግ እና ዱላ

የሰው ልጅ በልቦና ሕግ ከመመራት ጀምሮ የተጻፈ ሕግ በማሰናዳት እርስ በእርስ ተስማምቶ፣ ተፈጥሮ ያደለችውንም ሀብት በጋራ የሚጠቀምበትን ስርዓት ሠርቷል። ሕግንም ጽፎ ለተግባራዊነቱና ለጥበቃው የተለያዩ አካላትን አኑሯል። እነዚህ አካላትም ሰው ለተጻፈ ሕግ በልቦናው ላይገዛ ይችላል ብለው፣ ሕጉን ለማስከበር ዱላን ሳይቀር ይጠቀማሉ።…

በዓልና ቤተሰብ

የቻለ ቤቱ ሆኖ፣ ያልሆነለትና የሥራ ሁኔታ የማይፈቅድለት ሩጫውን እንደቀጠለ ፋሲካ በዓል ደርሷል። ቀድሞ የነበረው የቤት ውስጥ ጉድጉድ እንደወትሮው ላይኖር ይችላል። ለምን ቢሉ፣ እንደ ቀድሞው ሰው ዘመዱ ቤት እንዳይሄድ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከልክሏል። በትክክል ለቤተሰቡ፣ በእድሜ ለገፉ ወላጆችና ዘመዶቹ የሚያስብና የሚወዳቸው…

ስለ ቤት ውስጥ ሰላም!

የኮቪድ19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም አንድ አንድ ያለ የተጠቂዎቹን ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ሁኔታውን ሳይከፋ መቆጣጠር ካልተቻለ ነገሮች ምን ያህል አስፈሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ ከወዲሁ አስጨናቂ ሆኗል። አውሮፓ እና አሜሪካ ቫይረሱን እያስተናገዱ ባሉበት መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ ማስተናገድ የሚታሰብ አይሆንም። ይህ ጭንቀትና…

የቤት ሠራተኞችን በማሰብ…

የቤት እመቤት የማይከፈላት የቤት ውስጥ ሠራተኛ ስትሆን፣ ተከፍሏቸው በየሰው ቤት የሚሠሩትም የቤት ሠራተኛ ይባላሉ። መሥሪያ ቤት ተቀጥረው የሚሠሩትም በተመሳሳይ የድርጅት ሠራተኛ ናቸው። ቃሉ ለምን እንደ ‹ነውር› እንደሚቆጠር ባላውቅም፣ የቤት ሠራተኛ ሲባል ሰው ድንግጥ ይላል። ሥራ ሁሉ ሥራ መሆኑን ለሚያውቅና ሥራን…

ጥንቃቄን መታጠቅ!!

ሰዎች አንድ መሆናቸውንና የዘር፣ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የቀለምና የማንነት ወዘተ ልዩነቶች፣ ልዩነት ብቻ እንጂ የሚያበላልጣቸው እንዳይደለ የሚረዱበት አጋጣሚ ጥቂት ነው። አንድ ሆኖ ለመቆም ከሰላሙ ጊዜ ይልቅ የመከራውን ዘመን መርጠዋል፤ መርጠናል። እናም አሁን ይኸው ኮቪድ19 የተባለ የኮሮና ቫይረስ፣ ለዐይን ፈጽሞ የማይታይ ደቃቅ…

የተግባር ሙግት ጉራ ብቻ! ወሬ ብቻ!

ሙግትና ክርክር፣ ሰዎችን በሐሳብ ለመርታትና በጎ የሚሉትን ሐሳብ ለማስረጽ መሞከር ተገቢ ድርጊት ነው። በሠለጠነ ዓለምም መነጋገርና መደማመጥ አንዱ መፍትሔ ማምጫ መንገድ ሆኖ ያገለግላል። በአንጻሩ ደግሞ ንግግርና ወሬ ላይ ብቻ ችክ ማለትም ደስ አይልም። ‹አቀብሉኝ! አቀብሉኝ!› ከማለት ተነስቶ መውሰድ የሚባል አማራጭ…

እንኳን ደኅና መጡ!

በአቅምና በበጀት አቅሙ ካላቸው ግን መሪ ከማይወጣላቸውና ካልታደሉ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መካከል የሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር አንዱ ነው ብዬ አምናለሁ። ተቋሙ የተሾሙለት ሚኒስትሮች ይሄ ነው የሚባል ሥራ ሲሠሩበት አይታይም። አልፎም የፖለቲካ ማጫወቻ አድርገውት፣ ‹እገሊት ሥልጣን እስኪገኝላት የት ትቆይ?› ለሚለው ጥያቄ…

የመስዋዕትነት ቅብብል

ሰው እገሌ ቢወልድ እገሌን፣ እገሌ ቢወልድ እገሌን እያለ የዘር ሐረጉን ይቆጥራል። የሴት የዘር ሐርግ ወደኋላ እየተመዘዘ ቢቆጠርና ይህም በሕይወት ውጣ ውረድ መልክ ቢጻፍ ምን ይመስል ይሆን? ከአንድ የሥራ ባልደረባዬ ጋር ይህን ጉዳይ ስናነሳ፣ በመስዋዕትነት የደመቀ ነው ስትል ገለጸችው። እያንዳንዷ ሴት…

ስለ ‹ራስነት› ከተነሳ…

ሐሳብ በመለዋወጥ ውስጥ አንዳንዴ የተሻለ ሐሳብ ሌላ ጊዜ ደግሞ የተለየ ሐሳብ ይገኛል። ቀጣዩን ሐሳብ በአንድ ቤተሰብን ባሰባሰበ ክዋኔ ላይ ከወዳጆቼ ጋር በተገናኘንበት ያገኘሁት ነው። ላካፍላችሁ ወደድኩ፤ በአገራችን ታሪክ ሥልጣንን መያዝ ከኃላፊነት ይልቅ የራስን ክብር ማግኛ ሹመት ሆኖ ይቆጠራል። አገር የሚመራ…

መታጠፊያው መንገድ

የ2012 አገራዊ ምርጫ ቀኑ ተወስኗል። ከወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ እንዲሁም ምርጫው ይደረግበታል ከተባለው ሰሞን የአየር ጸባይ ጋር በተገናኘ፣ የፖለቲካ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ ነበር። ሆነም ቀረ፣ ያም ሆነ ይህ ምርጫው መካሄዱ እንደማይቀር ቁርጥ ሆኗል። ይህም እንደ አገር ለኢትዮጵያ፣ እንደ ዜጋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ…

ከየት እንጀምር?

ባለፈው ሳምንት የወለደች እህታችንን ለመጠየቅ ወደ የካቲት ሆስፒታል አቅንተን ነበር። በዛን ቀን የተወለዱትን ያህል ልጆች በየአንዳንዱ ሆስፒታልና በየአንዳንዱ ቀን የሚወለዱ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር ከታሰበው ጊዜ ፈጥኖ ራሱን እጥፍ ሊያደርግ እንደሚችል ጠረጠርኩ። ጥርጣሬዬ ወደ ጎን ይቀመጥና፣ ትዝብቴን ላኑር። ኢትዮጵያ አሁን…

አይበቃም?

ከሰሞኑ በሴቶች ላይ የደረሱ ጥቃቶች ብሶባቸው ታይተዋል። በተለይም በቤት ውስጥ ጥቃት ‹ባል ሚስቱን ገደለ› የሚል ዘግናኝ ዜና ሰምተናል። ከማውገዝ፣ ደጋግሞ ከመናገርና ከማሳሰብ ውጪ ምን ይደረግ ይሆን? እንደተለመደው ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንጩኽ ይሆን? ስድብ ይሻላል? እህቶቻችን እንደ ቅጠል ሲረግፉ እየተከተልን በሰልፍ…

ይልመድባችሁ!

ከአንድ/ኹለት ወር በፊት ጀምሮ ታገቱ የተባሉ ሴት ተማሪዎች ነገር ብዙዎቻችንን እንዳሳሰብን ግልጽ ነው። በሐሳባችን ላይ የቤተሰቦቻቸው ሐዘን እና እንባ ተጨምሮ እንደ ሰው ከሚያስበው ውጪ ፖለቲከኞችም ለየገዛ ፍላጎታቸው ግብዓትና መሣሪያ እንዳደረጉትም ይታያል። ግን እንደው ይሄ የፖለቲካ ሆነ እንጂ! የሴቶች መታገት አዲስ…

ደኅንነት ይሰማሻል?

የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት። እህቴ ስለሆነችና በቅርበት ስለማውቃት፣ ከተማሪነቷ ላይ ጎበዝ፣ በራስ መተማመን ያላትና ደፋር መሆኗን አውቃለሁ። ገና ተማሪ ስለሆነችና ዋናውን የሕይወት ሩጫ ባለመጀመሯ፣ አላት ብዬ የማምነው ጥንካሬ እንዳላት የምታውቅ አይመስለኝም። በቀደም ግን ከማይባት ጥንካሬ ውስጥ ሌላ ዓለም…

የወጥ ቤት ችሎታ!

እንዲህ ሆነ፤ እድሜያቸው ሰማንያውን እየጨረሰ እንደሆነ አኳኋናቸው የሚያሳብቅ፤ ቁመታቸው አጠር ያለ፤ እንደው እንዲህ ነው ብለው የማይገልጹት ግን አለ ቢባል ሁሉም ሊስማማበት የሚችል ደርባባነት የሚታይባቸው እናት ናቸው። በለጋ እድሜ የትዳር አጋራቸው በሞት ከተለይዋቸው በኋላ ብዙውን የሕይወት ፈተና ለብቻቸው ተጋፍጠው ልጆቻቸውን ከቁምነገር…

በመጻሕፍቱ ቃል አትታበይ!

ከቅርብ የሥራ ባልደረቦች ጋር ከሚነሱ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሴቶች ጉዳይ እንዲሁም ‹ፌሚኒዝም› ነው። በቀደም ታድያ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተጠቅሶ ክርክር ወይም ምልልስ ተጀመረ። እናት አባትን ማክበርን ከሚጠቅሰው የቅዱስ መጽሐፍም ሆነ የቁርዓን ክፍል ይልቅ ብዙዎች መርጠው የሚያውቁት ‹ሴት ለወንድ ትገዛ› ዓይነት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com