መዝገብ

Category: ርዕስ አንቀፅ

በታሪክ ውስጥ ብቻ አንኑር፤ ከታሪክ እንማር፤ ታሪክ እንሥራ!

ታሪክ የትላንቱን ከዛሬ ለማነጻጸሪያነት፣ ለነገም መንደርደሪያ ሆኖ ወደ ፊት የታሻለ እንድንሠራና እንድናይ የሚያደርግ የኋላ ማስታወሻ ትዝታ ነው ማለት ይቻላል። የአንድ አገር ታሪክ አገሪቱ እና ሕዝቦቿ ያለፉበትን መንገድ፣ ውጣውረድ፣ መጥፎ እና ጥሩ አጋጣሚዎችን ወደ ኋላ ሔዶ የሚያስታውስ ነው። የኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት…

ሰብኣዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ!

ኢትዮጵያ በሕገ መንግሥቷም ሆነ ውል ባሰረችባቸው ዓለም ዐቀፍ ድንጋጌ መሠረት ሰብኣዊና ዴሞክሪሲያዊ መብቶች የሚከበሩበት አገር መሆን ይገባታል። ይሁንና ይህ በኢትዮጵያ በምሉዕ እየተተገበረ እንዳልሆነ አዲስ ማለዳ ወቅታዊ አብነቶችን ነቅሳ በማሳያነት ታነሳለች። በቅርቡ በአማራ ክልል በቅማንት እና በአማራ ማኅበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት…

የአገር ሕልውና መጠበቅ፥ ሕግም መከበር አለበት

በኢትዮጵያ በፖለቲካ ፓርቲ በኅቡም ሆነ በይፋ ተደራጅቶ ይሆነኛል፤ ለአገር ይበጃል ተብሎ መታገል ከተጀመረ ከአምስት ዐሥርት ዓመታት አይዘልም። የፖለቲካ ፓርቲ መኖር በተደራጀ መልኩ የሕዝብን ንቃተ ሕሊና ለማዳበርና ለማደራጀት ጠቃሚና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ በአንድም ይሁን በሌላ…

በዳኞች ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም!

ኢትዮጵያውያን ለዳኝነት ክብር፣ በፍትሕም እምነት እንዳላቸው የታሪክ መዛግብት እንዲሁም አንዳንድ ብሂሎች ይነግሩናል። “በፍትሕ ከሔደ በሬዬ፣ ያለፍትሕ የሔደች ጭብጦዬ” ሲሉም ርቱዕ በሆነች ፍትሕ የማይቀበሉት እንደማይኖር ይናገራሉ። በዚህ መሠረት ኢትዮጵያ ዘመናዊ የሕግ ስርዓትን ከመተዋወቋ በፊት በአገር ሽማግሎች ዳኝነት ብዙ መፍትሔዎች ተሰጥተዋል፤ ዳኝነቶች…

ትምህርት ወደ ቀደመ ክብሩ ይመለስ!

ዓለማችን አሁን ለደረሰችበት ደረጃ ትልቁን ሚና የተጫወተው ትምህርት ነው። በነገሥታቱ ዓይን የተወደዱና ሞገስ ያገኙ ሰዎች ባሕር ማዶ አቅንተው እንዲማሩ የትምህርት ዕድል ያገኙ እንደነበር መዛግብት ያስረዱናል። እነዚሁ ሰዎች ትምህርታቸውን አጠናቅቀው አገራቸውንና መንግሥትን ለማገልገል ቀናዒ መሆናቸውንም እንታዘባለን። ባሕር ተሻግረው ትምህርት እንዲማሩ ዕድል…

“ዘመን ብቻውን አይለወጥ!”

በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ያለፈውን ዓመት መለስ ብሎ መቃኘት፣ ጠንካሮቹን ይዞ የደከሙበትን ለማሸነፍ አዲስ ዕቅድ ማስቀመጥ የተለመደ ነው። ይህም ለተግባራዊ እርምጃ የሚያቀርብ በመሆኑ ሊጠናከር የሚገባው ባሕል ነው። በዚህ መሠረት በአገር ዐቀፍ ደረጃ 2011 እንዴት አለፈ፤ ምን ጠንካራ ጎኖች ነበሩ፤…

የፖለቲካ ልዩነታችን ለውጪ ሃይሎች እንዳያስከነዳን

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ግብፅ ካመሩበት ሃምሌ 19/2011 በኋላ የግብፁ አቻቸው ኢትዮጵያን እና ሱዳንን በአንድ ቀን ርቀት ጎብኝተው ነበር። ሞሃመድ አብደል. ላቲ ሁለቱን አገራት የጎበኙበት ምክኒያትም ከተለመደው ውጪ አንድ አዲስ ጥናት በመያዝ በህዳሴው ግድብ ላይ…

ምርጫው መቼም ይሁን መቼ ሁሉም የቤት ስራውን አጠናቆ ይጠብቅ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከጨበጡበት የመጀመርያ ዕለት አንስቶ ባደረጓቸው ንግግሮች ስለቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫ በተደጋጋሚ የተለያዩ አስተያየቶች የሰጡ ሲሆን፣ አብዛኞቹ አስተያየቶችም የሚያጠነጥኑት ቀጣዩን ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ተዓማኒ፣ እንዲሁም አሳታፊ ለማድረግ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን የሚያወሱ ነበሩ። ቀኑ እየቀረበ ሲሄድም ጉዳዩ ከፖለቲከኞች…

የኑሮ ውድነት መልስ የሚሻ የብዙኀን ጥያቄ

በመንግሥት ግምት ሩብ ያህሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም ከድህነት ወለል በታች ነው። ይሁንና ይህ ቁጥር መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማያሳይ እና ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከድህነት ወለል በታች የድሃ ድሃ ኑሮን የሚገፋ መሆኑን የሚከራከሩ ባለሙያዎች አሉ። የመንግሥት ግምት ትክክል ነው ቢባል…

የሴት ባለሥልጣናት ትችት ሴትነታቸው ላይ ማነጣጠሩ ይቁም!

በሐምሌ መጨረሻ የፍትሕ አካላት በሚያዘጋጁት የፍትሕ ወር ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መአዛ አሸናፊ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን የመፈፀም እና የማስፈፀም ሒደትን በተመለከተ አስተያየት ሰጥተው ነበር። ፕሬዘዳንቷ የሰጡት አስተያየት በሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጡ የተለያዩ ድንጋጌዎችን የጣሰ ንግግር ነው በሚል ሲተች ቆይቷል።…

ሕግ የመጣስ ባሕል ወደ አምባገነንነት እንዳይወስድ ይታሰብበት

አዲስ ማለዳ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፤ ሐምሌ 20 ባወጣችው 38ኛ ዕትሟ “የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጋዊነት እስከ መቼ?” በሚል ርዕስ ሥር በሐተታ ዘ ማለዳ ዓምዷ፤ በአንድ ወገን በምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ የሚመራው የአዲስ አበባ አስተዳደርም ሆነ ምክር ቤቱ የሥልጣን ዘመኑ ሰኔ 30/2011…

ችግኞችን መንከባከብ፥ ዛፎችን በዘላቂነት መጠቀም ያስፈልጋል

የፊታችን ሰኞ፣ ሐምሌ 22 በመንግሥት ዋና አነሳሽነት በመላው ኢትዮጵያ ለማካሔድ የታቀደው በአንድ ጀንበር 200 ሚለዮን ችግኞችን በመትከል በዓለም ድንቅ መዝገብ መሥፈርም ሆነ በአጠቃለይ በያዝነው ክረምት ለመትከል የታሰበው 4 ቢሊዮን ችግኝ በጎ እርምጃ ብቻ ሳይሆን አገሪቱ ካጋጠማት የፖለቲካ ምስቅልቅል ብቸኛውና ሁሉንም…

ከኀይል ይልቅ ሕጋዊ አማራጭ ይቅደም

ሰሞኑን በአገር ዐቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የተለያዩ አካላት ስብሰባ ሲያካሒዱበትና መግለጫ ሲያወጡበት የከረሙት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ሥር የሚገኘው የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ጎልቶ ወጥቷል። በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 39 (3) መሰረት…

የእስረኞች ሰብኣዊ መብት ይከበር!

ሰኔ 15/2011 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተካሔደውን “መፈንቅለ መንግሥት” ተከትሎ በባሕር ዳርና በአዲስ አበባ የከፍተኛ ባለሥልጣናትና ሌሎች በውል ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎችን ክቡር ሕይወት መንጠቁ ይታወሳል። ይህንን ድርጊት ተከትሎም መንግሥት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከሰባት መቶ በላይ ሰዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን…

በሐረሪ ክልል የተንሰራፋው ስርዓት አልበኝነት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል!

አዲስ ማለዳ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምሥራቅ 525 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሐረርን በሥራ ጉዳይ ጎራ ባለችበት ወቅት አጠቃላይ ቅኝት በማድረግ ስለክልሉ ከዚህ በፊት ይሰሙ የነበሩት ጉዳዮች በቅርበት ለመታዘብ ዕድሉን አግኝታለች። በዚህ የጋዜጣችን ዕትም ላይ ሐረርን ማዕከል ያደረጉ ዘገባ፣ ትንታኔና…

መንግሥት የሕግ ልዕልናን ያክብር፤ ያስከብር! በቀውስ ጊዜ የዜጎች የመረጃ ማግኘት መብት ይከበር!

ቅዳሜ፣ ሰኔ 15/2011 በአማራ ክልል መንግሥት ላይ የተቃጣው እና በመንግሥት “መፈንቅለ መንግሥት” የተባለው ደም አፋሳሽ አጋጣሚ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር የነበሩትን አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) እና “ግድያውን መርተዋል” የተባሉትን ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌን ጨምሮ የአራት ከፍተኛ የክልሉን ባለሥልጣናት ሕይወት ቀጥፏል። ከዚሁ አሳዛኝ…

የ‘ፕራይቬታይዜሽኑ’ ድርድር ጉዳይ ‘ዐሥር ጊዜ ለካ፥ አንድ ጊዜ ቁረጥ’!

በኢትዮጵያ ውስጥ ከመጣው የፖለቲካ ለውጥ ጋር ተያይዞ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት በምጣኔ ሀብት በኩል ሊወስዳቸው ካሰባቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ይዞታነት እንዲዘዋወሩ ማድረግ ይገኝበታል። ለዚህ እርምጃ ከተለዩት የልማት ድርጅቶች መካከል…

ሕግ ይከበር፡- “ሆደ ሰፊነትም” ልክ አለው!

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ፣ ግንቦት 29/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ የሕግ አካላት ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ባለሙያዎቹ ብዙ ከሙያቸው ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ሕግ ማክበርንና የሕግ ሉዓላዊነትንም በተመለከተ መንግሥት ያሳየውን ዳተኝነት ግን አጽዕኖት ሰጥተውት ነበር። ጠቅላይ…

መሪዎች አርዓያነታቸውን ያሳዩ!

በቅርቡ በመላው የሙስሊም ማኅበረሰብ የተከበረውን ኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀደም ብለው ባቀረቡት ጥሪ መነሻነት ከክርስቲያኖች ጋር በመሆን ሕዝብ ሙስሊሙ በዐሉን በሚያከብርበትና በሚሰግድበትን አዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥና ዙሪያውን በኅብረት ጽዳት አካሒደዋል። ይሔ የጽዳት ክንውን ወትሮ…

መንግሥት ለጋዜጠኞች ደኅንነት ዋስትና ይስጥ!

ኢትዮጵያ ለጋዜጠኞች እና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መረጋገጥ በሯን ዳግም ከከፈተች ካንድ ዓመት በላይ አልሆናትም። ሆኖም ዛሬም ጋዜጠኞች እና ብዙኀን መገናኛዎች በርካታ ተግዳሮቶች እንዳሉባቸው ተደቅነውባቸዋል። ሌላው ቀርቶ በቅርቡ በጥቂት ቀናት ልዩነት ኹለት ጋዜጠኞች መዋከብ፣ ድብደባና እስር አጋጥሟቸዋል። ጋዜጠኛ ምስጋና ጌታቸው የሳምንታዊዋ…

የመንግሥት እና ሃይማኖት ግንኙነት መሠረቱን እንዳይስት!

ያለፉት መንግሥታዊ ስርዓቶች የመንግሥት እና ሃይማኖት መቀላቀል ሳያሳስባቸው ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅ ወይም ተቀባይነት ለማግኘት አንዱን ሃይማኖት፣ ወይም አንዱን የአንድ ሃይማኖት ክንፍ በመደገፍ ወይም ሌላውን በመቃወም እና በማዳከም በርካታ ስህተቶችን ሠርተዋል። ይህም ታሪካዊ ቁርሾዎች፣ ጠባሳዎች እና ቅሬታዎችን ትቶ አልፏል። እንደዚህ ዓይነቱ በመንግሥት…

በዘመቻ ዘላቂነት ያለው ሥራ መሥራት አይቻልም!

ቅዳሜ፣ ግንቦት 3/2011 የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ማፅዳት ዘመቻ በሚመስል መልኩ በተለያዩ ቡና ቤቶች ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ የጅምላ እስር መፈፀሙ ይታወሳል። በዘመቻው 600 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ተመክረው ሲለቀቁ፣ 8ቱ በምርመራ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል’ ‘አንድ ነጻ ሰው ከሚታሰር፣ ዐሥር ወንጀለኛ…

ቅድሚያ ለኢትዮጵያ ኅልውና እና ለዜጎች ደኅንነት!

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ፈታኝ ወቅት ላይ ነው የሚገኙት። በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ሠርቶ መብላት እና ነግዶ ማደር አስቸጋሪ ተግዳሮቶች ተጋርጠውባቸዋል። ከዓመት በፊት የተጀመረው የለውጥ ሒደት ሲበሰር ዜጎች የተደሰቱት ሁሉም ጥያቄዎቻቸው በአንድ ጊዜ መልስ ያገኛሉ በሚል የተሳሳተ አረዳድ ሳይሆን፥ ቢያንስ ሰላም ወጥቶ…

ብዙኀን መ ገናኛዎች የውስጥ ችግራቸውን ይቅረፉ መንግሥት የራሱን ኀላፊነት ይወጣ

ለ26ኛ ጊዜ የተከነረው የዓለም ዐቀፉ የፕሬስ ቀን “ጋዜጠኝነትና ምርጫ፡ በዘመነ የመረጃ ብክለት” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ረቡዕ፣ ሚያዚያ 23/2011 ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ለሦስት ቀናት ተከብሮ ውሏል። በርግጥ በተደጋጋሚ የፕሬስ ነፃነትን በመድፈቅ ግንባር ቀደም ከሆኑ አገራት ተርታ ትመደብ…

ዘላቂው መፍትሔ ሁሉን አካታች ነው

‘ኦሮማራ’ በሚል ቅፅል ሥም በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የኦሮሞ እና አማራ ፖለቲከኞች ትብብር በጥቅሉ መልካም ነው። ነገር ግን በርካታ ጎዶሎዎች ያሉት እና ዘላቂ መፍትሔም የማያመጣ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ብሔር ተኮር ትርክቶች ከተዋወቁ ወዲህ የበዳይ ተበዳይ፣ የጨቋኝ ተጨቋኝ…

አዲስ እና ብቁ ሰዎች ኀላፊነት ይሰጣቸው

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የአመራሮች ሹም ሽር የፖለቲካ ታማኝነት ያላቸውን ሰዎች ወደ ላይ ከማምጣት የበለጠ ፋይዳ ኖሮት አያውቅም ቢባል ማጋነን አይሆንም። በኢሕአዴግ ስርዓተ መንግሥት ደግሞ ከዚህ በባሰ አንዳንድ ሚኒስትሮች ሦስት እና አራት ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችን እየተሽከረከሩ እና እያፈራረቁ እንዲመሩ ይደረጋል። የሚኒስትርነት…

ሕዝባዊ አመፅን ለመቆጣጠር ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር

የዕድገቱ መጠን የቱንም ያህል እያወዛገበ ቢሆንም፥ ኢትዮጵያ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ የዓለማችን አገራት ተርታ ተሰልፋለች። ይሁን እንጂ ባለፉት አራት ዓመታት የነበረው የፖለቲካ ተቃውሞ እና የተከተለው ለውጥ የዕድገት ፍጥነቱን እያቀዛቀዘው ይገኛል። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ላየችው ሕዝባዊ ተቃውሞ የዳረጋት የምጣኔ…

የአደንዛዥና አነቃቂ ዕፆች ዝውውር ሳይቃጠል በቅጠል

ጥናቶች የአደገኛ ዕፅና መድኀኒቶች ተጠቃሚነት ከሰው ልጅ ዕድሜ ታሪክ እና ጋር አቻ እንደሆነ ይጠቁማሉ። በጥንት ጊዜ የሰው ልጅ የተክሎችን የተለያዩ አካላት ማለትም እንደ ሥር፣ ቅጠል፣ ግንድና ፍሬ በመጠቀም የተለያዩ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ድርጊቶች ላይ ይጠቀሙ ነበር። ሆኖም ግን ሳይንስና ቴክኖሎጂ እያደገና…

የእኩልነት እና መብቶች መከበር ጉዳይ ከውክልና ባሻገር ትኩረት ያሻዋል!

በዚህ ወር ከሚከበረው ዓለም ዐቀፉ የሴቶች ቀን መልካም ጎኖች አንዱ፥ በርካታ መረጃዎች የሚወጡበት ጊዜ በመሆኑ ኢትዮጵያ የስርዓተ ፆታን እኩልነት ለማስተካከል ምን ያህል ሥራ እንደሚቀራት ማስታወሻ መሆኑ ነው። በዚህ ዓመት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ወንድና ሴት ምጥጥን…

ለውጡ እንዳይቀለበስ፥ ድክመቶቹ ይታረሙ!

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣነ መንበሩን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለሦስት ዐሥርት ዓመታት ያህል የሕዝብ ብሶት አንዳንዴ እየጋመ፥ ሌላ ጊዜ ደግሞ እየተቀዛቀዘ እዚህ ደርሰናል። እስከ 2010 የመጀመሪያ ወራት ድረስ የሕዝብ ጥያቄዎችን ችላ በማለት ሕዝባዊ አመፆችን በፀጥታ አካላቱ ጡንቻ እየደፈቀ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com