መዝገብ

Category: ሕይወትና ጥበብ

የኦሮሞ ባሕል ማዕከልን በጨረፍታ

ክዋኔ ጠብቆ የሚከፈትን የደረጃ ፏፏቴ ከመካከል አድርጎ በኹለት ረድፍ የሚገኘው ወደ ማዕከሉ ቅጥር ገቢ የሚያስገባው ደረጃ ያለስስት የተሠራ መሆኑ ያስታውቃል። ደረጃውን ጨርሶ ገቢ ወጪውን በትኩረት ከሚያዩት ፈታሾችና ጥበቃዎች አልፎ ወደ ውስጥ ለዘለቀ፤ የማዕከሉን ሕንጻ የሙጥኝ ብለው የሚገኙ፤ በጎበዝ ቀራጺ የተሠሩ…

ቀርከሃን በጥበብ

አብሮ አደግ ናቸው፤ ፍቅርተ ገብሬ እና ወይንሸት አጨራምቶ። አሁን ላይ በጋራ ሆነው እየሠሩ ካሉት ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ ኅብረት ሽርክና ማኅበር በሚል ሥያሜ ከሚጠራው የቀርከሃ ሥራቸው በፊት የተጋሩት ሕይወት ነበር፤ ስደት። ፍቅርተ በስደት ከዐሥር ዓመት በላይ ቆይታለች። አካሔዳቸው ሕጋዊ…

“የምድራችን ጀግና” አዲሱ የዘነበ ወላ በረከት

“አስተዋይ፣ ትሁት አንዳንዴ ይሉኝታ የሚያበዛ ሰው ነው” ሲሉ ሽብሩ ተድላ (ፕሮፌሰር) ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ለተገኘው ታዳሚ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ምስክርነት ሰጡ። ፕሮፌሰሩ ይህን ምስክርነት የሰጡት ለረጅም ዓመታት ወዳጃቸውና ጓደኛቸው ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር (ዶ/ር) ነው። ስለዶክተር ተወልደ ብርሃን ይልቁንም ስለ…

አመሻሽን ተገን ያደረጉ የኪነ ጥበብ ድግሶች

የአዲስ አበባ ምሽቶች፤ የመጠጥ ቤቶች ማለዳ እንዲሁም ጭፈራ ብቻ የሚስተናገድባቸው መሆንን ከተዉ ከራርመዋል። ከፖለቲካ ይልቅ ማኅበረሰብ ላይ ለውጥ ማምጣትና ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚቻላት የሚነገርላት ጥበብ በተለያዩ ሥያሜና ክዋኔዎች ምሽቶቹን ተጋርታለች። ከቴአትርና ሲኒማ ቤቶች ውጪ፤ ወጣቶች ሰብሰብ ብለው በትልልቅ አዳራሽ በሮች ላይ…

የአዲስ አበባ “ቡና ሱቆች” ዓይነተ ብዙ – ከፍተኛ ዋጋ

አስቴር ደምሴ የቀይ ዳማ ቆዳ፣ ስታወራ ፈገግታ የማይለያት ፍልቅልቅ የ27 ዓመት ወጣት ስትሆን ለገሀር አካባቢ በሚገኝ የግል ባንክ ውስጥ በሒሳብ ባለሞያነት ተቀጥራ እየሠራች ትገኛለች። “ቡና ሳልጠጣ መዋል አልችልም” የምትለው አስቴር በቀን ቢያንስ ኹለት ጊዜ ቡና የምትጠጣ ሲሆን ምሳ ከበላች በኋላ…

የሰኔ ሰላሳ ትዝታዎች

ሰኔ ሰለሳ ተማሪው ውጤቱን በሰርተፊኬት ማረጋገጫ የሚቀበልበትና የቀጣዩን ክፍል ዕጣ ፈንታ የሚያውቅበት በመሆኑ ጎበዞቹ በጉጉት ይጠብቁታል። በትምህርታቸው ደከም የሚሉት ደግሞ በታላቅ ፍርሃትና ሥጋት ቀኑ ላይ ይደርሳሉ። ከዚህ ባሻገር ግን ሰኔ ሰላሳን ለተለየ ውሎ የሚጠቀሙበት ተማሪዎች ጥቂቶች አልነበሩም። በየክፍሉ ውጤት ተሰጥቶ…

ሕጋዊ የስፖርት አወራራጆቹ

ይርገዱ ጫኔ ኢራቅ በነበረችበት ጊዜ ለዓመታት በቱርኮች ባለቤትነት በሚመራው የስፖርት ማወራረጃ ተቋም ውስጥ በመጀመሪያ በጽዳትነት ቀጥሎ ደግሞ በገንዘብ ያዥነት አገልግላለች። ይህም የስፖርት ውርርድ ሥራ ምን እንደሚመስል ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት እንዲኖራት አስችሏታል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና ለጥቂት ዓመታት ከሠራች በኋላ እውቀትዋን…

“አውታር” ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ትንሣኤ!?

በኢትዮጵያ በርካታ የሥነ ጥበብ በተለይም ደግሞ በሙዚቃው ዘርፍ የተሰለፉ ግለሰቦች እንቅልፋቸውን ሰውተው ለሕዝብ የሚያቀርቧቸው የሙዚቃ ሥራዎች በተለያዩ ምክንያቶች መና ቀርቶባቸው አንገታቸውን የደፉበት ያለፉትን ዓመታት አሁን ተረት ለማድረግ እየተሠራ ይመስላል። በተደጋጋሚ ለቁጥር የሚያዳግቱ ኢትዮጵያዊያን የሙዚቃ ሰዎች አደባባይ በመውጣት ስለቅጂ እና ተዛማጅ…

“ፊልም በፍላሽ”

እዮብ ሀብታሙ በኻያዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት ነው። ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት እሱን ጨምሮ ከሌሎች ኹለት ወንድሞቹ ጋር ነበር የውጭ አገር ፊልሞችን ለተጠቃሚ በኹለተኛ ደረጃ ማጠራቀሚያ መሣሪያ (secondary storage device) ፍላሽ ዲስክ፣ ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ ላይ በመጫን መሸጥ የጀመሩት።…

‘ሲትኮም’ ከማሳቅ ባሻገር

አጭርና ራሰ በራ የሆነው ቶኪቻው ከጭቃ በተሠራች ደሳሳ ጎጆ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሏል። ጠላ እየጠጣ የሚገኘው ቶኪቻው ክፍለ ሀገር አብሯቸው የሔደው ጓደኞቹ ሲመለሱ ጥለውት ስለመጡ ይቅርታ ቢጠይቁትም, ይቅርታ ሊያደርግላቸው አልፈለገም። ጓደኞቹም ተስፋ ባለመቁረጥ የይቅርታ ጥያቄያቸውን ደጋግመው በማቅረባቸው የተናደደው ቶኪቻው, የለበሰው…

እዳ’ዬ የሺዎች እናት

የበጎነት እና የመልካም እናትነት ተምሳሌት የሆኑት የ84 ዓመቷ ዕድሜ ባለፀጋ አበበች ጎበና ዛሬ አቅማቸው የደከመ፣ ጤናቸውም የጎደለ ይመስላል። ሺዎችን በፍቅር ያሳደገው ልባቸው ታውኳል፣ ዘመናትን ወደ ኋላ ተጉዘው የተደረጉ ጥቃቅን ነገሮችን እንኳን የማይስቱት ደጓ እናት አበበች፥ ከዕድሜያቸው ጋር ተያይዞ የመዘንጋት ችግር…

ረመዳን ታላቁ የፆም ወር

በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ በከፍተኛ ናፍቆት የሚጠበቀው የታላቁ ረመዳን ፆም ሰኞ፣ ሚያዚያ 28 መጀመሩ ይታወቃል። ረመዳን በየዓመቱ በዚህ ወቅት የሚካሔድበትም ዋነኛው ምክንያት ቅዱስ መፅሐፍ ወይም ቁራን ለነብዩ መሐመድ የተገለጠበት ወቅት ስለሆነ እንደሆነ የእምነቱ ምሁራን ይናገራሉ። ነገር ግን ከዓመት ዓመት የተወሰነ የቀናት…

የሴቶች ሰቆቃ በማረሚያ ቤቶች

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የሴት ታራሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያሳያሉ። በመላው አገሪቱ ከሚገኙት 200 ሺሕ ታራሚዎች ውስጥም 3 ነጥብ 7 በመቶ ሴቶች ሲሆኑ አብዛኞቹ በትዳር አጋሮቻቸው፣ በፍቅር ጓደኞቻቸው፣ ወይም በጥቃት አድራሾቻው ላይ ራስን በመከላከል ወቅት ጉዳት ያደረሱ ናቸው። የኢትዮጵያ…

የሹሩባ ትንሳኤ

ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ከሰማንያ በላይ ቋንቋዎች እና በርካታ ባሕላዊ አልባሳቶች በተጨማሪ ለየት ያለ የጸጉር አሰራር ባለቤት በመሆን ትታወቃለች። እንደ ጉዱላ፣ ዘራንቺ፣ ጉቴና፣ ናዝራው እና ሹሩባ የመሳሰሉት የጸጉር አሰራሮች በተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ሰዎችን ሀይማኖት፣ ዕድሜ፣ የጋብቻ ሁኔታንና መሰል…

በገናን ለመታደግ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ባሕላዊና መንፈሳዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች መካከል በገና አንዱ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ትልቅ ቦታ ያለው መሆኑም ይታወቃል። በተለይ እንደዚህ እንደአሁን የፆም ወቅት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በገና ዝማሬዎች መስማት በጣም የተለመደ ነው። ከክርስቶስ ልደት በፊት በገናና…

‘ነብይ ዤሮ’

ዕለቱ እሁድ፣ ቦታው ባለግርማ ሞገሱ የአዲስ  አበባ ቴአትርና ባሀል አዳራሽ፣ ሰዓቱ ስምንት ተኩል፤ ቴአትር በተጠማ ተመልካች አዳራሹ ጢም ብሎ ሞልቷል። መብራቶች ጠፍተው ለአፍታ አዳራሹ ጨልሟል፤ ወዲያውም የመድረኩ መጋረጃ ተከፈተ። መቼቱን የባሕር ዳርቻ አድርጎ የሚጀምረው ተውኔት ዋናው ገጸ ባህሪይ ደማቅ አረንጓዴ…

“እንዲህ አይደሉ እንዴ?”

የልብ_ወለድ ድርሰቶች፣ ፊልሞች፣ ቴአትሮችና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ሥራዎች ሴቶችን ንዑስ ስብእና እና አፍቃሪ ንዋይ አስመሥለው የመሣላቸው እውነታ የአደባባይ ምስጢር ነው። ብዙውን ጊዜ እነዚህ የፈጠራ ገጸ ባሕርያት የምናውቃቸውን ሴቶች አይወክሉም የሚሉት ተዋናይት እና ጸሐፌ ተውኔት አዜብ ወርቁ፥ ገጸ ባሕርያቱ የሚያሳዩን በኪነ…

ድሬና የጎዳና ላይ ምግቦቿ

ሻሺ መርሻ ከአዲስ አበባ 450 ኪሎ ሜትር ርቃ ባለችው ድሬዳዋ መኖር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ገቢዋ አንስተኛ በመሆኑ ሕይወቷን መምራት ቀላል ሆኖላት አያቅም። በተለይም የከተማዋ ዕድገትን ተከትሎ የኑሮ ውድነቱ በመክፋቱ ሕይወቷን በአግባቡ ለመምራት ተቸግራለች ነበር። ነገር ግን፤ ከዛሬ ሦስት ዓመት አንስቶ…

ሚፍታህን እንደማሳያ የአዲስ አበባን የጎዳና ላይ ንግድ

ዕለቱ ሰኞ፣ መጋቢት 9 አስራ አንድ ሰዓት፥ ቦታው በተለምዶ ʻቦሌ ድልድይʼ ወይም ብራስ በመባል የሚታወቀው አካባቢ ነው። ሰርክ እሁድን ብቻ ሳይጨምር ቦታው ጠዋትና ከሰዓት በኋለ በተለይ ከ10 ሰዓት ጀምሮ ከሥራ በሚወጡ ሰዎች፣ በተማሪዎችና በተላላፊ መንገደኞች ይጨናነቃል። የጎዳና ላይ ʻነጋዴዎችምʼ ለመንገዱ…

የፊት ቆዳ ውበት አጠባበቅ

ጥቂት ነጥቦች ሰዎች ጊዜው ያለፈበትን የውበት መጠበቂያ ሲጠቀሙ ፊታቸው ወዲያው ይቆጣል። ለዚህም ውሃ ጨው ጨምሮ በማፍላት ፎጣን በመጠቀም ወደ በፊቱ ቆዳቸው እንዲመለስ ይረዳል። ቆዳችን በተፈጥሮው በየ28ኛው ቀን ስለሚቀያየር አላስፈላጊ ቆዳዎችን በማስወገድና ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ለቀጣዩ የውበት አጠባበቅ ዝግጁ ማድረግ ይቻላል።…

የዓለማየሁ ታደሰ የጥበብ ጉዞ በጨረፍታ

ʻባቢሎን በሳሎንʼ በኢትዮጵያ የቴአትር ኢንዱስትሪ ታሪክ ውጤታማና መድረክ ላይ ብዙ ከቆዩት መካከል ይመደባል። በርግጥ ቴአትር ተመልካች ሆኖ ባቢሎን በሳሎንን ያልተመለከተ ማግኘት ከባድ ነው። የቴአትሩ ሥም በተነሳ ቁጥር አንድ የማይረሳ ተዋናይ ቢኖር ዓለማየሁ ታደሰ ነው። ሐረር ተወልዶ ያደገው ዓለማየሁ ታደሰ ወደ…

ክብረ ዓደዋ የካቲት ፳፫ – ፲፰፻፹፰

በቅኝ ግዛት ዘመን ‹‹አፍሪካን መቀራመት›› የሚል አጀንዳን ያነገቡ የአውሮፓ ኃያላን አገራት ባህር አቋርጠው ፣ ጦራቸውን ሰብቀው ፣ ህያዋንን እየፈጁ አፍሪካ ላይ ከተሙ። ይሁን እንጂ ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ የአናብስት ምድር ዓይኑን የጣለው የዱቼ ሞሶሎኒ ጦር ግን እንዳሰበው የልቡን ሊሞላ አልቻለም። ኋላቀርነታቸው…

በማደግ ላይ የሚገኘው የሕንፃ ውስጥ ማስዋብ

ከክርስቶስ ልደት በፊት በግብፅ ሥልጣኔ ዘመን መኖሪያን በጨርቃ ጨርቅ እና በእንስሳት ቆዳዎች በማሸብረቅ የጀመረው ሕንፃን የማስዋብ ጥበብ ከዘመን ጋር እየዘመነ አሁን ላይ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕንፃን የማስዋብ ጥበብ በሁሉም ቦታ ለአንድ ዓይነት አላማ ይዋል እንጂ ከቦታ ቦታ የማኅበረሰቡን…

የቴዲ አፍሮ የቪዲዮ ሙዚቃ ዛሬ ገበያ ላይ ዋለ

“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር” በሚል ርዕስ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (‘ቴዲ አፍሮ’) ከአቦጊዳ ባንድ ጋር በጥምረት በአዲስ አበባ ሚሊንየም አዳራሽ ጥቅምት 24 ተዘጋጅቶ የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ምስል ቅንብር ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 16 በገበያ ላይ ዋለ። ይህንን ሥራ እውን ለማድረግ የስድስት ወራት…

“ወቶ አደር” የሚለው ፈልም ለዕይታ ቀረበ

የአንተነህ ኃይሌ ፊልም የሆነው “ወቶ አደር” የተሰኘው ፊልም ከየካቲት 8 እስከ 10 ድረስ በሁለም ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል አንድ ሰዓት ከአርባ ሁለት ደቂቃ የሚረዝመው ይህ ፊልም ወቅታዊ እና ሀገራዊ ሀሳቦችን በቀልድ እያዋዛ የሚነግረን ፊልም ሲሆን ፊልሙን አጠናቆ ለመጨረሰ 3 ወር ግዜ…

‘እርጥብ’

እርጥብ በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየተለመደ የመጣ የምግብ ዓይነት ሲሆን በብዛት የሚገኘው በየሰፈሩ በሚገኙ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው የምግብ አገልግሎት በሚሰጡት ሱቆች ውስጥ ነው፤ በተለምዶ ‘አርከበ ሱቅ’ በመባል በሚታወቁት ትንንሽ ምግብ ቤቶች ናቸው። ሌላው የእርጥብ መገኛ አዳዲስ ሕንፃዎች በሚገነቡበት አካባቢዎች…

ማስቆሚያ የታጣለት ያለ ዕድሜ ጋብቻና መዘዙ

ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለአትዮጵያ አዲስ ባይሆንም በቅርቡ የብዙኃን የተከሰተው ከወትሮው ለየት ያለ ነበር። የተፈፀመው ትግራይ ክልል፤ ቦታው ደግሞ ተንቤን ወረዳ ሙዜ ደበት የሚባል አካባቢ ነበር። ዕድሜው በግምት ወደ 20ዎቹ አጋማሽ የሚጠጋው ክብሮም ግደይ የተባለ ወጣት ዘንግቶት ኖሮ ይሁን ረስቶት፤ ለብዙዎች…

ሳይንስ አካዳሚ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ ሳይንሳዊ ገለፃ ሊያካሒድ ነው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፟አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአገር እድገት ያለው አስተዋፅኦ ፟ በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ ገለጻና ውይይትሐሙስ፣ ጥር 30/2011 በ11 ሰዓት በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሒዳል። ሳይንሳዊ ገለጻውን የሚሰጡት ጌታቸው አሰፍ ሲሆኑ ገለጻቻም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለዕድገታችን፟፟ በምን መልኩ እንጠቀም?…

የባሕላዊ ዳንስ ማንሰራራት እና ዕጣ ፈንታ

ባሕላዊ ዳንስ የኢትዮጵያውን የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ በሰፊው ከሚተገበር ተግባራት መካከል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይሁን እንጂ፤ ይህ ለብዙ ሺሕ ዓመታት የቆየ ልማድ ቢሆንም፤ እንደ ጥበብ ተቆጥሮ መተግበር ከጀመረ፤ አንድ ምዕተ ዓመት አልሞላውም። በርግጥ፤ ከ1920ዎቹ አንስቶ ቴአትር ቤቶች ባሕላዊ ዳንሶችን…

̋መቅደላ˝ በተሠኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት ይደረግበታል

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል 45ኛውን የጥበብ ውሎ መርሐ ግብር ዛሬ ጥር 18/2011 ከ8 ሰዓት ጀምሮ ያካሂዳል፡፡ የአጼ ቴዎድሮስን 200ኛ የልደት ዓመት ምክንያት በማድረግ የንጉሰ ነገስቱን የመጨረሻ ዘመን የዓይን እማኝ ሆኖ ታሪካቸውን የተከታተለው ሄንሪ ሞርተን…

This site is protected by wp-copyrightpro.com