መዝገብ

Category: አንደበት

የኢትዮጵያ ፖለቲካን ጠርንፎ የሔደው የትግራይ፣ አማራና ኦሮሞ ፖለቲካ ነው

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአክቲቪስትነት ስማቸው ገንኖ ከወጣና ተሳትፏቸው እንዲሁም ተጽእኖ ፈጣሪነታቸው ከጠነከረ ሰዎች መካከል ይገኛሉ፤ የኦሮሚያ ሚድያ ኔተወርክ ሥራ አስኪያጅ ጀዋር መሐመድ። ፖለቲካ ውስጥ በተወዳዳሪነት የመሳተፍ ፍላጎት ያልነበራቸው ጃዋር፤ በቅርቡ ነው ለመወዳደር ወደ መድረኩ እንደሚመጡ የሳወቁት። ከዚህና ከግል ጉዳያቸው ጋር…

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመጾች ከትላንት እስከ ዛሬ

ትውልድና እድገታቸው አዲስ አበባ ነው፤ መስፍን ማናዜ። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሒሳብ፣ ኹለተኛውን በትምህርትና እቅድ ሥራ አመራር አግኝተዋል፤ አሁን ላይ ደግሞ በትምህርት ፖሊሲ አስተዳደር እጩ የሦስተኛ ዲግሪ (ፒ ኤች ዲ) ተማሪ ናቸው። መማር ብቻ አይደለም፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ዘልቀው አስተምረዋል፣ ጥናቶች…

‘‘የጦርነቱ ተራራ እንኳን አስከፍቶኝ አያውቅም፣ ጦርነት ላይ ቁጭ ብዬም እስቅ ነበር”

የመጀመሪያ የትውልድ ሥማቸው በጂጋ ገመዳ ነበር፤ በኋላ ትምህርት ቤት ሲገቡ ምናሴ በሚል ተቀይሯል። በኋላ አባዱላ በሚል ጸንቶ ከዚሁ ሥማቸው በፊትም ጄኔራልን ጨምሮ የተለያዩ ወታደራዊ እና የሲቪል ኀላፊነቶች ተጠርተዋል፤ አገልግለውማል። በጥቅምት ወር ታትሞ ለንባብ የበቃው ‹‹ስልሳ ዓመታት›› የተሰኘ መጽሐፋቸው ከአያቶቻቸው ታሪክ…

‹‹የትግል ሚዲያ የሚል የሚዲያ ፈቃድ አልሰጠንም››

በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቡር አልጌ ከምትባል ትንሽ መንደር ነው ይህን ዓለም የተቀላቀሉት። አምስት ዓመት ሲሞላቸው በመምህርነት ሙያ ላይ የነበሩት ወላጅ አባታቸው ወደ አዲስ አበባ መዛወርን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተሙ። ዕድገታቸውም በአዲስ አበባ ከተማ ቀጠለ። የያኔው ብላቴና በኋላም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋዜጠኝነትና…

ሴታዊት ከኢዜማ ጋር መደበኛ የሆነ ቁርኝት የላትም

በማንም ላይ የሚደርስን ጥቃት የሚጠየፍ ስብዕና ከልጅነት ጀምሮ አብሯቸው የነበረ በተፈጥሮም የታደሉት ነው። “ፌሚኒስት ሆኜ ነው ራሴን ያገኘሁት” ይላሉ፤ ስሂን ተፈራ (ዶክተር)። ትውልድና ዕድገታቸው በአዲስ አበባ ነው። እኩልነትንና የሴት ልጅን ክብር እያዩ ባደጉበት ቤተሰብ፤ የአባታቸው መልካም ተግባራት በአረዓያነት ደጋግመው የሚያነሱት…

“አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሦስተኛ ውስጥ 18 ክፍሎች ጨለማ ቤቶች አሁንም አሉ።”

ስንታየሁ ቸኮል የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት መስራች አባልና የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንደነበሩ የሚናገሩት ስንታየሁ፥ በተለይ ከ1993 ጀምሮ በቀጥታ የፖለቲካ ፓርቲ ተሳትፎ እንደነበራቸውም ይናገራሉ። ከተሳተፉባቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ…

“የፍትሕ ስርዓቱ ከአስፈጻሚው አካል ነጻና ገለልተኛ አለመሆኑን አረጋግጬ ነው ከእስር የወጣሁት።”

ኤሊያስ ገብሩ የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ፀሐፊ ናቸው። ላለፉት 12 ወራት ከ12 በላይ በሆኑ የኅትመት መገናኛ ብዙኀን ላይ ከዘጋቢነት እስከ ዋና አዘጋጅነት ማገልገላቸውን የሚናገሩት ኤሊያስ፥ መሰናዘሪያ፣ አውራምባ ታይምስ፣ ፍትሕ፣ ዕንቁ፣ አዲስ ገጽ ከተሳተፍባቸው ጋዜጦችና መጽሔቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። የአባይ…

ኦኬሎ አኳይ ማን ናቸው?

ኦሌሎ አኳይ ኦቻላ የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ናቸው። ለዘጠኝ ወራት በክልል ፕሬዘዳንትንት፣ ለስምንት ዓመታት በስደት እንዲሁም ለአራት ዓመታት በእስር አሳልፈዋል። በኢፌዴሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቸኛው የተቃዋሚው የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኮንግረስ (ጋሕዴኮ) አመራር አባል ሆነው የክልል ፕሬዘዳንት መሆን የቻሉም ሰው ናቸው። ለመሆኑ…

የብርቱ እናትነት ተምሳሌት – ዘሚ የኑስ

የእናቶችን እንባ የተመለከቱ፣ ድምጽ አልባውን የልጆችን ስቃይ ያዳመጡ ሴት ናቸው፣ ገበያ ወጥቶ ‹ልጄን የማስርበትን ሰንሰለት ስጡኝ› ብሎ የመግዛትን ሕመም ተረድተውታል፤ ይህም በተለይ ኦቲዝም ያለበት ልጅ ለወለዱ እናቶች ቁስል እንደሆነ ደጋግመው ይናገራሉ። የቆሙበትን ቦታ ተረድተው፣ ምንም ሆነ ምን ብቻ ለምክንያት መሆኑን…

“ሜቴክ የስኬት ታሪክ አለው።”

ብርጋዴር ጀነራል አሕመድ ሐምዛ የብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክትር ናቸው። በአሁኑ አጠራሩ ደቡብ ወሎ ዞን በቀድሞ አጠራሩ ወሎ ክፍለ ሀገር፣ ወረኢሉ አውራጃ፣ ለጌዳ ወረዳ የተወለዱት አሕመድ፥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ወይን አምባ ኹለተኛ ደረጃን ደግሞ ወረኢሉ በሚገኘው አባውባየው ትምህርት ቤት…

“ብርሃን ስታይ ተከተል፤ ወደ ጨለማ እንዳይወስድህ መርምር”

ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (አአዩ) የፍልስፍና መምህር ናቸው። ውልደታቸው ደሴ ይሁን እንጂ ዕድገታቸው አዲስ አበባ ነው። የአንደኛ እና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው በጥሩ ውጤት በማጠናቀቅ በወቅቱ የነበረውን የቀዳማዊ ኀይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (አሁን አአዩ) ለከፍተኛ ትምህርት ተቀላቅለው ለአንድ ዓመት ተከታትለዋል።…

“በአገራችን አርዓያ እንዳይኖር፣ በታሪክ እንዳናምን ተደርጓል። ”

ኦባንግ ሜቶ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ናቸው። ወላጆቻቸው ካፈሯቸው ስድስት ወንድ ልጆች መካከል ሦስተኛ የሆኑት ኦባንግ፣ ውልደትና እድገታቸው ጋምቤላ ነው። በ16 ዓመታቸው ኢትዮጵያን ለቅቀው ወደ ካናዳ በማምራት የኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ምዕራብ ካናዳ ከሚገኘው ሳስካችዋን ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ…

ብሔራዊ ማንነት መፍጠር ባለመቻላቸው የፈራረሱ አገሮች አሉ።

በአሜሪካ ቺካጎ ግዛት እ.ኤ.አ በ1952 የተወለዱት ፈራንሲስ ፉኩያማ (ፕሮፌሰር) በሃርቫርድ ዩኒቨስሪቲ ፖለቲካል ሳይንስ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ሰርተዋል፡፡ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥናት፣ ምርመር እና ትምህርት የሚሰጡት ፍራንሲስ አወዛጋቢ በሆኑት መፅሃፍቶቻቸው ይታወቃሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በስታንፎርድ ዩኒቨስርሲቲ የዲሞክራሲ፣ የልማትና የሕግ የበላይነት ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር…

“አፋር ከኢትዮጵያዊነት ውጪ ሌላ ማንነት የለውም።”

ዶ/ር ኮንቴ ሞሳ የአፋር ሕዝቦች ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው። የተወለዱት በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ሲሆን አብዛኛውን የልጅነት ዕድሜያቸውን በአርብቶ አደርነት በተለይም ከግመል ጋር ማሳለፋቸውን የሚናገሩት ኮንቴ፥ የ1966ቱን ድርቅ ተከትሎ በመካከለኛው አዋሽ እርሻ ልማት አሁን ከሰም ቀበና ስኳር ፋብሪካ ቋሚ ሕይወት መጀመራቸውን…

“አገር ውስጥ ላለው ለውጥ ኢሳት እና ኦ ኤም ኤን ያበረከቱት አስተዋጽዖ ከማንም በላይ ዋጋ ሊሰጠው የሚችል ነው።”

 በፈቃዱ ሞረዳ  የብዙ ዓመታት ተመክሮ ያላቸው ጋዜጠኛ ናቸው። በ50ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙት በፍቃዱ፣ “ለእግራቸው መጫሚያ፣ ለራሳቸው ባርኔጣ” ከሌላቸው ደሃ ገበሬ ቤተሰብ በአሁኑ አጠራር በኦሮሚያ ክልል ኢሊባቦር ዞን መወለዳቸውንና እስከ 11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን መከታተላቸውን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውንም በእርሻ ሥራ ማገዛቸውን ይናገራሉ። በወቅቱ…

“ኢትዮጵያ አትፈርስም!”

አበበ ተክለ ሃይማኖት (ሜጀር ጀነራል) ከ1987 እስከ 1993 ድረስ የኢትዮጵያ አየር ኀይል ዋና አዛዥ በመሆን አገልግለዋል። ውልደታቸውና ዕድገታቸው መቀሌ ሲሆን እስከ 11ኛ ክፍል ድረስ ትምህርታቸውን እዛው መቀሌ ተከታትለው በወቅቱ በቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ሥር ይገኝ ወደነበረው…

“በሐረር ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት 650 ሔክታር መሬት ተዘርፏል”

አብዱላኪም ዮኒስ የሐረሪ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኀላፊ አብዱላኪም ዮኒስ ይባላሉ። ከለውጡ በኋላ የሐረሪ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኀላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ፣ ደንብ ማስከበር፣ የመሬት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሴፍትኔት ፕሮግራም፣ ማዕድንና ኢነርጂ፣…

“ኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ግል ማዛወር በጣም ትልቅ ስህተት ነው።” ዓለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ

ዓለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምጣኔ ሀብት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ናቸው። የሦስተኛ ዲግሪ (የዶክትሬት) ተማሪችን ማክሮኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነቶች ከማስተማራቸውም በተጨማሪ በሚሠሩት የምርምር ሥራቸው ያማክሯቸዋል። በኬኒያ – ናይሮቢ በሴንትራል ባንክ ኤንድ ትሬዠረሪ፣ በካምፓላ – ኡጋንዳ ኢፒአርሲ/ማካራሬ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በምሥራቃዊ…

“ኢዜማ የመከፋፈል ዕድል ይገጥመዋል ብለን አናስብም”

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ ናቸው። ብርሃኑ ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በንቃት በማሳተፍ በሰፊው ይታወቃሉ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ ቀስተ ዳመና እና ቅንጅት ለአንድነትና ዴሞክራሲ (ቅንጅት) ፓርቲዎች ውስጥ እስከ አመራርነት የደረሰ…

አዶኒክ ወርቁ የመዝናኛው ኢንዱስትሪ አንቀሳቃሽ

አዶኒክ ወርቁ በተለይ በመዝናኛ የቴሌቪዥን ዝግጅትና ትልቅ የንግድ ትርዒቶችን በማሰናዳት የሚታወቀው የሀበሻ ዊክሊ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነው። ውልደትና እድገቱ አዲስ አበባ የሆነው አዱኒክ፥ ከፍተኛ ትምህርቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፍ ተከታትሎ የመጀመሪያ ዲግሪውን ሰርቷል። በ2001 በሶፍተዌርና ኔትወርክ ልማት ላይ…

ፀጋዬ ገብረመድኅን ቀዌሳ (ሎሬት)

ይህ ቃለ ምልልስ ፀጋዬ መድኅን (ሎሬት) ከዌንዲ ላውራ ጋር ለኢትዮጵያን ሪቪው እ.ኤ.አ. በ1998 ያደረገው ቃለ ምልልስ ትርጉም ነው። ተርጓሚው ጥላሁን ግርማ አንጎ ትርጉሙን በግጥሞቹ አዋዝተዋቸዋል። ከግጥምና ጸሐፌ ተውኔቱ ፀጋዬ ገብረመድኅን በተሻለ ለኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ ታላቅነት ተምሣሌት ሊሆን የሚችል የለም። ከ1960ዎቹ…

ልዩ ቃለ ምልልስ ከጎሣዬ ተስፋዬ ጋር

‘ሲያምሽ ያመኛል’ በሚል ርዕስ ሦስተኛ የሙዚቃ አልበሙን ከሦስት ወር በፊት የለቀቀው ድምፀ መረዋው ጎሣዬ ተስፋዬ፥ ቅዳሜ፣ ሚያዚያ 26 ለሚያካሒደው የሙዚቃ ድግሥ 2 ሚሊዮን ብር ሀበሻ ዊክሊ ሊከፍለው ውል አስረዋል። በተስረቅራቂ ድምጹና በአዚያዚያም ስልቱ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ እንዳኖረ…

˝ኦዲፒ ስግብግብ የመሆንና ሁሉንም የእኛ ነው የማለት ዓይነት ዝንባሌ አሳይቷል˝

ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግና አስተዳደር ኮሌጅ መምህርና በፌደራሊዝምና ሰብኣዊ መብቶች ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። ትውልዳቸው ራያ፣ አላማጣ ሲሆን በልጅነታቸው ቤተሰባቸውን በእረኝነት አገልግለዋል። በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት ሲከፈትም ዕድል አግኝተው ለመከታተል የቻሉ ቢሆንም፥ የትውልድ ቀያቸው በደርግና በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ…

በሥራ ላይ ሴትነቴ ትዝ ብሎኝ አያውቅም

ሒሩት ወልደማርያም (ፕሮፌሰር) የመጀመሪያ እና ኹለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ልሳን ትምህርት ዘርፍ ይዘዋል። ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ጀርመን አገር ከሚገኘው ኮሎኝ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ የትምህርት መስክ ሠርተዋል። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመመለስ በተማሩበት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍል መምህር፣ ተመራማሪና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ…

˝የመብት ተሟጋችነትና ጋዜጠኝነት የተለያዩ ነገሮች ብቻ ሳይሆኑ ተፃራሪም ናቸው˝

ተሻገር ሽፈራው (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ቤት የድኅረ ምረቃ መርሃ ግብር አስተባባሪና መምህር ናቸው። ኹለት የመጀመሪያ ዲግሪዎች በፍልስፍና እና በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት አላቸው። የማስተርስ ዲግሪያቸውን በጋዜጠኝነትና ተግባቦት የሠሩት ተሻገር፥ በ2009 የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሥነ ልሳንና ተግባቦት…

“በትግራይ የትጥቅ ትግል ዝግጅት መኖሩ የአደባባይ ሚስጢር ነው”

አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ሊቀ መንበር ናቸው። የተወለዱት በትግራይ አድዋ ሲሆን፣ አንደኛና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዛው አድዋ ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ማጥናት ጀምረው ነበር። ኋላቀርነት እና መጥፎ ስርዓት ያመጣው…

‹‹ሁሉንም መቆጣጠር አንችልም››

ገመቹ ዱቢሶ ለመምራት ወስብስብ ከሆኑ ተቋማት ከሚመደቡት መካከል የሆነውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን ከዘጠኝ ዓመት አንስቶ እየመሩ ይገኛሉ። ተቋሙን እንዲመሩ በፓርላማ ከመመረጣቸው በፊት የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት ገመቹ፦ ወደ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የመጡት በአጨቃጫቂ…

“እኛ መርዶ ነጋሪ ፖለቲከኞች አይደለንም”

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀ መንበር ናቸው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በታሪክና በኢኮኖሚክስ በተናጠል የያዙ ሲሆን፣ በተቀናጀ የውሃ ተፋሰስ ልማት የኹለተኛ ዲግሪያቸውን በውሃ ማኔጅመንት በተለይ የጥናታቸው ትኩረት ‘ሃይድሮሎጂ’ እና ‘ኢሮዥን’ ላይ በማድረግ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ሠርተዋል። በሥራው ዓለም በአጠቃላይ የዐሥር…

“ለውጡን የሚመጥን ሥራ ካልሠራን፥ አስቸጋሪ እንደሚሆን በደንብ እረዳለሁ”

ብርቱካን ሚዴቅሳ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ናቸው። ፊታቸው በፈገግታ የተሞላው፣ ለማነጋገርም ቀለል ያሉት ብርቱካን ቀደም ሲል ዳኛ፣ የቅንጀት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የአንድነት ፍትሕና ዴሞክራሲ ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል። በፖለቲካ ተሳትፏቸው ጎላ ብሎ ከሚነሱት ሴቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚሰለፉት ብርቱካን፥…

“እስካሁን የተሞከረው አዲሱን አስተሳሰብ በአሮጌው መዋቅር ውስጥ [ማሠራት] ነው”

ዩናስ አዳዬ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የአካዳሚክ ተባባሪ ዳይሬክተር ሆነው ላለፉት አራት ዓመታት በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ዮናስ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋምን ከማቋቋም ጀምሮ የመጀመሪያው ዳይሬክተር ሆነው ለሁለት ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፥ በርካታ ከሰላምና ደኅንነት ጋር በተያያዘ ያሳተሟቸው…

This site is protected by wp-copyrightpro.com