መዝገብ

Category: ማኅበረ ፖለቲካ

ብሔራዊ “አለመግባባት”

ቤተልሔም ነጋሽ ሰሞኑን በአንዳንድ ባለሥልጣናትና የመብት አራማጆች የተፈጠሩ እሰጣ ገባዎችንና ንትረኮችን እንዲሁም የተፈጠሩ ኩነቶችን በማንሳት ለእብደት እየዳረጉን ነው ሲሉ ያማርራሉ፤ መፍትሔውም መቆጨት ነው ሲሉም አመላክተዋል።     የሰሞኑን ዙሪያ መለስ ትርምስና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ጉዳዮች ችላ ሲባሉ ላየ፤ ከግራ ቀኝ…

ደብሊን፤ ጊነስ ቢራና የአየርላንዳውያን አበርክቶ

ቤተልሔም ነጋሽ ባለፈው ሳምንት የጀመሩትን የአየርላንድ ጉብኝት በዚህ ሳምንት ያጠቃልላሉ። የዚህኛው መጣጥፋቸው የሞሃር ገደሎችን፣ የጊነስ ቢራ ታሪክ ሥፍራ እንዲሁም መዘክራቸውን ከማስጎብኘታቸው ባሻገር ከአገሬው ወግ ጀባ ብለዋል።     (ክፍል ኹለት) ደህና ብራ ሆኖ ከርሞ አስተናጋጅ ጓደኛዬን ይህን አየር ጠባይ ነው…

የደብሊን ተረኮች – ከውስኪ ሙዚየም እስከ አራቱ ወንጌላት

ለዕረፍት ኹለት ሳምንታትን በአየርላንድ ያሳለፉት ቤተልሔም ነጋሽ፥ የአገሪቱ መስህብ ከሆኑት መካከል በተለይ ስለውስኪ ሙዚየም እና ስለታዋቂው ቡክ ኦፍ ኬልስ ኤግዚቢሽና ቤተመጻሕፍት በመጻፍ ተደራሲያንን የጉብኝታቸው ተቋዳሽ አድርገዋል።     ስትገዙት ሀብታም የሚያደርጋችሁ ብቸኛ ነገር ጉዞ ነው። “TRAVEL IS THE ONLY THING…

“ሰንበት ለሰው እንጂ፥ ሰው ለሰንበት አልተሠራም!”

መንግሥት ሕግ ወይም መመሪያ የማውጣት ተመክሮው ለማሠራት ሳይሆን ለማሰር፤ ለሰው ሳይሆን በሰው ላይ እንደነበር የሚተቹት ቤተልሔም ነጋሽ፥ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የወጣውንና በተለይ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የብዙዎች መነጋገሪያ የሆነውን የኤሌክትሮኒክ የታክሲ ስምሪት (የኤታስ) አገልግሎት አሰጣጥ ለመወሰን…

“ራዕይ በሌለበት ተስፋ የለም”

አምና ከነበርንበት በባሰ ሁኔታ እንገኛለን የሚሉት ቤተልሔም ነጋሽ፣ እንደሕዝብ መሥራት የነበረብንን የቤት ሥራ ባለመሥራታችን፣ ስንጀምረው ምናልባት ስለምንመኘው ውጤት እንጂ ስለአካሔዳችንና ስለሒደቱ፣ በሒደቱም ሊገጥመን ስለሚችለው እንቅፋትና ተግዳሮት ያንንም ለማለፍ ስለሚያስፈልገን ዝግጅት ባለመምከራችን የመጣ ነው ሲሉ ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል። በግልም ይሁን በመንግሥት በጋራ…

“የሴቶችን መብት ለማሳነስ ሕገ መንግሥቱን እስከመተው?”

ቤተልሔም ነጋሽ በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ረቂቅ” በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁን መነሻ በማድረግ፥ ከሴት ተወዳዳሪዎች ጋር በተያያዘ የተካተተውን አንቀጽ አግባብነት የለውም ሲሉ ተችተዋል። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 35 የተዘረዘሩትን የሴቶች መብት አትንጠቁን ሲሉም…

ወሲብ ንግድ ወንጀል ሳይሆን – አንድ መልኩን መከልከል ይቻላል?

ቤተልሔም ነጋሽ ባለፈው ቅዳሜ፣ ነሐሴ 17 የአዲስ ማለዳ ዕትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴተኛ አዳሪነት፣ ልመናና ጎዳና ተዳዳሪነትን ለመከላለከል ያዘጋጀውን ረቂቅ ሕግ መሰረት በማድረግ በተለይ ሴተኛ አዳሪነትን በተመለከተ አንድ መጣጥፍ ማስነበባቸው ይታወሳል። ጽሑፉን በሚያዘጋጁበት ወቅት ረቂቅ ሕጉን ማግኘት ባለመቻላቸው የመገናኛ…

የወሲብ ንግድን በሕግ መከልከል ፤ የበሽታውን መንስዔ ትቶ ምልክቱን?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሲብ ንግድን፣ ልመናንና ጎዳና ተዳዳሪነትን የሚከለክል አዲስ ሕግ ለማውጣት ረቂቅ ማዘጋጀቱን መነሻ በማድረግ፥ ቤተልሔም ነጋሽ የወሲብ ንግድን በተመለከተ ሕጉ መነሻውን ሳይሆን ምልክቱን ለማከም የሚሞክር እንዳይሆን ሲሉ ያላቸውን ሥጋት አንጸባርቀዋል።     “የወሲብ ንግድ ፣ አስቀያሚ ማኅበራዊ…

የማስተማሪያ ቋንቋ ጉዳይ

ቤተልሔም ነጋሽ የአፍ መፍቻ ቋንቋን ትምህርት ለማስተማር ተግባራዊ የተደረገውን ፖሊሲ በተመለከተ የሐረሪ ክልልን እንደማሳያ ተጠቅመው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የተጠና ጥናትን ዋቢ አድርገው ፖሊሲው ከአተገባበሩ ጋር አልተጣጣመም ሲሉ መከራከሪያቸውን ተግዳሮት ካሏቸው ነጥቦች ጋር አቅርበዋል፤ ፖሊሲው ክለሳና ማሻሻያ ያስፈልገዋልም ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።…

ሚዲያና የሴቶች ነገር

መገናኛ ብዙኀን ማኅበረሰቡ ለሴቶች የሚሰጠው ቦታ፣ ደረጃና አመለካከት በአጠቃላይ አሉታዊ ጅምላ ፍረጃ ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተዛባ አመለካከት ሰለባ አድርጓቸዋል ሲሉ ኹለት የቴሌቪዥን መርሃ ግብሮችን ለአብነት የጠቀሱት ቤተልሔም ነጋሽ፥ ይህንን በሚመለከት በተለይ በመገናኛ ብዙኀን ላይ መወሰድ ይገባቸዋል ያሉትን እርምጃዎችንም ጠቁመዋል። ባለፈው እሁድ…

ከሴት ሕፃን ልጅና ከችግኝ፡ የማን ሕይወት ይበልጣል?

ሴት ሕፃናትን “አስገድዶ” በመድፈር ወንጀል የፈጸሙ አንድ አዛውንትንና ችግኞችን በመንቀል በተከሰሰ ግለሰብ ላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፈባቸውን ቅጣት በማነፃፀር ጽሑፋቸውን የሚጀምሩት ቤተልሔም ነጋሽ፥ የሴት ሕፃናትና ሴቶች ደኅንነት ለመንግሥት አንገብጋቢ አይደለም ሲሉ መከራከሪያቸውን አቅርበዋል። ሐሳባቸውንም ለማጠናከር አሳማኝ ያሉዋቸውን ማስረጃዎች ጠቃቅሰዋል። ገና ርዕሱን…

ረቂቅ የምርጫ ሕጉ እና ሴቶች “እኩል ውክልና ከሌለ ድምጽ አንሰጥም ብንልስ?

የምርጫ ረቂቅ ሕጉን መነሻ ያደረጉት ሩት ሰለሞን፥ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ በሁሉም መስክ ለማረጋገጥ እያደረገች ያለችውን ጅምር ጥረት በማድነቅ የሴቶችን መብቶች ለመጠበቅ በሕገ መንግሥቱ የተካተቱትም ሆነ አገሪቱ ፈርማ ያጸደቀቻቸውን ዓለም ዐቀፍ ስምምነቶች መከበር እንዳለባቸው ያሳስባሉ። ሩት ረቂቅ የምርጫ ሕጉ እነዚህን…

ማኅበራዊ ፍትሕ ስለማስፈን – የአዲስ አበባ ነፃ ዩኒፎርምና ደብተር ዘመቻ እንደማሳያ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ በቅርቡ ተማሪዎችን መመገብ፣ ደብተርና ዩኒፎርም በነፃ መስጠትን እንደ አንድ የማኅበራዊ ፍትሕ ማስፈኛ መንገድ ማሳያነት የተጠቀሙት ቤተልሐየም ነጋሽ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደሃ ዜጎች መኖሪያ በሆነችው ኢትዮጵያ እነዚህ ተግባራት እንደመልካም ልምድ መወሰድ ይገባቸዋል ይላሉ። ይሁንና ማኅበራዊ…

ሞምባሳ፤ የኬንያዋ የባሕር ፈርጥ

ለሥራ በተለያዩ አገሮች የሚጓዙት ቤተልሔም ነጋሽ፥ ገላጭ በሆነው ጽሁፋቸው የቱሪስቶች መናኸሪያ የሆነችውን የኬንያዋን የባሕር ዳርቻ ከተማ ሞምባሳን ያስቃኙናል፤ በጎ በጎውን ብቻ ሳይሆን ሥጋት ናቸው ያሏቸውንም ጉዳዮች ከትበዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሞምባሳ ቀጥታ በረራ ያደርጋል። ኢቲ 322 ከዚህ…

“አንበሳው መጻፍ እስኪማር፤ ሁሉም ታሪክ አዳኙን ያወድሳል” የአፍሪካውያን አባባል

ኢትዮጵያ በዓለም ዐቀፍ ቋንቋ ብዙ ጻሕፍት ማፍራት ባለመቻሏ ሌሎች ለእኛ የሚኖራቸው ግምት የተሳሳተ እንደሆነ ቤተልሔም ነጋሽ በሥራ አጋጣሚ በተዘዋወሩባቸው የአፍሪካ አገራት መታዘባቸውን መነሻ በማድረግ የራሳችንን ታሪክ መጻፍ ካልቻልን ሌሎች በፈለጉት መንገድ ታሪካችንን እንደሚጽፉትም ማስረጃ በማጣቀስ መከራከሪያቸውን አቅርበዋል። በርግጥ ኹለት ኢትዮጵያውያን…

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ – የምንከፍለውን ዋጋ ለመቀነስ

በቅርቡ በአማራ ብሔራዊ ክልል የተካሔደውን “መፈንቅለ መንግሥት” መሰረት በማድረግ መንግሥት ተከታታይና ወቅታዊ መረጃ መስጠት አለመቻሉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲስፋፉ በማድረግ ወደ ብጥብጥና አለመረጋጋት ሊያመራ ይችላል የሚሉት ቤተልሔም ነጋሽ፥ ኮሽ ባለ ቁጥር ኢንተርኔትና ማኅበራዊ ሚዲያን መዝጋት እስከ መቼ መፍትሔ ይሆናል ሲሉም ይጠይቃሉ።…

የ“ፌሚኒዝም”ን ዓይነት የተሻለ ዓለም ለመፍጠር

“ፌምኒዝም” ከቃሉ እስከ ጽህሰ ሐሳቡ ብዙዎችን ያጨቃጭቃል። ቤተልሔም ነጋሽ ከቀላሉ የመዝገበ ቃላት ብያኔው በመነሳት በሴትና በወንድ እኩልነት ላይ ተመስርቶ የሴቶች መብት እንዲከበር የሚሠራ ንቅናቄ ሲሉ ይንደረደራሉ። ፌሚኒዝም ጎጂ ባሕልን ከመቃወም ባሻገር በኢትዮጵያ መሰረታዊ መብቶች መከበር ያስፈልጋል ሲሉ መከራከሪያ ሐሳብም ያቀርባሉ።…

ምርጫ ሲመጣ፣ የመረጃ ነፃነት በምርጫ ወቅት ቢታይ

መጪውን የ2012 አገራዊ ምርጫ እሳቤ ውስጥ በመክተት ቤተልሔም ነጋሽ ከኹለት ዓመት በፊት በአፍሪካ ኅብረት የፀደውን “የአፍሪካ የምርጫ ወቅት የመረጃ ነፃነት መመሪያ” የሚል ሰነድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከወጣው መመሪያ ቁጥር 6/2010 ጋር አብረው ግንዛቤ በሚሰጥ መልኩ ቃኝተውታል። “ለመገናኛ ብዙኀንና ለጋዜጠኞች ምርጫ…

የሕፃናት ማቆያ ጉዳይ

የሕፃናት ማቆያ ለሴት ሠራተኞች የሥራ ላይ ውጤታማነት የሚጫወተውን ሚና ከፍተኛነት የጠቀሱት ቤተልሔም ነጋሽ, በአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተጀመረው የሕፃናት ማቆያ ስፍራዎች ማዘጋጀት የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባ መሆኑን ገልጸው ብዙ ርቀት መጓዝ እንደሚቀር ግን የአገራት ልምዶችን በማጣቀሻነት አቅርበዋል።   አዲስ ዓመት…

የሚያበራየውን በሬ አፉን ላለማሰር

የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን ሠርተው ለሚያድሩ ሠራተኞች እንደ ክህደት መቁጠር አግባብ አይደለም በማለት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የቅርብ ጊዜ ንግግርን የሚተቹት ቤተልሔም ነጋሽ፥ እንዲያውም ለሠራተኞች ተመጣጣኝ ክፍያ የሚያገኙበትን አሠራር በፖሊሲ ደረጃ ቀርፆ መከታተል ያስፈልጋል ይላሉ።     “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፥…

የአንበሳ ቢራ ማስታወቂያ እግድ ተገቢ ወይስ የደቦ ፍርድ ያመጣው ውሳኔ?

የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና የኅትመት መገናኛ ብዙኀን ሲተላለፍ የቆየውን የአንበሳ ቢራ ማስታወቂያ ሸማቾችን የሚያሳስት መልዕክት ይዟል በሚል ምክንያት ከግንቦት 6/2011 ጀምሮ በማንኛውም ሚድያ እንዳይተላለፍ ያስጠነቀቀበት አግባብ የፍትሓዊ ጥያቄ ያስነሳል ሲሉ ቤተልሔም ነጋሽ መከራከሪያቸውን አቅርበዋል።   “በማስታወቂያ…

ከማመን መጠየቅ፣ ከማድረግ ማሰብ እንዲቀድም

የኡጋንዳ ተሞክሯቸውን መነሻ በማድረግ ቤተልሔም ነጋሽ÷ ስለ ሒሳዊ ትችት ወይም ራሳቸው በተጠቀሙበት ሐረግ አጠንክሮ ማሰብና መጠየቅን በተመለከተ ከማመን በፊት መጠየቅ እንደሚቀድም ከድርጊት ደግሞ ውጤትና ዓላማን የመመርመርን ጠቀሚነት አስምረውበታል’ እንዴት የአጠንክሮ ማሰብና መጠየቅን ክህሎት ማደበር እንደሚቻልም መንገዶችን ጠቁመዋል ።   “በዓለማችን…

ምነው በሴቶች ላይ “መቀነስ” በዛ?

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር ያደረጉትን ውይይት መነሻ በማድረግ በተለይ ለሴት ሐኪሞች ጥያቄዎችና የሥራ ላይ ተግዳሮትን በተመለከተ የተሰጡትን ምላሾች በመተቸት ቤተልሔም ነጋሽ ይህንን ጽሁፍ አዘጋጅተዋል።     በሥራ ላይ ከቆየሁባቸው ዓመታት አንጻር ምናልባት በሕይወቴ…

በ“ዘር” እና በ“ብሔራዊ ማንነት” መካከል

በአገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው በዘር ወይም በብሔርና በማንነት የማመን ጎራ መነሻ በማድረግ፥ ቤተልሔም ነጋሽ ኹለት የመንግሥት አወቃቀሮችን በማነጻጸር ምናልባት አስታራቂ ሊሆን የሚችል ሐሳብ ለማምጣት የሚቻልበትስ ሁኔታ አለ ሲሉ ይጠይቃሉ።     “የሰው ልጅ አመክንዮ ስህተት ሊሆን መቻሉና አመክንዮን…

በ“ማንነት” ሥም

በኢትዮጵያም ይሁን በዓለም ዐቀፍ ነባራዊ ሁኔታዎች የማንነት ጉዳይ አንገብጋቢ ሆኗል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ያለው የማንነት አረዳድ በአንድ ነገር ላይ ብቻ የተቸከለ ነው። ቤተልሔም ነጋሽ በሕይወት ገጠመኛቸው እና ንባባቸው የተረዱትን በማጣቀስ የማንነት ጉዳይ ውስብስብ እንደመሆኑ በቀላሉ ለመተርጎም መሞከር እንደማይገባም ያመላክታሉ።  …

የንግድ ባንክ “ሴት ሠራተኞች ቅርንጫፍ” እና የሴቶች “እኩልነት”

በቅርቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴት ሠራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጡበትን አዲስ ቅርንጫፍ ቢሮ መክፈቱን መነሻ በማድረግ ቤተልሔም ነጋሽ፥ የዓላማውን አሳማኝነት በማጠየቅ ውጤታማ የሆኑትን ሴት ሠራተኞቹን በሽልማትና በሹመት ወደ ተሻለ ቦታ በማድረስ በሥራ አመራርና ከፍተኛ ቦታ ላይ ያሉትን ሴቶች ቁጥር መጨመር የተሸለ…

ብዙኀን መገናኛዎች የሁሉንም ድምፅ አካታች እንዲሆኑ

ብዙኀን መገናኛዎች ብዝኀነትን ማካተታቸው የሚረጋገጠው በሚያስተናግዱት የሐሳብ ብዝኀነትም እና በሥራ በሚያሳትፏቸው ሰዎች ነው የሚሉት ቤተልሔም ነጋሽ፣ ስለ ብዙኀን መገናኛዎች አካታች መኾን እና ሕዝቦቻቸውን መምሠል አስፈላጊነት የሚከተለውን ጽፈዋል።     “አንድ ነጻ ፕሬስ ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል። ነገርግን ያለነጻነት ፕሬሱ መጥፎ…

“ለውጡ” ሴቶችን ከጥቃት ለማስጣል እንዲበቃ የመዓዛ ካሣ ጉዳይ እንደማሳያ

ባሳለፍነው ሳምንት ከሰማናቸው አሳዛኝ ዜናዎች አንዱ መዓዛ ካሣ የተባለች ግለሰብ በሥራ ባልደረባዋ በደረሰባት ጥቃት ሕክምና ስታገኝ ቆይታ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ጥቃት የፈፀመባት ሰው ከእስር ቤት ማምለጡ ደግሞ ሌላው አሳዛኝ ገጽታ ነው። ቤተልሔም ነጋሽ ይህንን ክስተት…

እንስታዊነት

“ሴቶች ሰብኣዊ ፍጡራን ናቸው ብሎ የማመን ፅንፈኛ ፍልስፍና” ‘እንስታዊነት’ (‘ፌሚኒዝም’) ሴቶች ከወንዶች እኩል የተጠበቁ መብቶች እና ዕድሎች እንዲያገኙ የሚደረግ የፖለቲካ ንቅናቄ ነው። ቤተልሔም ነጋሽ ለዚህ ጽሑፍ በንዑስ ርዕስነት የተጠቀሙት “እንስታዊነት ሴቶች ሰብኣዊ ፍጡራን ናቸው ብሎ የሚያምን ፅንፈኛ አስተሳሰብ ነው” (“Feminism…

የተዛባው ምሥል

ማኅበረሰቦች በተለያዩ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ምክንያቶች ስለ አንድ የማኅበረሰብ ክፍል የተሳሳተ ምሥል ይፈጥራሉ። ሙኒራ አብድልመናን በዚህ መልኩ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተሰጣቸውን የተዛባ ምሥል አግባብ አለመሆን በመተንተን የውክልናን ፋይዳ እና የተዛባ ምሥልን ዳፋ በዚህ መጣጥፋቸው ያስረዱናል። መግቢያ ጓደኛዬ ነው፤ ብዙ ነገሬን ያውቃል።…

This site is protected by wp-copyrightpro.com