መዝገብ

Category: ዓውደ-ሐሳብ

በለውጥ ሐሳብ ጎዳና ማኅበራዊና ፖለቲካዊ እሳቤዎች

የግለሰቦች ተራማጅነት ወይም አፈንጋጪነት ትርጉም አልባ በሆነ ጊዜ የሞያ ክብር አይኖርም የሚሉት ፍቃዱ ዓለሙ፣ ሐሳቦች ቡድናዊ በሆነ ዲስኩራዊ ቅኝት ሊያልፍ የግድ የሚልባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን ያነሳሉ። ይህም ብዙ የለውጥ ሐሳቦችን ያሳጣና ያመከነ ጉዳይ ነው ሲሉ የሙግታቸውን የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው አቅርበዋል። የማሰብ፣…

የማንነት ፖለቲካ ያገበረው ፕሬስ በኢትዮጵያ

መገናኛ ብዙኀን በኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ በፈጠረው ውስብስብ ማኅበረ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የማንነት ፖለቲካ ልክፍት ውስጥ ለምን ገቡ ሲሉ የሚጠይቁት ፍቃዱ ዓለሙ፣ ይህን መሠረት በማድረግ የመገናኛ ብዙኀን ባለቤቶች ሐሳብና ፍላጎት እንዴት በመገናኛ ብዙኀን እንደሚንጸባረቅ አንስተዋል። እንዴት መስተካከል ይችላል የሚለውም ላይ የመፍትሔ ሐሳብን አቅርበዋል።…

የአያት የገበያ ማእከል ሰቆቃ መቼ ነው የሚያበቃው?

አዲስ አበባ መልኳን እንደ ሥሟ ለማደስ ደፋ ቀና በምትልበት ጊዜ፣ በተለያየ መልክ የሚነሱና በተለያዩ አካላት የተፈጸሙ ድርጊቶች ወደኋላ እየጎተቷት ይታያሉ። በተለይ እውቅና ተሰጥቷቸው በልማት ሥራ ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ያሉ አካላት፣ በብልሹ አሠራር ውስጥ ሲጠመዱ፣ ለከተማ ልማት ሊመጡ የሚችሉ እድሎች…

ለዘመናዊ ችግር አሮጌ መፍትሔ

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ እና አብዛኛው ኦሮሚያ ክልል ከተሞች ላይ ከተነሳው አለመረጋጋት እና መነሻውን በድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት ያደረገው ኹከት ከመንግስት የተሰጠው ግብረ መልስ እና ለማረጋጋት የተወሰደው እርምጃ ከዚህ ቀደሙ የተለዩ እንዳሆኑ በአመክንዮ የተቀመተበት ጉዳይ ሆኗል። በዚህ ጽሑፍም የደቡብ ምስራቅ…

‹ኢንተርኔት› የሌለ ጊዜ!

በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። ይህም ለአገር ሰላምና ደኅንነት በሚል እንደሆነ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ከሚያደርጉ ሰዎች ወገን ቢሰማም፣ በአንጻሩ ‹ምስጢር ለመደበቅ ነው! ሰዎች እንዳይናገሩ ለማፈን ነው!› የሚሉም አሉ። መቅደስ ቹቹ ይህን ሐሳብ አንስተው፣ በተለይ አሁን ላይ ይልቁንም የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን…

የደረሰው ሳይሆን የሚደርሰው ጥቃት!

የሴቶችና ሕጻናት ጥቃት በየጊዜው ተፈጸመ ሲባል ይሰማል። መፍትሄ ሳይገኝ ግን ተመሳሳይና የከፋ ሌላ ጥቃት ይደርሳል። ሰዎችም በየጊዜው የደረሰውን ጥቃት እንጂ ወደፊት ሊደርስ የሚችለውንና እየደረሰ ያለውን ልብ አይሉም። ይህም በሰብአዊ መብትና በሰብአዊነት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው። መቅደስ ቹቹ ይህን ሐሳብ አንስተው፣…

ግልጽ ደብዳቤ ይድረሰ ለኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ምሁራን፣ አባገዳዎች እንዲሁም ቄሮዎች

በቅድሚያ የአክብሮት ሠላምታ አቀርባለሁ። ይህቺን የግሌ የሆነች አጭር መልዕክት ከቁም ነገር አስገብታችሁ በጥሞና እንደምትመለከቷት ስለማምንም ቀድሜ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። አባቶቼና ወንድሞቼ፣ እህቶቼ እንዲሁም ልጆቼ ለምትሆኑ ሁሉ በቅድሚያ ለመልዕክቴ መነሻ የሆነኝን ምክንያት እንድገልጽ ፍቀዱልኝ። ዛሬ እየተከናወነ ስላለው አገራዊ ጉዳይ የተለያየ አመለካከት ቢኖርም…

አሜሪካ ግን በኢትዮጵያ ላይ ድርሻዋ ምን ያህል ነው?

አገራት ልዕለ ኃያልነት ከጊዜያት ወዲህ እንደቀደሙት ኣመታት አይሁን እንጂ ከቴክኖሎጂ ጋር አብሮ በመዘመን ምናልባትም ለሚዘምነው ቴክኖሎጂም የራሰቸው (አስተዋጽኦ መኖሩ ባያጠራጥርም) አብረው እየገነኑ ለቀሪው ዓለም ገናናነታቸውን ማሳያ ካደረጉ ውለው አድረዋል። ይኸው ልዕለ ኃያልነት እና የጡንቻ ውድድር ታዲያ ኃያላን አገራት እርስ በራስ…

ዐይናችንን ከዋናው መዳረሻችን ላይ አንንቀል!

የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የአንበጣ መንጋ፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብና ድርድሩ፣ 2012 አገራዊ ምርጫ ጉዳይ፣ የፌዴራልና በክልል መንግሥታት መካከልና ውስጥ የሚነሱ ውዝግቦች ወዘተ በኢትዮጵያ የጉዳይ ገበታ ላይ በየዓይነቱ ተቀምጠዋል። ሁሉንም ችግር የመፍታት ግቡ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ኑሮ ከድህነት ወለል አሻግሮ…

ኮቪድ-19 – በዕውቀትና በዕውቀት ብቻ የሚዋጉት ጠላት ነው!

ኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭቱን ቀጥሎ ዘግይቶ የጎበኛትን አፍሪካም እያስጨነቀ ይገኛል። ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቋቋም በሚደረግ ሂደት ውስጥ ታድያ በየጊዜው ተለዋዋጭ አካሄዶች ቢታዩም፣ በአፍሪካ ይልቁንም በኢትዮጵያ የሚታዩ ስህተቶች ግን ዋጋ እንዳያስከፍሉ እንደሚያሰጋ ግዛቸው አበበ አንስተዋል። በተለይም ባለሥልጣናትና ሹመኞች ከሙያቸውና ከሕዝብ…

ኢትዮጵያ፣ ሚዲያና ዴሞክራሲ

መገናኛ ብዙኀን መንግሥትን ተጠያቂ ከማድረግ ጎን ለጎን በአንድ አገር ውስጥ ለሚደረጉ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ውይይቶች መድረክ የሚፈጥር እንዲሁም ሦስቱ የመንግሥት አካላት እርስ በእርስም ሆነ በተናጠል የሚሠሩት ሥራ ግልጽነት እንዲኖረው የሚያደርግ የዴሞክራሲ መሣሪያ ነው። እነዚህ የዴሞክራሲ መሣሪያ የተባሉ ተቋማት ታድያ የየራሳቸው ርዕዮተ…

በአስቸጋሪ ወቅቶች ከሥራ ኃላፊዎች የሚጠበቁ የአመራር ስብዕናዎች

በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት የንግድ ተቋማትና ገንዘብ አንቀሳቃሽ ትልልቅ ድርጅቶች በራቸው ከተዘጋ ከራርሟል። በርን ዘጋግቶ ሕይወትን መቀጠል ግን ከጥቂት ወራት በዘለለ እንደማያስሄድ ሆኗል። እናም ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ወደ ሥራው እንቅስቃሴ መግባት ግድ እንደሚል አመላካች ጉዳዮች ታይተዋል የሚሉት አብርሐም ፀሐዬ፣…

ጉዞው ከአንዱ ኮሮና ወደ ብዙ ‹ኮሮናዎች› እንዳይሆን!

ከሰሞኑ በአዲሰ አበባውና በመቀሌው ቡድን መካከል የሚታየው የዛቻ ልውውጥ እንደ ዋዛ መታየት አይገባውም የሚሉት ግዛቸው አበበ፣ ቀድሞ በሕወሓትና ሻእብያ መካከል የነበሩ ተመሳሳይ መልክ ያላቸውን የቃላት ልውውጦች አውስተዋል። በቃላት መተነኳኮሱ አዲስ ነገር ስላልሆነ ቀላል ቢመስልም፣ መዘላለፎች አሁን ወደ ጦርነት ዛቻ እያደጉ…

ኮቪድ 19 በሕጻናት ዓለም

ልጆችና ሕጻናት ባለንጹህ ነፍስ ናቸው። የአዋቂዎችን ያህል በዙሪያቸው ያሉ ነገሮችን አይረዱም። የራሳቸው ዓለም አላቸው፣ በራሳቸው መንገድ ነገሮችን ይተረጉማሉ። እንደ ንጹህ ወረቀት የሚያርፍባቸውን ይከትቡና ይይዛሉ። ለአዋቂነት መሠረት፣ ለልምድ መጀመሪያ ለጸባይና ለአመል መሠረት በዚህ የልጅነት እድሜ ይጣላል። ታድያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ መከሰት…

ኮቪድ 19 በምጣኔ ሀብት ላይ ያለው ተፅዕኖና መዉጫ መንገድ

የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ካመሳቀላቸው የሰው ልጅ ምድራዊ ስርዓቶች መካከል ቫይረሱ በማኅበራዊ ሕይወት የሚፈጥረውና የፈጠረው ማኅበራዊ ምስቅልቅሎሽ አንዱና ተጠቃሹ ነው። ይህም በአንድ ጀንበር የሚገለጥ ሳይሆን እያደር የሚታይ ሲሆን፣ ከምጣኔ ሀብት ድቀት ጋርም ዝምድናው የጠነከረ ነው። በተለይም የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከል…

የአንበጣ መንጋ፣ ኮቪድ-19 እና የምግብ አቅርቦት

ኮቪድ 19 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ በቀጠለበት በዚህ ሳምንት፣ አፍሪካ ከሌሎች ክፍላተ ዓለም አነስተኛ ነው ቢባልም እድገቱ ያልቀነሰ የቫይረሱን ወረርሽኝ አስተናግዳ ቀጥላለች። ይህም ስርጭት ከአሁን በባሰ ወደፊት ይመጣል የሚል ስጋት እየተሰማ ሲሆን፣ አፍሪካ የሚሆነውን በመጠበቅ ውስጥ የነበሩ ችግሮቿንም…

ኮሮናና የማስኩ ገበያ!

ኮቪድ-19 የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ፣ ሰዎች ማኅበራዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ አካሄድ እንዲቀይሩ ተገደዋል። አንደኛውም አካላዊ ወይም ማኅበራዊ ፈቀቅታ ሲሆን፣ ለዚህም የሚያግዙ ሳኒታይዘር፣ የእጅ ጓንትና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች ተጠቃሽ ናቸው። ይልቁንም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክን በሚመለከት መገናኛ ብዙኀን የተለያዩ ባለሞያዎችን የተለያየ…

የኮሮና ወረርሽኝ እና የዓለማቀፉ ኢኮኖሚ መጻኢ እጣ፡ እንደምን እንዳን?

የኮቪድ 19 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለም የምጣኔ ሀብት ላይ መናጋት ፈጥሯል። የቫይረሱ ስርጭት ቀጥሎ ዓለም ከዚህ ሕማሟ በቶሎ የማትላቀቅ ከሆነም፣ የክስተቱ ጠባሳ ከሦስት ዓመታት በላይ ዘልቆ በኢኮኖሚው ላይ እንደሚታይ ባለሞያዎች እያሳሰቡ ነው። ይህን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ግብርና ላይ ትኩረቷን ብታደርግ ይበጃል…

ወረርሽኙ ጥላ ያጠላበት ምጣኔ ሀብትና የሚጠበቁ የመንግሥት እርምጃዎች

ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ እንደ ጣልያን መዘናጋት የሚያስከፍለውን ዋጋ፣ እንደ ደቡብ ኮርያ በማስተዋል የሚወሰድ እርምጃ የሚኖረውን ጥቅም ከዚህ ቀደም አስቃኝተዋል። አሁን ደግሞ ቫይረሱ ስር የሰደደ ጫና እንዳያሳደርና ኢኮኖሚውን የከፋ ውድቀት ውስጥ እንዳይከት፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ በኩል የፖሊሲ ቅኝች ማደረግ…

አገርን የመዝጋት ዘመቻ – ለዓለም የቀረበ አስጨናቂ ፈተና

የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ መከሰትና ስርጭትን ተከትሎ፣ አገራት በሮቻቸውን ዘግተዋል። የሰዎች እንቅስቃሴ የተገታ ሲሆን አብሮት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያው እንቅስቃሴም ወደመቆሙ ተቃርቧል። ታደሰ ጥላዬ ይህን ነጥብ በማንሳት፣ በቫይረሱ ምክንያት ዛሬ የተገታው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ነገ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ባይ ናቸው። እናም አውሮፓና አሜሪካ…

ጅምላ ጨራሹ ኮቪድ19 እና የተፈጥሮ ሀብት!

ኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ከወራት ቀደም ብሎ ምድርን ከተቀላቀለ ጀምሮ ለሰው ልጅ እረፍትና ሰላም ነስቶ ይገኛል። ቫይረሱ በቻይና ዉሃን ግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ከእንስሳ ወደ ሰው ልጅ ተላልፎ ነው የሚል ዘገባ ሲሰማ የቆየ ሲሆን፣ ፕሮፌሰር መንግሥቱ ውቤ (ዶ/ር) እንደውም የተፈጥሮ…

የተንከባካቢዋ ማስታወሻ

በኮቪድ 19 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሰዎች በቤት የመቀመጥ አዲስ ልምድ እያዳበሩ ነው። ይህ ነገር በሴቶች ላይ የቤት ውስጥ ጥቃት እንዲበረታ እንዳደረገ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙኀን የሚዘገቡ ዜናዎች እየጠቆሙ ነው። በኢትዮጵያ ምንም እንኳ ሴቶች ራሳቸውን ‹ገመና ሸፋኝ› አድርገው የደረሰባቸውን የመደበቅ…

ኮቪድ19 ለመዋጋት – የደቡብ ኮርያን ዳና መከተል

ዓለም አሁን ያለችበት ሁኔታ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሜሪካን በግንባር ቀደምትነት አስቀምጦ የዓለምን ሕዝብ አሁንም ድረስ እያሸበረና እያመሰ ይገኛል። በየቀኑ በቫይረስ እንደተያዙ የተረጋገጡ አሜሪካኖች ቁጥር ከቀዳሚው ቀን በበለጠ ቁጥር ከፍ ማለቱን ሳያቋርጥ ቀጥሎበታል። በአግባቡ መቆጣጠር ካልተቻለ አሁንም የስርጭት ፍጥነቱ አሳሳቢ እንደሆነ…

ኮሮናን ተደግፈው ፎቶ የሚነሱት…!

በአገራችንና ዓለም ዙሪያ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የጤና ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች ኮሮና ቫይረስ ያመጣውን አደገኛ ችግር ለመፋለምና የሰውን ሕይወት (የሰውን ዘርም ሊሆን ይችላል) ለመታደግ ሌት ተቀን ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ስለ እምነት (ሐይማኖት) በጥልቀት…

ከአዲሷ የኮቪድ19 ማእከል ጣሊያን፤ ዓለም እንዲማርበት

  ኮቪድ19 ዓለምን ማስጨነቅ ከጀመረ የወራት እድሜን አስቆጥሯል። በዚህ ጊዜ ውስጥም የዓለም አገራት ቫይረሱን መለየትና የሰዎችን እንቅስቃሴ መገደብ ቀድመው ተፈጻሚ ሊሆኑ እንደሚገባ ተረድተዋል። ይህም በአግባቡ ጥርት ባለ መንገድ ሊተገበር የሚገባ ነው። እርምጃዎች በተገቢው መንገድና በትኩረት ተግባራዊ አለመደረጋቸው፣ የሕዝብ እንዲሁም የመንግሥት…

የውጭ ግንኙነት ድሽቀት!

አባይና የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት፣ አደራድሩን ሸምግሉን እያለች የተለያዩ አገራት በሮችን የምታንኳኳው ግብጽ፣ ጥቂት የማይባሉ በሮች ተከፍተውላታል። አሜሪካም በአደራዳሪነት ሥም ገብታ ወደ ግብጽ ማድላቷና ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ስትሞክር በጉልህ ታይቷክ። ግዛቸው አበበ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ብቻ ሳይሆን አረብ አገራት…

የግብፅን ፈላጭ ቆራጭ ሥነ-አመክንዮ በጋራ ክንድ እንመክት!

አሁን ላይ የዓለም አገራት ሁሉ ትኩረት ዓለም አቀፍ ስጋት በሆነው ኮቪድ19 ወይም ኮሮና ቫይረስ ላይ ሆኗል። ሌሎች አንገብጋቢና አወዛጋቢ ጉዳዮች በይደር የተቀመጡ ይመስላል። ዓለማየሁ ሞገስ በበኩላቸው ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች መዘንጋት እንደሌለባቸው ለማሳሰብ፣ ይልቁንም በአባይ ጉዳይና በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያ ሕዝብ…

የአፓርታይድ መንፈስ በኢትዮጵያ….. ?!?!

በኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ቀጥታ ስርጭት ይተላለፍ በነበረ ስብሰባ፣ አንድ አስተያየት ሰጪ ባደረገችው ንግግር አልፎም በሐሳቧ ብዙዎች ደንግጠው ነበር። ጉዳዩም የብዙኀኑ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ግዛቸው አበበ በበኩላቸው፣ ከዚህች ሴት ሐሳብ ባልተናነሰ አልፎም በባሰ መልኩ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እንዳሉ አንስተዋል። እንደውም ከኢትዮጵያ…

የዓለም ጫና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና መጪው ምርጫ ላይ

ምርጫ ቦርድ ምርጫው የሚካሔደው ነሐሴ መጨረሻ ላይ እንደሚሆን ካሳወቀ ጊዜ ጀምሮ ፖለቲካ ፓርቲዎች በሚወዳደሩባቸው ቦታዎች እንዲሁም በአገሪቱ ዙሪያ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምረዋል። የአገር ውስጥ ጉዳዮች የምርጫውን ውጤት ለመወሰን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ሁሉ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችም ከዚህ ያነሰ የማይባል ሚና ይኖራቸዋል።…

ይድረስ ለብርቱካን ሚደቅሳ!

የኢትዮጵያ የ2012 አገራዊ ምርጫ ቀኑ ተቆርጦ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተጠበቀ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ፣ የታዩ የተለያዩ ለውጦችና መሻሻሎችም ይህን ምርጫ ፍትሐዊ ይሆናል ተብሎ እንዲጠበቅ አድርጎታል። ከዚህም ለውጥ አንደኛው ብርቱካን ሚደቅሳ የቦርዱ ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸው ነው። ግዛቸው…

This site is protected by wp-copyrightpro.com