መዝገብ

Category: ሰሞነኛ

የ”መስበር” እና የ“መሰበር“ ነገር

ከሰሞኑ አዲስ አበባ በተለይም ደግሞ መስቀል አደባባይ በሳምንት ልዮነት ኹለት ታላላቅ በዓላት ሲካሔዱበት ከተማዋም እንደየበዓላቱ ስታሸበርቅ አሳልፋለች። መስከረም 24/2012 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ዐይነ ግቡ የሆነ ትዕይንት የታጀበ እና ለቁጥር በሚያዳግት ታዳሚ የኢሬቻ በዓል ተከብሯል። በዚህ ክብረ በዓል ላይ ታዲያ…

ሰሞነ ኢሬቻ

የክረምቱ የጨለማው ጊዜ አብቅቷል፤ ወደ ብርሃናማው ወራት ተሸጋግረናል ይህም የሆነው ደግሞ ‹‹ዋቃ›› በአንተ ነው እና ምስጋና ይገባሃል የሚባልበት በዓል ነው ኢሬቻ። በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ አዲሱ ዓመት በጀመረበት በመጀመሪያው ወርሃ መስከረም ከመስቀል በዓል አንድ ሳምንትን ተሻግሮ የሚከበር በዓልም ነው። ታዲያ በዚህ…

ውል በማሰር የሚጀምረው አዲሱ የትምህርት ዓመት

በመላው ኢትዮጵያ በ2011 የመሰናዶ ትምህርታቸውን አጠናቀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በ2012 ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች ከወትሮው በተለየ ተቋማት አዲስ ገቢ ተማሪዎቻቸውን ከአንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ ባለፈ ከሚኖሩበት አካባቢ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት በኩል የፈረሙትን ውል ይዘው እንዲመጡ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ጉዳዩ እንዲህ…

የከተማዋ ታክሲዎች ነገር እንዴት ሰነበተ?

ባሳለፍነው ሳምንት በማኅበራዊ ሚዲያዎች የመነጋገሪያ እንዲያውም ላቅ ብሎም በርካታ እንቅስቃሴዎች እና የድጋፍ ድምጾችም በዋናነት በትዊተር ሲደመጡ ነበር። ጉዳዩ ደግሞ ማክሰኞ፣ መስከረም 6/2012 አዲስ አበባ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ አገልግሎትን በተመለከተ አዲስ መመሪያ ይዞ ብቅ ማለቱ ነበር። ቢሮ ኀላፊው ሰለሞን…

በበዓላት የታጀበችው ጳጉሜን

ኢትዮጵያን ከዓለም የተለየች ከሚያደርጓት እሴቶች አንዱ በሆነው የቀን መቁጠርያ ውስጥ ከሳምንት ባነሱ ቀናት የተዋቀረች አንዲት ወር አለች፤ ጳጉሜን። በወርሃ ጳጉሜን መጪው አዲስ ዓመት ለመቀበል ሽርጉዱ የሚደምቅበት፣ ከመንግሥት እስከ ተርታው ሕዝብ ድረስ የአከባበሩ ሁኔታ ይለያይ እንጂ ዝግጅቱ በሚገባ አለ። ከቅርብ ዓመታት…

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በዚህ ሰሞን

በዚህ ሰሞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቴን እና ህልውናዬን የሚፈታተን አንድ ጉዳይ ገጥሞኛል ስትል አስታውቃለች። ምክንያቱ ደግሞ ቀሲስ በላይ መኮንን አማካኝነት በኦሮምኛ ካልተቀደሰ ምኑን ፀሎታችን መንግሥተ ሰማያት ገባ ዓይነት አመክንዮ ያለው እና አዲስ ስርዓት ኦሮምኛን ማዕከል ያደረገ በኢትጵያ ኦርቶዶክስ…

የኹለቱ ደብዳቢ ፖሊሶች ጉዳይ

ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች የብዙዎችን ቀልብ የሳበ፣ ያወያየና ያናደደ በኋላም ውጤት ያመጣ አንድ የቪዲዮ ምስል ተሰራጭቶ ነበር። ምስሉ በአዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ሰኞ፣ ነሐሴ 20 ኹለት የፖሊስ ደንብ ልብስ የለበሱ አባለት – አንዱ ጠብ…

የአዲሱ የትምህርትና ሥልጣና ፍኖተ ካርታ ጉዳይ

ትምህርት ሚኒስቴር ረቡዕ፣ ነሐሴ 15 ከዚህ ቀደም ለበርካታ ዓመታት ሲተገበር የነበረውን 8-2-2 የትምህርት መዋቅርን በማስተካከል 6-2-4 በሚል እንዲቀየር መወሰኑን በይፋ ማስታወቁን ተከትሎ የሰሞኑ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል። በዚህ ትምህርት መዋቅር መሰረት እስከ 8ኛ ክፍል የነበረው የመጀመሪያ ሳይክል በ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና…

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት አነጋገረ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 7 በይፋ የተለቀቀው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መደበኛ የሆኑትንም ሆነ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀንን ስቧል፤ የብዙዎችም መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል። በአንድ በኩል በአገር ዐቀፍ ደረጃ 645 ነጥብ በማስመዝገብ ብሩክ ዘውዱ የተባለ በባሕር ዳር የአየለች ደገፉ (የታዋቂው አትሌት…

የመአዛ አሸናፊ አነጋጋሪ መሆን

ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ ከፍትሕ ማሻሻያዎች እና ችግሮች ዙሪያ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ለተነሳ ጥያቄ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መአዛ አሸናፊ ሰጡ የተባለው ምላሽ ሰሞኑን በሰፊው የማኅበራዊ ትስስር መድረኮችን አጨናንቆ ከርሟል፤ በአንዳንድ መደበኛ መገናኛ ብዙኀንም ላይ የውይይት ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ…

የችግኝ ተከላ ዘመቻ ወጎች

ሰኞ፣ ሐምሌ 22 በአገር ዐቀፍ ደረጃ የታቀደውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጠራው “የአረንጓዴ አሻራ” ቀን በተሳካ ሁኔታ መካሔዱ በርካታ ማኅበራዊም ሆነ መደበኛ የመገናኛ ብዙኀንን ቀልብ ስቦ አልፏል። በአንድ ቀን 200 ሚሊየን ችግኞች ሊተከሉበት ከታሰበለት የችግኝ ተከላ ዘመቻ ቀን በኋላም…

የኮማድ ፖስቱ ጉዳይ በደቡብ ክልል

ከሰኞ፣ ሐምሌ 15 ጀምሮ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሁሉም ዞኖች፣ የሐዋሳ አስተዳደርና ልዩ ወረዳዎች የጸጥታ ሥራው በፌደራል ጸጥታ ኀይል ቁጥጥር ሥር ሆኖ በጊዜያዊ ኮማድ ፖስት እንዲመራ መወሰኑ ክልሉ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወቃል። ደቡብ ክልልን በኮማንድ ፖስት ስር እንዲሆን የዳረገው…

የርዕሰ መስተዳድሩ መታጨት ጉዳይ

በአማራ ብሔራዊ ክልል ሰኔ 15 የተካሔደውን “መፈንቅለ መንግሥት” ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥትና የፓርቲው የአመራር ቦታዎች ክፍተት መፈጠራቸው ይታወቃል። ይህንን ክፍተት ለመሙላት የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አካሒዶ ሰኞ፣ ሐምሌ 8 ተመስገን ጥሩነህን ዕጩ ርዕሰ መስተዳድር እንዲሁም ዩሐንስ ቧያለውን…

“ካልቆሙ እርምጃ ውሰዱባቸው” እውነት ይሆን?

ከሳምንታት በፊት የአዲስ አበባ አስተዳደር እኔ ከሰጠሁት እውቅና ባለኹለት እግር ሞተር ተሽከርካሪዎች ከሰኔ 30/2011 ጀምሮ በአውራ ጎዳናዎቼም ሆነ በውስጥ ለውስጥ መንገዶቼ ላይ ውር ውር ማለት የተከለከለ ነው ሲል የእግድ ትዕዛዝን ማውጣቱን ተከትሎ የዛ ሰሞን መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል። ሞተረኞቹም “ግብታዊ” ያሉትን…

“. . . ማስረጃ ሳንይዝ አናስርም” የት ገባ?

ሰኔ 15 የተሞከረውንና የአምስት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሕይወት የነጠቀውን በአማራ ክልል የተካሔደውን “መፈንቅለ መንግሥት” ተከትሎ በተለይ በአማራ፣ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ መንግሥት ጠርጥሪያቸዋለሁ ያላቸውን ግለሰቦች በጅምላ ማሰሩን በተመለከተ ተቃራኒ ሐሳቦችና አቋሞችን በዜጎችም በፖለቲከኞችም ዘንድ አሰናዝሯል። የጅምላ እስራቱ በሕጋዊነት ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ…

“በሬ ካራጁ. . .”

ቅዳሜ፣ ሰኔ 15 አመሻሽ ላይ የማኅበራዊ ትስስር አውታሮች ላይ በሰፊው የመወያያ ርዕስ ሆኖ የወጣው ከፍተኛ የአማራ ክልል መንግሥት ባለሥልጣናት እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ በጥይት ተመተው መቁሰላቸውን በተመለከተ ሲሆን አንዳንዶቹም የሰዎቹን ፎቶዎች በማስደገፍ ጭምር ወሬውን አራግበውታል። ሌሎች በበኩላቸው እከሌና እከሌ ላይ አንድ…

የኢንተርኔቱን ባልቦላ ማን አጠፋው?

ከሰኔ 3/2011 ጀምሮ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የኢንተርኔት አገልግሎት በመላው ኢትዮጵያ በከፊልና ሙሉ ለሙሉ የውሃ ሽታ ሆኖ መክረሙ ከፍተኛ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል። ብዙዎቹ ተቋማት የአገልግሎት መስተጓጎል ያጋጠማቸው ሲሆን በተለይ በኢንትርኔት ላይ ጥገኛ የሆኑት የንግድ ተቋማት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው ካሰሟቸው…

እመጫት ተማሪዎች

ከሰኞ፣ ሰኔ 3 ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ እየተሰጠ የሚገኘው የ10ኛ፣ 12ኛ እና 8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዚህ ቀደም ከተሰጡት ፈተናዎች ልዩ ትኩረት አግኝቷል። የዘንድሮውን ብሔራዊ ፈተና ከከዚህ ቀደሞቹ የተለየ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል በተከታታይ ቀናት በኹለት ሳምንታት ውስጥ እንዲሰጥ መደረጉ አንዱ ከፍተኛ…

ኢሳት እና ኢትዮ 360°

ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ያዝ ለቀቅ እያለ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች መከራከሪያ ሆኖ የሰነበተው በኢሳት ጋዜጠኞች መካከል እንዲሁም በጋዜጠኞቹና በቦርዱ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ሲሆን በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል። የተባረሩትና ራሳቸውን ያገለሉ ጋዜጠኞች በኅብረት ኢትዮ 3600 የሚባል የፌስቡክና የዩቲዩብ ሚዲያ መጀመራቸውን በዘመቻ…

የግንቦት 20 በዓል ‘ይከበር፣ አይከበር’ ንትርክ

ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር ገፆች በከፍተኛ ደረጃ ቃላት ያሰናዘረው የግንቦት 20 መከበር ‘ይገባዋል፣ አይገባውም’ የሚለው ተቃርኖዊ ሙግት ነበር። መከበር የለበትም ብለው ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ ከነበሩት መካከል፣ ግንቦት 20 የድል ቀን ሆኖ ለመከበር ሁሉንም ያካተተ የደስታ ቀን መሆን ይገባዋል በማለት ባሏን ያጣች…

‘ገበታ ለሸገር’

ሰሞኑን ማኅበራዊ የትስስር ገፆችን ያጨናነቀውንና የመወያያ ብሎም የንትርክ መድረክ ሆኖ የከረመው የ‘ገበታ ለሸገር’ የእራት ድግስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርቡ ይፋ ያደረጉትን የአዲስ አበባ ወንዞችና ዳርቻዎቸችን የማልማት ሥራ ዕውን ለማድረግ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ መግለፃቸው ተከትሎ ጽሕፈት ቤታቸው ‘ገበታ…

የጌታቸው አሰፋ ጉዳይ

ባለፈው ሳምንት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለቀድሞ የብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ ዋና ኃለፊ ጌታቸው አሰፋ የፍርድ ቤት መጥሪያ ካወጣባቸው ዕለት ጀምሮ ጉዳዩ በማኅበራዊ ትስስር አውታሮች ከፍተኛ የመነጋገሪያ ብቻ ሳይሆን የመነታረኪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል። በአንድ በኩል ማንኛውም ተጠርታሪ ፍርድ ቤት የመቅረብና ፍትሕ…

‘ብሩህ ተስፋ ለሚታየው ልባም’

ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በተለይም በፌስቡክ በከፍተኛ ደረጃ መነጋገሪያ ከሆኑትና የብዙዎችን ቀልብ ከሳቡት መካከል የአንበሳ ቢራን ወደ ገበያ መግባት ተከትሎ የተለቀቀው ʻብሩህ ተስፋ ለሚታየው ልባምʼ የተባለው ማስታወቂ ነው። ብዙዎችን በኹለት ጎራ አሰልፎ አነታርኳልና የቃላት ጦርነት ውስጥም ከትቷል። አንዳንዶች ማስታወቂያው በከፍተኛ…

የአማራ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ

ከሰሞኑ በበርካታ የማኅበራዊ ድረ ገጾች መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል። በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ታቦር፣ ጎንደር፣ መርአዊ እና ሌሎች ከተሞች በርካታ ሕዝባዊ ሰልፎችን አስተናግደዋል። ሰልፎቹ ላይ “በአማራ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ይቁም!”፣ “መንግሥት የዜጎችን…

የቡርቃ ዝምታ መንታ ትርክቶች

ባሳለፍነው እሁድ ሚያዝያ 13፣ 2011 የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝቦችን ትስስር ለማጠናከር በሚል ዓላማ በተዘጋጀ መድረክ ላይ በቅርቡ አለሙ ስሜን በመተካት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አዲሱ አረጋ የሰጡት አስተያየት ሰሞኑን መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። የአማራ እና ኦሮሚያ…

የምኒልክ ቤተ መንግሥት!

ከሰሞኑ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን አውታሮች መከራከሪያ ሆነው ከሰነበቱትና የአሜሪካን ኤምባሲም ካስቆጡት መካከል በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚንስትሩ መቀመጫ ሆኖ የሚገለግለው የምኒልክ ቤተ መንግሥት ይገኝበታል። የነገሩ መነሻ የኋይት ሀውስ አማካሪዋና የትራምፕ ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ ጉብኝት ሲሆን አማካሪዋ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር…

በቁጥጥር ስር ዋለች!

አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል ተጠርጥራ በቻይና እስር ቤት የምተገኘው ኢትጵያዊቷ ናዝራዊት አበራ፣ በሀገረ ቻይና ይህ መሰሉ ወንጀል አስከፊ ፍርድን ከማስከተሉ ጋር ተያይዞ የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ የኢትጵያ መንግሥት ነገሩን በዲፕሎማሲዊ መንገድ እንዲፈታው ከብዙዎች ሲጠየቅ መሰንበቱ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርና የፌደራሉ…

ብርጋዴር ጀነራሉ ከስልጣን ተነሱ!

ከጥቅምት 2011 ጀምሮ ያለፉትን አምስት ወራት ገደማ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአስተዳርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ብርጋዴር ጄነራል ከማል ገልቹ ሰኞ መጋቢት 23 በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ለማ መገርሳ ፊርማ ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ቀድሞም ቢሆን ይህ እንደሚፈጠር…

4 ሚሊዮን አይመጥነንም!?

2.7 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃይ የያዘችው ኢትዮጵያ ለዜጎች መጀመሪያ የዕለት ደራሽ እርዳታ ለማቅረብ ሲያልፍም በዘላቂነት ለማቋቋም የመንግሥት አቅም ብቻ የሚችል ባለመሆኑ ሁሉም እንዲረዳ ጥሪ አቅርባለች። 90 ሺሕ ተፈናቃዮች እንዳሉት ያሳወቀው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትም የእርዳታ ጥሪ በማቅረቡ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉለት…

ተራዝሟል!

አራተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ በተያዘለት ጊዜ ይካሔድ አይካሔድ የሚለው በርካቶችን ጎራ ለይተው እንዲከራከሩ ሲያደርጉ ከነበሩ አገራዊ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ነው። ቆጠራው ቀደም ብሎ በወጣለት መርሀ ግብር መሰረት ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 30 ይካሔዳል መባሉ ይታወሳል። ይሁንና አሁን ላይ በኢትዮጵያ ካለው…

This site is protected by wp-copyrightpro.com