መዝገብ

Author: በለጠ ሙሉጌታ

የ430 ተሽከርካሪዎች የግዢ ጨረታ ታገደ

የመንግሥት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚውሉ 430 ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ወጥቶ የነበረው ጨረታ፣ በላይ አብ ሞተርስ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ታገደ። በጨረታው ሰነድ ላይ የሰፈረው የውጪ አገር ተጫራቾች ጂቡቲ ወደብ ድረስ ተሽከርካሪዎቹን ለሚያጓጉዙበት የትራንፖርት ወጪ…

ላለፉት ኹለት ዓመታት በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው አልሚዎች ድጋፍ ሊሰጣቸው ነው

ባለፉት ኹለት ዓመታት በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው አልሚዎች መንግሥት ድጎማ ለማድረግ እያስጠና ያለው ጥናት፣ በቀጣይ ኹለት ሳምንታት ተጠናቆ ወደ ተግባር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። በ2010 እና በ2011 በተለያዩ ዓመታት በተፈጠሩ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ጉዳት የደረሰባቸው ባለሀብቶች የድጎማው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ…

በቦሌ አየር ማረፊያ የሚደረገው የኮቪድ19 ምርመራ አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል

በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ ለኮሮና ቫይረስ የሚደረገው ምርመራ አጥጋቢ አለመሆኑን በአየር መንገዱ አገልግሎት የሚያገኙ ተጓዦች ገለፁ። ሥማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት የመጡ ተጓዦች ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ በአየር መንገዱ የሙቀት ምርመራ ለማከናወን ረዥም ሰልፍ ሲጠባበቁ ከቆዩ…

ከጨርቃ ጨርቅ ምርቶች ከፍተኛ የተባለ ትርፍ ተገኘ

የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዘርፉ በስምንት ወራት ብቻ 129 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ። ገቢው የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች፣ ክር እና ባህላዊ አልባሳትን ወደ ውጪ አገራት በመላክ የተገኘ ሲሆን፣ ለገቢው መጨመር በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ አዳዲስ አምራቾች ምርት…

በሰዎች በመነገድ ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች አዲስ አበባ ተያዙ

በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች በዓለም ዐቀፉ የወንጀለኞች አዳኝ የፖሊስ ግብረ ኃይል (ኢንተርፖል) እና በአውሮፓ አገራት በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ ኹለት ኤርትራውያን እንዲሁም አራት ኢትዮጵያውያን አጋሮቻቸው አዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎቹ ኪዳኔ ዘካሪያስ እና…

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎቼ እየታሰሩብኝ ነው አለ

በመመሥረት ላይ የሚገኘው የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ እየታሰሩበት እና በምሥረታ እንቅስቃሴው ላይ በመንግሥት ጫና እየተደረገበት መሆኑን ገለፀ። ፓርቲው በድሬዳዋ ሳተናው የወጣቶች ማኅበር በሚል ሲያደርግ ከነበረው እንቅስቃሴ የተወለደ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የመንግሥት አካላት የፓርቲውን አባላት እና ደጋፊዎች በማሰር…

በነቀምቴ ከተማ በግማሽ ቢሊዮን ዶላር አዲስ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው

ኢንተር ኮላር ኮንሰልቲንግ ከስፔን አገር ከመጡ አልሚዎች እና ከኦሮሚያ ክልል ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በ500 ሚሊዮን ዶላር በምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ አዲስ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊመሰረት ነው። ኢንዱስትሪ ፓርኩ የግብርና ምርቶችን በማምረት እና ዕሴት በመጨመር ለውጪ እና ለአገር ውስጥ…

ክልሎች ማዳበሪያ በወቅቱ ባለመድረሱ ምርት እንዳይቀንስ ሰግተዋል

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ለ2012/13 የምርት ዘመን የሚያገለግል ማዳበሪያ በሚፈለገው መጠን ወደ ክልሉ እየተጓጓዘ አለመሆኑ ስጋት ላይ ጥሎኛል ሲል፣ የደቡብ ክልል በበኩሉ ማዳበሪያ በወቅቱ እየደረሰለት አለመሆኑን ገልፆ የበልግ ወቅት መድረሱን ተከትሎ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብሏል። የአማራ ክልል…

ኮሮና ቫይረስ የህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት እቅድ እየተፈታተነ ነው

የኮሮና ቫይረስ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በተያዘለት ዕቅድ መሰረት እንዳይከናወን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ተገለፀ። በህዳሴ ግድብ የብረታ ብረት ሥራዎች የሚያከናውነው ሲኖ ሀይድሮ የተባለ የቻይና ኮንትራክተር ኮሮና ቫይረስ በተከሰተባት ዉሃን ግዛት ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ፣ ከቦታው ባለሙያዎችን እና የግንባታ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ…

ለለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ አዲስ የትግበራ እቅድ ተዘጋጀ

ሥራ አቁሞ የሚገኘው የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ማውጫን ወደ ሥራ የሚመልስ እቅድ በጥናት እንዲሁም በድርድር ተደግፎ መዘጋጀቱን ሜድሮክ ጎልድ ይፋ አደረገ። ሜድሮክ ጎልድ ይህን ያስታወቀው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ ለአልሚዎች እንቅፋት የሆኑ አሰራሮችን በማስወገድ አዲስ ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ ለመተግበር የካቲት 6/2012 ኢሊሌ…

በስድስት ወር ያልቃሉ የተባሉት የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ግንባታ አልተጀመረም

ከፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ ኅዳር/2012 ተጀምሮ በስድስት ወር ለመጨረስ ታስቦ፣ ከተቋራጮች ጋር ውል ቢታሰርም፣ ከሚገነቡት 12 ፕሮጀክቶች መካከል የስምንቱ ግንባታ እስከ አሁን አልተጀመረም። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ12 ገጠራማ እና ከዋና የኤሌክትሪክ መስመሮች ርቀው የሚገኙ ከተሞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ…

የኢንዱስትሪ ፓርኮች የወጪ ንግድ በ42 ሚሊዮን ዶላር አደገ

አብዛኛዎቹ ባለሀብቶች በጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ ውጤቶች ላይ የተሰማሩ ናቸው። የኢንዱስትሪያል ፓርኮች የስድስት ወራት የወጪ ንግድ ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የ42 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አስመዘገበ። ፓርኮቹ በሳለፍነው 2011 ግማሽ ዓመት 48 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ወደ…

የደቡብ ክልል የማዳበሪያ እዳ 5 ቢሊዮን ብር ደረሰ

በክልሉ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ እስከ 10 ቀን ይዘገያል በደቡብ ክልል ለአርሶ አደሮች የሚሰራጭ የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ የክልሉ መንግሥት ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ የወሰደው ብድር በወቅቱ ሳይከፈል እየተጠራቀመ ሲሆን፣ እስከተያዘው ወር ድረስም የብድር መጠኑ አምስት ቢሊዮን ብር መሻገሩ ታወቀ።…

የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር የኃይል መስመር ዝርፊያ ተፈፀመበት

አገልግሎቱ ወደ መደበኛ ሥራው መመለሱ ተገልጿል የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር መስመሮች ላይ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ መስመሮች ዝርፊያ ምክንያት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሎ መቆየቱን አስታወቀ። በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በተፈፀመው ስርቆት ምክንያት በአገልገሎት ላይ መቆራረጥ የተከሰተ ሲሆን፣ በተለይም ከቃሊቲ እስከ ምኒልክ…

በድሬዳዋ የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎች ቅሬታ አነሱ

በከተማው 20ሺሕ ቤት ፈላጊዎች አሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በ 2012 የበጀት አመት ይተላለፋሉ ከተባሉት ሁለት ሺህ ቤቶች ውስጥ 353ቱን ብቻ መስተላለፉ ለአመታት ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ ከ ስድስት ሺህ በላይ ነዋሪዎቹን አስቆጥቷል። በከተማ አስተዳደሩ ከ 2008 ጀምሮ የቤት ባለቤት ለመሆን ከ…

ሕገወጥ ምንዛሬን ሕጋዊ ለማድረግ አይ ኤም ኤፍ እና ብሔራዊ ባንክ ጥናት ሊያደርጉ ነው

በሕገ ወጥ መንገድ በውጭ ምንዛሬ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መንዛሪዎችን ሕጋዊ በሆነ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ፣ ከፊታችን ሰኞ የካቲት 16/2012 ጀምሮ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ እና ብሔራዊ ባንክ ጥናት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለፀ። ብሔራዊ ባንኩ በቀጣይ ሦስት ዓመታት…

በጋምቤላ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ የሌላቸው ኮሌጆች ትምህርት እየሰጡ ነው

በጋምቤላ ክልል 11 ኮሌጆች የከፍተኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ፍቃድ ሳይኖራቸው ተማሪዎችን በመመዝገብ የከፍተኛ ትምህርት እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ። ኮሌጆቹ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ምዘና ኤጀንሲ ከፍተኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ ሳይሰጣቸው፣ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ደረጃዎች…

በወላይታ ዞን ብሔርን መሠረት ባደረገ ጥቃት በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በወላይታ ዞን አረካ ወረዳ ብሔርን መሰረት አድረጎ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ንብረት መውደሙን በአካባቢው የሚገኙ ግለሰቦች ለአዲስ ማለዳ ገለፁ። ጥቃቱ ጥር 22/2012 የተፈፀመ ሲሆን፣ በወላይታ ዞን አረካ ወረዳ ውስጥ ስልጤ ሰፈር በተባለ እና ከስልጤ አካባቢ ለሥራ ወደ ቦታው ሄደው ኑሯቸውን እዛ…

የጥጥ ዋጋ ባለፉት ሳምንታት ከኹለት እጥፍ በላይ ጨመረ

የጥጥ ዋጋ በ20 ቀናት ውስጥ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ ማሳየቱን ባህላዊ ልብሶችን የሚያመርቱ ማኅበራት ገለፁ። አንድ ኪሎ ጥጥ ከ20 ቀናት በፊት ከ50 እስከ 70 ብር በሆነ ዋጋ ሲገዙ እንደቆዩ የገለጹት ማኅበራቱ፣ አሁን ግን ይኼው መጠን ጥጥ እስከ 230 ብር እየተሸጠ…

ገንዘቡ የት ገባ?

የምጣኔ ሀብት እስትንፋስ የሆነው የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ፍጥነትና መጠን ለገንዘብ ባለሞያዎች መነጽር ነው፤ የአንድ አገርን ኢኮኖሚ የሚያዩበት። ከቅርብ ወራቶች ወዲህ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት በግልጽ እየተስተዋለ ይገኛል። ሁኔታውን ከገንዘብ ባለሙያዎች አልፎ ‹‹ከኹለት ሺሕ ብር በላይ ከሒሳባችሁ አታወጡም›› ወደሚሉ ባንኮች…

የድንጋይ ከሰል ከውጪ ማስገባት ሊቆም ነው

በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት ለመጠቀም እና ከወጪ አገራት የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ለመተካት በመታሰቡ የድንጋይ ከሰል ከውጪ አገራት እንዳይገባ ሊደረግ ነው። ከውጪ አገራት የሚመጣውን የድንጋይ ከሰል ምርት ማስቆም ያስፈለገው፣ ኢንዱስትሪዎች በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት መጠቀም…

ብልፅግና ፓርቲ በ40 ሚሊዮን ብር አዲስ ጽሕፈት ቤት ሊገነባ ነው

ብልፅግና ፓርቲ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለሦስት ወለል የጽሕፈት ቤት ሕንፃ ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ። ግንባታው በያዝነው ዓመት ተጀምሮ በቀጣይ ኹለት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል የተባለ ሲሆን፣ የፓርቲው የዞን ኃላፊዎች እና ድጋፍ ሰጪ…

አንበሳ ጋራዥ በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደ ዴፖ ሊቀየር ነው

ከሃምሳ ዓመት በላይ የአንበሳ አውቶቡስ ማቆሚያ እና የጥገና ቦታ ሆኖ ያገለገለው ዋናው መሥሪያ ቤት፣ በአንድ ጊዜ ከ850 በላይ አውቶቡሶችን ማስተናገድ እንችልና የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ‹‹የካ ዴፖ›› በሚል ግንባታ ሊከናወንለት ነው። በሦሰት ወራት ውስጥ የሚጀመረው ይህ ግንባታ፣ ኹለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን…

በደቡብ ኦሞ የኮሌራን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የኬሚካል እጥረት አጋጥሟል

በደቡብ ኦሞ ዞን አራት ወረዳዎች ከታኅሳስ 15/2012 ጀምሮ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ውሃን ለማከም የሚያገለግሉ ኬሚካሎችን ለማግኘት እና የትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ችግር እንደገጠመው ዞኑ አስታወቀ። ወረርሽኙ በዞኑ ማሌ፣ ሀመር፣ ሰላማቦ እና ፀማይ በተሰኙ ወረዳዎች ላይ ከተከሰተ ከአንድ ወር 15 ቀን…

የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሥልጠና በመንግሥት ወጪ መደረጉ ቅሬታ አስነሳ

የመንግሥት ተንቀሳቃሽ ሂሳቦች ዝግ ሆነው ቆይተዋል ብልፅግና ፓርቲ ከመስተዳድር ጀምሮ እስከ ዞን ላሉ የቢሮ ኃላፊዎች እና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ እየሰጠ ላለው ሥልጠና የውሎ አበልን ጨምሮ ሌሎች ወጪዎችን ከመንግሥት ካዝና እንዲሸፈን መደረጉ ቅሬታ አስነሳ። ለፓርቲው አባላት እና ከክልላዊ መስተዳደር…

ብሔራዊ ባንክ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ አደረገ

ጭማሪው የሰራተኞችን የስራ ደረጃ መሰረት ባደረገ መልኩ የተደረገ ነው ብሔራዊ ባንክ ከጥር 01/2012 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ ለሠራተኞቹ አደረገ። ባንኩ ከ50 በመቶ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ ማድረጉን ለሠራተኞቹ በላከው የውስጥ ደብዳቤ ላይ…

የታኅሳስ ወር የቡና ወጪ ንግድ ቅናሽ ተመዝግቦበታል

በታኅሳስ ወር ወደ ውጪ አገራት የተላከው የቡና መጠን ቢጨምርም የተሰበሰበው ገንዘብ መጠን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ4 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱ ተገለፀ። ባሳለፍነው ወር ቡናን ወደ ውጪ አገራት በመላክ 14 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት መቻሉ የተገለፀ ሲሆን፣ የወሩ የቡና…

ንግድ እና ኢንዱስተሪ ሚኒስቴር ለ 20 ዓመታት የተገለገለበትን ሕንፃ ሊለቅ ነው

ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከልማት ባንክ በመከራየት ከ20 ዓመታት በላይ ሲገለገልበት ከነበረው እና በባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ባለ ስምንት ወለል ሕንጻ ሊለቅ እንደሆነ አስታወቀ። ባንኩ አገልግሎቶችን ለደንበኞች አመቺ በሆነ መልኩ ለመስጠት የቦታ ጥበት እንደገጠመው የገለጸ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በተለያዩ…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ8 ሺሕ በላይ አዲስ ተመራቂዎችን ሊቀጥር ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በሚገኙ ከማእከላት እስከ ወረዳ ባሉ ክፍት የሥራ ቦታዎች 8 ሺሕ 100 አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን በመቅጠር ሂደት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ። በ2010 እና 2011 ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከ56 በላይ በሚሆኑ የትምህርት መስኮች የተመረቁ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲወዳደሩ ጥሪ…

በአዲስ አበባ ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው ሼዶች ያለሥራ ቆመዋል

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው 527 ሼዶች የኤሌክትሪክ ኃይል ባለማግኘታቸው ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ አለመቻሉን አስታወቀ። የመሥሪያ ቦታዎቹ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚገኙ የገለፀው ኤጀንሲው፣ ግንባታቸው ከተጠናቀቀ ከኹለት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com