መዝገብ

Author: አዲስ ማለዳ

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ስድስት  አዳዲስ እና 16 የተሻሻሉ የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ በማቅረብ በስድስት ወራት ውስጥ 22 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ኢትዮ ቴሌኮም  በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ተቋሙ የእቅዱን 104 በመቶ ያሳካ ሲሆን፣ ገቢው ከባለፈው በጀት ዓመት…

ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩበትን 50ኛ ዓመት ሊያከብሩ ነው

ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩበትን የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ጥር 8 ቀን 2012 በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። አገራቱ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል በሚያከብሩበት ጊዜ የ50 ዓመት…

ገቢዎች ሚኒስቴር በታኅሳስ ወር 18.1 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር በታኅሳስ ወር ከ18.1 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ። በታኅሳስ ወር መሥሪያ ቤቱ 18 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ከእቅዱ በላይ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል። በተመሳሳይ ወርም ከአገር ዉስጥ ገቢ 8.59 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ ከቀረጥና ታክስ 9.5 ቢሊዮን…

በዘንድሮው ጉዞ አድዋ 60 ተጓዦች ይሳተፋሉ ተባለ

የአድዋን ድል ለመዘከር የሚከናወነው ጉዞ አድዋ ሰባተኛ ዙር ተጓዦች ጥር 9/2012 ከአዲስ አበበ በመነሳት 1 ሺሕ 10 ኪሎ ሜትሮችን በእግራቸው ለማቆራረጥ መዘጋጀታቸው ተገለፀ። ለሰባተኛ ጊዜ በሚደረገው ጉዞ አድዋ፣ ከአዲስ አባባ ተነስቶ እስከ አድዋ ድረስ 1 ሺሕ 10 ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን…

በቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

በቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በታሰሩ አመራሮች በጌታቸዉ ወድሻ (ዶ/ር) እና በጌታሁን መርጋ ላይ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ተገለፀ። አመራሮቹን ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑንና የቤንሻንጉል ክልል ምክር ቤት የፋይናንስና ገንዘብ ቋሚ…

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢን ለማሳደግ የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢን ለማሳደግና ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የማማከር ሥራ ለማከናወን ኤ ኤፍ ሜርካዶስ እና ኤ ኤፍ ኮንሰልት (AF-Mercados and AF Counsult) ከተሰኙ የስፔን ኩባንያዎች ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የ68 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱ የተካሄደው ከገቢ ማሳደግና…

የደኅንነቱ መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እርምጃ ይውሰዱ፣ ይቅርታም ይጠይቁ!

በየሳምንቱ ሰኞ ምሽት በትግራይ ቲቪ የሚተላለፈው ‹‹ኢትዮ ፎረም›› የተሰኘው ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ የሆኑት ያዬሰው ሽመልስ አርብ ታኅሳስ 24/2012 ከቦሌ ዓለማቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መቀሌ ለመጓዝ በመሰናዳት ላይ ሳሉ በፀጥታ ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበረ በማኅበራዊ ገፃቸው መግለፃቸው ይታወሳል። ይህ…

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚያሳድግ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ

የውሃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር የኃይል አቅርቦቱን በአራት እጥፍ ማሳደግ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን ገለፀ። ፍኖተ ካርታው አቅምን ያገናዘበ ፍትሐዊ የአገልግሎት ተጠቃሚነትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም አጠቃላይ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማፋጠን የሚያስችሉ አላማዎችን የያዘ ነው። ከዚህ…

አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የሼር ሽያጭ ጊዜውን እስከ የካቲት 30 አራዘመ

በምሥረታ ላይ የሚገኘው አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜውን እስከ የካቲት 30/2012 ማራዘሙን አስታወቀ። በምስረታ ላይ የሚገኘው ባንኩ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ባለሃብቶች አክሲዮን የመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን ተከትሎ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የአክሲዮን ባለቤት ለማድረግ በማሰብ የሽያጭ ጊዜውን ማራዘሙን አስታውቋል።…

ምርት ገበያ በ5 ወራት የ12 ቢሊዮን ብር ምርቶችን ለገበያ አቀረበ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በታኅሳስ ወር 5 ነጥብ 12 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 101 ሺሕ 948 ቶን ምርቶችን ማገበያየቱን ገለፀ። ምርቶቹም ሰሊጥ፣ ቡና፣ ነጭ እና ቀይ ቦሎቄ ናቸው። በታኅሳስ ወር ለግብይት ከቀረበው 52 ሺሕ 598 ቶን ሰሊጥ በ2 ነጥብ 24 ቢሊየን…

ሕብረት ባንክ የቀድሞዉን ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሽልማት አሰናበተ

ሕብረት ባንክ ባለፈዉ ቅደሜ ታኅሳስ 25/2012 የባንኩ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ታዬ ዲበኩሉን በሂልተን ሆቴል በተካሄደ ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም ማሰናበቱን አስታወቀ። በዝግጅቱ ላይ የአሁኑ የባንኩ የቦርድ ኃላፊ ዛፉ ኢየሱስ ወርቅ እና ከፍተኛ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች…

በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ ስርቆት የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ የተያዘው ግለሰብ በአስር ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ። ግለሰቡ ጥቅምት 17/2012 ከምሽቱ 2:00 አካባቢ በወላይታ ዲስትሪክት ሾኔ አገልግሎት መስጫ ማእከል አካባቢ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት ሲፈፅም በኅብረተሰቡ ጥቆማና…

10ቱ በጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት የሥራ ዕድል የተፈጠረባቸው ክልሎች

ምንጭ:የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (2018/19) ምንጭ፡ – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የ2018/19 ዓመታዊ ዘገባ ላይ፣ በበጀት ዓመቱ 110 ሺሕ 253 አዳዲስ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት መፈጠራቸውን ይገልጻል። በዚህ መሠረት ከዚህ አሃዝ ውስጥ 30 በመቶ የሚጠጋው ወይም በቁጥር 33 ሺሕ 047 የሚሆኑት…

ልማት ባንክ ባለፉት አምስት ወራት 3.9 ቢሊዮን ብር ብድር አስመለስ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብድር አሰጣጥ እና አመላለስ ስርዓቱን በማስተካከል በ 2012 በጀት ዓመት አምስት ወራት ከ 3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ የተበላሸ ብድር ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ። ልማት ባንኩ በ 2010 እና 2011 የሰጣቸው የተበላሹ ብድሮች መጠን ባንኩን ኪሳራ ውስጥ…

የዩኒቨርሲቲዎች የእርምጃ ሳምንት

በኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘን በሚገኙ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሰላማዊ መማር ማስተማር ሒደት የቅርብ ጊዜ ትውስታቸው ረዘም ሲልም እንደ ‹‹ደጉ›› ጊዜ የሚተርኩት ሆኖባቸው ከርመዋል። ከተወሰኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውጭ ኹሉም ጊቢዎች ሰላማቸው ከመደፍረሱ የተነሳ ተማሪዎች አገር አማን ብለው ለትምህርት ከወላጅ ጉያ…

የፖርቲዎች ጥምረት ወደ ጥቂት ትልልቅ አማራጮች ሊደርስ ይገባል!

በሕወሐት ይመራ የነበረው ኢሕአዴግ ከውስጥና ከውጭ በገጠመው ጫና ራሱን ከቀየረና የለውጥ ኃይል በመባል የሚታወቀው ቡድን ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንዳንዴ ተስፋ ሰጪ አንዳንዴ ደግሞ ተስፋ አስቆራጭ ሲሆን ቆይቷል። ከውጭ የገቡትም ሆኑ በአገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ያለፉትን…

ካፒታል ጋዜጣ በቀድሞው ሠራተኛው ክስ ተመሰረተበት

ተስፋዬ ጌትነት የተባሉ የቀድሞ የካፒታል ጋዜጣ ጋዜጠኛ፣ የቀድሞ ቀጣሪያቸው የአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጁን በመጣስ ደሞዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና ባገለገሉበት ቋንቋ የሥራ ልምድ ክልክሎኛል ሲሉ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሥራ ክርክር ችሎች አርብ ታኅሳስ 24/2012 ክስ መሠረቱ። ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በድርጅቱ ውስጥ…

በገና በዓል በከተማዋ የተሻለ የውሃ ስርጭት እንዲኖር ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የተሻለ የውሃ ስርጭት እንዲኖር ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ። የከርሰ ምድር እና የገጸ ምድር የውሃ መገኛዎች ከዚህ ቀደም በሚያመርቱት የውሃ መጠን ላይ ተጨማሪ 12 ሺሕ 500 ሜትር ኪዩብ ውሃ በማምረት…

ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን 95 ሚሊዮን ብር ካሳ ተከፈለው

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ወደ ሥራ ከገባ ኹለተኛ ዓመቱን ለያዘውና ከአገሪቱ ግዙፍ የባቡር ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር ለደረሰበት አደጋ ከ 95 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ መክፈሉ ተገለፀ። የካሳ ክፍያው የተፈፀመው ከስምንት ወራት በፊት ከሞጆ ወደ ጂቡቲ ይጓዝ በነበረ…

በፓዊ ወረዳ ለወጣቶች ከተሰጠ 4.4 ሚሊዮን ብድር የተመለሰው 116 ሺሕ ብር ነው

በአማራ ክልል በመተከል ዞን በፓዊ ወረዳ ለወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ከተሰራጨው 4.4 ሚሊዮን ብር ብድር ውስጥ የተመለሰው 116 ሺሕ ብር ብቻ መሆኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ። በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በወጣቶች ስፖርትና…

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ያስገነባውን የመድኃኒት ማቀዝቀዣ መጋዝን አስመረቀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የተለያዩ መድኃኒቶችን ሳይበላሹ ማቆየት የሚችሉ ማቀዝቀዣ መጋዘኖችን በመገንባት አስመረቀ። የመድኃኒት ማቀዝቀዣ ሰንሰለቱ ለፖሊዮ ክትባትና ለካንሰር የሚሆኑ መድኃኒቶችን ሳይበላሹ ለረጅም ጊዜ የማቆየት አቅም እንዳለውም ተገልጿል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ዋና ዋና የጤና ችግሮች ላይ ያተኮሩ መሠረታዊ መድኃኒቶችና…

የጃዋር መሐመድ የፓርቲ አባልነት ሳምንት

አሁን ኢትዮጵያን እያስተዳደራት የሚገኘው ለጋው የለውጥ አመራር በትረ ሥልጣኑን ከመጨበጡ አስቀድሞ በርካቶች ነፍጥ አንስተው ጫካ ገብተዋል፣ እምቢ ባይነታቸውን በሰላ ትችትና በርቱዕ አንደበት በአደባባይ ሞግተው እና ገልፀው ወደ እስር ቤት ተግዘዋል። ከፊሎቹ ደግሞ በምዕራባውያን አገራት ዘንድ ሆነው በጊዜው ሥልጣን ላይ የነበረውን…

‹‹ዋናው አገር ሰላም!›› በገና ገበያ

ሾላ ገበያ የለመደው የበዓል ሰሞን ግርግር የቀረበት ይመስላል። ድምጽን አጉልተው የሚያሰሙ የሙዚቃ ማጫወቻዎች ግን ከዓለማዊ ዘፈኑም ከመንፈሳዊ መዝሙሩም ቀላቅለው ከወዲያና ከወዲህ የበዓሉን ድባብ ሊጠሩ የሚታገሉ ይመስላሉ። እንዳልተሳካላቸው አይቶ መገመት ይቻላል። ጭር ካሉት ሱቆች መካከል አዲስ ማለዳ ወደ አንዱ አቀናች። ዓለም…

በአንድ ሳምንት ውስጥ አራት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ዋጋ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ የጉምሩክ ጣቢያዎች በተደረገ ፍተሻ፣ የአራት ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ጌጣጌጦች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና አልኮል መጠጦች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። ኅዳር 21/ 2012 በከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ሕጋዊ ዕቃ ጭኖ በመግባት ላይ ሳለ በስካኒንግ ማሽን በተደረገለት…

10ቱ የገና ዛፍ በብዛት ያስገቡ አገራት

የገና በዓልና የፈረንጆች አዲስ ዓመት ሲከበር ለበዓሉ ድምቀት ከሚሰጡት መካከል የገና ዛፍ አንደኛው ነው። አልፎም በቁመት፣ በስፋትና በዛፉ ላይ በሚሰቀሉ አምፑሎች ብዛት አገራት የገና ዛፎችን ሲያወዳድሩና ሲያነጻጽ ማየት የተለመደ ነው። ይህም የገና በዓልና የፈረንጆች አዲስ ዓመት መግቢያ ትዕይንት ነው። ታድያ…

ፖሊስ ለሕግ ይገዛ !

በተለያዩ ጊዜያት የሕዝብ መነጋገሪያ የሆኑ በፖሊሶች የተፈፀሙ የመብት ጥሰቶች እና ጭካኔዎች ቢኖሩም አጥፊዎች ግን ሕግ ፊት ቀርበው ቅጣታቸውን ሲቀበሉ አይሰማም። በዚህ [ታኅሳስ 18/2012] የአዲስ ማለዳ ዕትም ያካተትናቸው ኹለት የፖሊስ የመብት ጥሰት ዜናዎች እንደሚያሳዩት፣ በፖሊሶች ተገድለዋል የተባሉ ግለሰቦችን አስመልክቶ ፖሊስ ለቤተሰቦቻቸው…

10ቱ ከፍተኛ የውጭ ብድር ያለባቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት

በአፍሪካ ይልቁንም በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ አገራት የገንዘብ እጥረታቸውን የሚሞሉት በብድር ነው። ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው መሠረተ ልማቶችንም በብድር ሸፍነዋል። ታድያ ከአበዳሪዎች መካከል ቻይና ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ፣ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የቻይና ባለ ዕዳ ሆነዋል። ይህ ብድር ውድ ቢሆንም አፍሪካ በተለይም ምሥራቁ…

የቤተ እምነቶች ቃጠሎ

ቤተ እምነቶችን እና ምእመናን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቃሚያ እያደረጉ ከጀርባ ያዘሉትን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም መውደቅ መነሳት መቼም የቅርብ ጊዜ ትውስታ እና እየኖርንበት ያለው ነባራዊ ሃቅ ለመሆኑ ማስረጃ የሚያስፈልግ ጉዳይ አይደለም። ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከራስ ዳሽን አናት እስከ ዳሎል ረባዳ መሬት ድረስ…

ኢትዮ ቴሌኮም ለአራት ሺሕ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ ደጎመ

ኢትዮ ቴሌኮም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ13 ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ ስምንት መቶ ተማሪዎች በየወሩ ሲያቀርብ የነበረውን የኪስ ገንዘብ ድጎማ በሁሉም የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በማስፋፋት ለአራት ሺሕ ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ ሊጀምር ነው። የቴሌኮሙ የማኅበራዊ ግዴታ ክፍል ከሰው ኃይል ጋር በመተባበር ያቀናጀው ይህ…

በኹለት ወር ውስጥ አንድ ነጥብ ኹለት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ተወገደ

የመንግሥት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በታኅሳስ እና በኅዳር 2012 ውስጥ ባወጣቸዉ ጨረታዎች ከ12 የመንግሥት ተቋማት የማይፈለጉ ንብረቶችን በማስወገድ አንድ ነጥብ ኹለት ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። በታኅሳስ ወር 2012 ኹለት ጊዜ ንብረት ሲወገድ፣ አንደኛዉ ከጂማ ዩኒቨርሲቲ 161 ያገለገሉ ንብረቶች…

This site is protected by wp-copyrightpro.com