በጎንደር ዩኒቨርስቲ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተገለፀ

Views: 1509

በጎንደር ዩኒቨርስቲ ትናንት ኅዳር 28/2012 አንድ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ ህይወት ማለፉን የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስታውቋል። ትናንት ንጋት ላይ በዩኒቨርስተው የቬተርናሪ ፋርማሲ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ማሾ ዑመር በደረሰበት ጉዳት ሕክምና ሲደረግለት የቆየ ቢሆንም አመሻሽ ላይ ህይወቱ ማለፉን ዩኒቨርስቲው ባውጣው የሀዘን መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።

ጉዳቱን በማድረስ የተጠረጠሩት ከሟች የመኝታ ክፍል  ፊት ለፊት የሚገኙ ተማሪዎች ሲሆኑ ፖሊስ ሌሊቱን ሙሉ ምርመራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን የምርመራ ውጤቱም እንደ ተጠናቀቀ ዩኒቨርስቲ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ጎንደር ዩኒቨርስቲ እና የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ በተማሪ ማሾ ዑመር ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል። ለሟች ቤተሰብም መጽናናቱን እንደሚመኝ አስታውቋል።

ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከቀናት በፊት በግቢው ውስጥ ብሔርን መሰረት ያደረጉ የጥላቻ ጽሑፎች ሲሰራጩ በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና ብጥብጥ ሊያስነሱ ነበር ያላቸውን ኹለት ተማሪዎችንም እጅ ከፍንጅ በግቢው ጥበቃ አባላትና በክልሉ ልዩ ኃይል ማዋሉ የሚታወስ ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com