እናት ባንክ ከ2መቶ ሚሊዮን ብር በላይ አተረፈ

Views: 175

እናት ባንክ በ2011 በጀት ዓመት 201 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ። ባንኩ በተጠቀሰው ዓመት ከታክስ በፊት 231 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገብ እንደቻለም ለማወቅ ተችሏል። እናት ባንክ በዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ እንዳስታወቀው በ2011 በጀት ዓመት ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ42 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው።

ከዚሁ በተጨማሪ የባንኩ አጠቃላይ ወጪ በበጀት ዓመቱ በ2010 ከነበረበት የ40 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ በማሳየት 983 ሚሊዮን ብር መድረሱም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

በባለፈው የበጀት ዓመት እናት ባንክ 742 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ከወለድ ያገኘው ገቢ ሆኖ ሲመዘገብ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ከነበረበት የ489 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ለማወቅ ተችሏል። እስከ ሰኔ 30/2011 ባለው ጊዜ እናት ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መድረሱ የታወቀ ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 43 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com