ደኢሕዴን ‹‹የፓርቲውን ውሕደት አስፈላጊነት እና ቀጣይ ትግል አቅጣጫዎች ››በሚል ርዕስ በሐዋሳ ውይይት ጀመረ

Views: 186

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የፓርቲ ውሕደት አስፈላጊነት እና የቀጣይ ትግል አቅጣጫዎች በሚል ርዕስ በሐዋሳ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል። በውይይቱ ላይ የፓርቲ ውሕደት መነሻዎች እና የፓርቲ ውሕደት አስፈላጊነት፣ የፓርቲ ውሕደት ጥናት ሂደት እና አፈጻጸም ፣ የውሕደት አጃንዳ ውሳኔ እና የውሕድ ፓርቲ ምሥረታ፣ የዕቅዱ ዓላማ፣ ግቦች ዐበይት ተግባሮችን እንዲሁም ውሕደት እና የፓርቲ ምዝገባ ጊዜ፣ የምርጫ ተግባራት እና ዝግጅት፣ የፓርቲ ጉባኤ ዝግጅቶች የሚሉ ርእሶች በዋናነት የሚዳሰሱ መሆናቸው ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮፖሬሽን ዘግቧል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው እና የደኢሕዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ውይይቱን እየመሩት እየመሩ እንደሚገኙ ተገልጿል። በውይይቱ ላይ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ ደኢሕዴን ለውሕድ ፓርቲው ምሥረታ ከፍተኛ መሥዋትነት የከፈለ መሆኑንና ከኹለት አሥርት ዓመታት በላይ የሕብረ-ብሔራዊነት ተምሳሌት ሆኖ አንድነት እና ብዝኃነትን አጣምሮ እና አጣጥሞ ለመምራት የቻለ እንደሆንም አስታውቀዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com