በመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ የተመራው ልዑካን ቡድን አሜሪካ ገባ

Views: 247

በኢፌዲሪ የመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ ኅዳር 22/2012 አሜሪካ መግባቱ ተገለፀ። ልዑካን ቡድኑ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ ያለውን የመከላከያ ትብብር ማዕከል አድርጎ እንደሚወያይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ ያመላክታል። ወደ አሜሪካ ካቀናው የልዑካን ቡድን ውስጥ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሐመድ እንደተካተቱበትም ለማወቅ ተችሏል።

ለማ መገርሳ ባሳለፍነው ዓርብ ኅዳር 19/2012 ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ ስማቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ሲነሳ መቆየቱ የሚታወስ ነው። ለማ በመግለጫቸው ”መደመር” የተሰኘውን እና በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚቀነቀነውን አዲስ ሃሳብ በይፋ እንደማይቀበሉት ገልፀው፤ የፓርቲዎችንም ውህደት በተለመከተ ተቃውሞ እንዳላቸው ገልፀው ነበር።

የፓርቲዎችን ውህደት በተመለከተ ትናንት እሁድ ኅዳር 21/2012 የስምንት ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የፊርማ ስነ ስርዓት ተካሒዷል። በፊርማ ስነ ስርዓቱም ላይ የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የውህደቱ አካሔድ ሕጋዊነትን በተከተለ መልኩ እንደሚቀጥል በንግግራቸው ወቅት ገልፀዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com