አገር ዐቀፍ የኮምዩኒኬሽን እና ሕዝብ ግንኙነት ማኅበር ተመሠረተ

Views: 673

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አገር ዐቀፍ የኮምዩኒኬሽን እና ሕዝብ ግንኙነት ማኅበር ሕጋዊ የሰዉነት ፍቃድ ተሰጥቶት ሥራዉን በይፋ ጀምረ።
ማኅበሩ ባለፉት ኹለት ዓመታት የመንግሥት የኮምዩኒኬሽን ባለሞያዎችና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽን ተማሪዎች ያሳዩትን ተነሳሽነትና ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የተቋቋመ ነው። ከትምህርት ተቋም እንዲሁም ከዚህ በፊት የካበተ ልምድ ያላቸዉን፤ በሙያዉ ላይ የተሰማሩ አካላት የዚህ ማኅበር አባል በማድረግ የተሻለ አቅም ይገነባ ዘንድ የተመሠረተ እንደሆነ የማኅበሩ ፕሬዘዳንት ደምሰዉ በንቲ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በአገራችን የሚኖሩ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላም፣ የልማት እና ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ያሉ ጉድለቶችን ከመሙላት አኳያ አስተዋፅዖ ያደርጋል በሚል ተነሳሽነት፣ ቁጥራቸዉ 70 በሚደርስ ሞያተኞች የተጀመረ ነው። በቀጣይም የአባላት ቁጥር እንደሚያድግ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዘዳንት ወንድሙ ተናግረዋል።

ማኅበሩ ለትርፍ ያልተቋቋመ፤ ከሀይማኖት፣ ከዘር፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነትና አድሎ የፀዳ ሙያተኞች ያለ ልዩነት የሚሳተፉበት አገር ዐቀፍ የሙያ ማኅበር እንደሆነ ተገልጿል።

ቅጽ 2 ቁጥር 56 ኅዳር 20 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com