እርማት!

Views: 1183

 

ዛሬ ኅዳር 11/2012 በማለዳው የዜና ጊዜያችን የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔን በሚመለከት ዋልታን ምንጭ ጠቅሰን 90በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ሻፌታን መርጧል ብለን  የዘገብነው ዜና ስህተት መሆኑ አረጋግጠናል። በዚህም መሰረት የአዲስ ማለዳ ኤዲቶሪያል ቦርድ ይቅርታ ይጠይቃል።

አዲስ ማለዳ እንዳረጋገጠችው መግለጫውን የሰጡት የሐዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጥራቱ በየነ በተሳሳተ መንገድ ንግሬ ተተርጉሞብኛል ሲሉም አስታውቀዋል። አያይዘውም ትክክለኛው መረጃ በሕዝበ ውሳኔው ላይ ለመሳተፍ ከተመዘገው ሕዝብ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው ድምጽ መስጠት መቻሉን አስታውቀዋል። 90 በመቶ ደምጽ ሰጪ ሻፌታን መርጧል ተብሎ በእኔ ስም የወጣው ፍጹም ስህተት ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com