ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ ከ 21 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

Views: 877

የመንግሥት ንብረት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ያገለገሉ 44 ተሽከርካሪዎችን ሽያጭ በማከናወን ከ 21 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገባቱን አስታወቀ።
ተሸከርካሪዎቹም በተለያዩ 17 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጥያቄ መሰረት በጨረታ ለገበያ እንደቀረቡ የተገለፀ ሲሆን፣ ተሸከርካሪዎቹ ከፍተኛ የጥገና ወጪ እና የነዳጅ ፍጆታ የነበራቸው እንደሆነ ተገልጿል።

በቀጣይም በተለያዩ የግንባታ ቦታዎች ላይ የሚገኝ ከ 240ሺሕ ኪሎ ግራም በላይ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ለመሸጥ በጨረታ ሒደት ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተሰራጭቶ እንደነበር እንዲሁም ጨረታው ኅዳር 10/ 2012 እንደሚከፈት ተገልጿል።

ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚቀርብለትን መረጃ መሰረት በማድረግ የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት እና መጠን እንዲሁም ንብረት አስተዳደር ጉዳዮች ልዩ መረጃዎችን መስጠት፣ በመንግሥት ግዥ አፈጻጸምና ንብረት አወጋገድ ላይ በዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እንዲያይ ለተቋቋመው ውሳኔ ሰጪ ቦርድ፣ የጽሕፈት ቤትና የቴክኒክ ድጋፍ አገልግሎት መስጠትና የቦርዱን ውሳኔዎች ተግባራዊነት መከታተል ኀላፊነት አለው።

አግባብነት ባላቸው የብሔር ክልላዊ መንግሥታት አካላት በክልሉ የመንግሥት ግዥ አፈጻጸም ላይ እንዳይሳተፍ የታገደ እጩ ተወዳዳሪ ወይም አቅራቢ፣ በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግዥ እንዳይሳተፍ ማድረግ፤ በመንግሥት መሥራያ ቤቶች አገልግሎት ላይ ለሚውሉ ዋና ዋና ቋሚ ንብረቶች ደረጃ ማውጣት አፈጻጸሙን የመከታተል ሥልጣን አለው።

ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com