የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ሰበሰበ

Views: 365

የገቢዎች ሚኒስቴር በተያዘዉ በጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡን አሰታወቀ።

‹‹ግዴታዬ እወጣለሁ፤ መብቴን እጠይቃለሁ›› በሚለው የታክስ ንቅናቄ መርህ እና ‹‹አገሬን እወዳለሁ፤ ግዴታዬን እወጣለሁ!›› እያሉ የአገራችን ታዋቂ ድምጻውያን ባዜሙት ቀስቃሽ መልዕክት ግብር ከፋዮች ብቻ ሳይሆኑ መላው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርና ሠራተኞችም ተነሳሽነት  ባለፈዉ አንድ አመትና በ2012 በጀት አመት አራት ወራት የገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ አሰባሰቡ ማደጉን ገልጿል።

ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30  ዓመታዊው የትርፍ ግብር መክፈያ ወቅት ሲሆን በነዚህ ጊዜያት ከሚጠበቀው ገቢ አብዛኛው የሚሰበሰበው ከደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች ሲሆን በተለይ ጥቅምት ወር ከፍተኛው ገቢ የሚሰበሰብበት ወቅት ነው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም በነዚህ ወራት ከዕቅዱም፣ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅትም ጋር ሲነፃፀር ያለው ልዩነት የሚያኮራ መሆኑን ገልጿል ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com