10ቱ ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ አገራት

Views: 589

ምንጭ:ኒው ወርልድ ዌልዝ (2018)

የነፍስ ወከፍ ገቢ አንዱ የአገራትን ምድብ የሚያሳውቅ መስፈርት ነው። አገራት ያደጉና ከፍተኛ ገቢ ያላቸው፣ መካከለኛ ገቢ ያላቸው እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተብለው ነው ደረጃ የሚወጣላቸው። ለዚህ ነው የነፍስ ወከፍ ገቢ ትኩረት ተሰጥቶት አገራትም ያንን መመዘኛ መለኪያ አድርገው በየጊዜው እድገታቸውንና የደረሱበትን የሚመለከቱት። ታድያ የአገር ሀብት ሲጨምር የነፍስ ወከፍ ገቢም ከፍ ይላል፤ የነፍስ ወከፍ ገቢ ሲጨምርን የአገር ሀብት እንደዛው።

በዚህ መሠረት ከአፍሪካ አገራት ደቡብ አፍሪካ ዛሬም ሀብታሟ አፍሪካ አገር መሆኗን በ2019 የአፍሪካንን ሀብት መጠን በተመለከተ የወጣ ዘገባ ያመለክታል። ዘገባውን ያወጣው አፍርኤሽያ የተባለ ባንክ፤ በዚሁ ዘገባው አካትቶ እንደገለጸው ደቡብ አፍሪካ 649 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ሀብት ያላት አገር ስትሆን፤ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ሆና የምትከተላት ግብጽ ከግማሽ በታች የሚሆን የሀብት መጠን ይዛ ነው።

ይሁንና በነፍስ ወከፍ ገቢ የታየ እንደሆነ ሞሪሽየስ ከደቡብ አፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች። ናሚብያ እና ቦትስዋና ተከታትለው ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ደቡብ አፍሪካን ተከትለው ይገኛሉ። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ 17ኛ ደረጃ ላይ ናት። በዚህ ደረጃ ላይ የተቀመጠችውም በ650 የአሜሪካን ዶላር ነው። ኢትዮጵያ በጠቅላላው 57 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት እንዳላት ነው ሪፖርቱ የዘገበው።

ቅጽ 2 ቁጥር 53 ጥቅምት 29 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com