ቻይና ከፍተኛውን አምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን አስተዋወቀች

Views: 653

ቻይና ውስን ከሆኑ አገራት ውጪ እምብዛም ያልተለመደውን  እና ቀሪዎቹ ዓለማት ያልደረሱበትን የአምስተኛ ትውልድ የኔትወርክ ቴክኖሎጂን በዓይነቱ ከፍተኛ ተባለውን ይፋ አድርጋለች። በቻይና የሚገኙ ሦስት የኔትወርክ አገልገሎት ሰጪ ድርጅቶች በጋራ ገመድ አልባውን እና ቀጣዩን ትውልድ ቴክኖሎጂ የሆነውን 5ጂ ወይም አምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን አስተዋውቀዋል።

ቻይና ሞባይል፣ ቻይና ቴሌኮም እና ቻይና ዩኒኮም የተባሉት ኩባንያዎች በአዲስ መልክ ያስተዋወቁት የኔትወርክ ቴክኖሎጂ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚ እንደሚያደርሱም ታውቋል። በዚህም ረገድ ለ30 ጊጋ ባይት የኢንተርኔት አገልግሎት 128 የቻይና ገንዘብ(ዩዋን) ወይም 18 ዶላር እንደሚያስከፍሉ ይፋ አድርገዋል።

አዲሱ የኔትወርክ ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ በ50 የቻይና ከተሞች ተግባራዊ ሆኗል። አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ አምስተኛ ትውልድን በጥቂቱ ቢያስተዋውቁም ቻይና ቀጣዩን ትውልድ ቴክኖሎጂ ለንግድ ማቅረቧ ቀዳሚ እንደሚያደርጋት ተነግሯል።

ቻይና ከሌሎች አገራት በቀዳሚነት በርከት ያለ ቁጥር ያለው የተንቀሳቃሽ ስልክ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ያለባት አገር እንደሆነች የሚጠቀስ ሲሆን ይህም በቁጥር 850 ሚሊዮን ገደማ እንደሆነ ታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com