አዲስ አበባ እና ዋሽንግተን የእህትማማች ከተሞች ፊርማ ይፈራረማሉ

Views: 508

አዲስ አበባ እና የአሜሪካዋ ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ግንኙኑታቸውን ለማጠንከር የእህትማማች ከተሞች ስምምነት እንደሚፈራረሙ ታወቀ። ጥቅምት 29/2012 ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገቡት የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር በቆይታቸው የኹለቱን ከተሞች ወዳጅነት ላቅ ወዳለ ደረጃ የሚያደርሰውን የእህትማማች ከተሞችን ስምምነት እንደሚፈራረሙ ታውቋል።

በመጪው ቅዳሜ ከከንቲባዋ ጋር ሃምሳ የሚደርሱ ታላላቅ የንግድ ማኅበረሰቦችም አብረው ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ጉብኝት ባለፈው ግንቦት 2011 አዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከንቲባዋ አዲስ አበባን እንዲጎበኙ ያቀረቡትን ሃሳብ ተከትሎ ነው። ኢንጅነር ታከለ በጉብኝታቸው ወቅትም ኹለቱን ከተሞች በተለያዩ ዘርፎች ለማስተሳሰር ሰፊ ስራ መሰራት እንደሚገባ ከከንቲባ ቦውሰር ጋር መምከራቸወ የሚታወስ ሲሆን፤ የእህትማማች ከተሞች ፊርማን ለመፈራረም መግባባት የተደረሰውም በምክትል ከንቲባው ጉብኝት ወቅት ነበር።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com