የገናሌ ዳዋ ሶስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በኹለት ወር ውስጥ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተገለጸ

Views: 585

የገናሌ ዳዋ ቁጥር ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በኹለት ወራት ውስጥ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገልጸዋል። 451 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የኃይል ማመንጫው ግድብ ውሃ ሙሊት ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ዋና ዋና የሙከራ ስራው ተጠናቆ አፈጻጸሙ 99 በመቶ ላይ እንደሚገ|ኝ ታውቋል።

254 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት ቀሪ የሙከራ ስራው እንደተጠናቀቀ ከኹለት ወር በኋላ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። ግንባታው በ2003 የተጀመረው የገናሌ ዳዋ ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በካሳ ክፍያ ሳቢያ ለሦስት ዓመታት ስራው ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት ችግሩን በመፍታት ፕሮጀክቱን የማፋጠን ስራው እየተከናወነ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። የገናሌ ዳዋ ቁጥር ሦስት ኃይል ማመንጫ በሙሉ አቅሙ ኃይል ማመንጨት ሲጀምር የኢትዮጵያን የኃይል መጠን ወደ 4ሽሕ 514 ሜጋ ዋት ከፍ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com