መንግስት በቅርቡ 900ሽሕ ፓስፖርት ይረከባል

Views: 544

በአገር ውስጥ የሚታየውን ፓስፖርት እና የጉዞ ሰነድ እጥረት ተከትሎ መንግስት ለፈረንሳዩ ኩባንያ እንዲያትም የሰጠውን ፓስፖርት በቅርቡ እንደሚረከብ አስታወቀ።

ከፈረንሳዩ ኦቨር ቱር ከተባለ ኩባንያ ጋር 1 ሚሊዮን ፓስፖርቶችን እንዲያትም ውል በተገባው መሰረት እስካሁን 100 ሽሕ የሚሆኑትን ብቻ መንግሥት መረከቡን የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና  እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሙጂብ ጀማል አስታውቀዋል። በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን የገመገመው ኤጀንሲው፤ በተጠቀሰው ጊዜ በኤጀንሲው ያጋጠመውን የፓስፖርት እጥረት ተከትሎ አግለግሎት ጠያቂው ኅብረተሰብ ረጅም ጊዜያትን በቀጠሮ ከማሳለፉም በላይ ለብልሹ አሰራሮች እንደተጋለጠም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

የታየውን እጥረት ለመቅረፍም በቅርቡ ከሚገባው 900ሽሕ ፖስፖርት በተጨማሪ 1 ሚሊዮን ፓስፖርት ለማሳተም እና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እንደሚሰራም ጠቁመዋል። ዳይሬክተሩ አያይዘውም በአገር ውስጥ ያሉ ማተሚያ ቤቶች ፓስፖርትን ለማተም የቴክኖሎጂ ክፍተት በመኖሩ እና አዋጪም ባለመሆኑ በውጪ ኩባንያዎች ማሳተም እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com