‹‹ወደ ግጭት ቦታዎች የምልካቸው ባለሞያዎች የሉኝም›› የሰብአዊ መብት ኮሚሸን

Views: 691

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተቋማዊ ማሻሻያ በማድረግ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ብቃት ያለው ተቋምን ለመገንባት እያካሄደ ባለው ስራ አማካኝነት በቅርቡ በኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ እና በሀረሪ የተከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ቡድን ለመላክ እንደማይችል አስታወቀ።

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ግጭቶች በሚጋጥሙበት ወቅት ባለሞያዎቹን ወደየ አካባቢው የሚልከው ኮሚሽኑ ወራት በፊት አዲስ ሃላፊዎች በመሾማቸው የጀመረው የለውጥ ስራ እስኪጠናቀቅ በግጭቱ አካባቢዎች ባሉ ቅርንፎቹ አማካኝነት ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተል አስታውቋል። በተጨማሪም ስልታዊ መከታተተያ ተብለው በተለየአማረጮች ጉዳዩን እየተከታተሉ እንደሆነ የሚናገሩት ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በተለይም የሚዲ ሪፖርቶችን እና የህግ አስፈፃሚ መረጃዎችን እንደሚተቀሙ ተናግረዋል።

የተለያዩ ጠቋሚዎች ወደ ኮሚሽኑ እየመጡ መረጃ በማቀበል ላይ መሆናቸውን ተናግረው አዳዲስ ስልቶችን በመከተል የሚፈጠረውን ክፈተት ለመሙላት እና በቅርቡም የለውጥ ስራዎችን በመነጠናቀቅ ተቋሙን በሚጠበቅበት ደረጃ ላይ እንዲገኝ ለማድረግ እየተሳ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
‹‹አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ አደጋ ላይ የወደቁት መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች በተለይ በህይወት የመኖርና የአካል ደህንነት የመጠበቅ መብቶች ናቸው›› ያሉት ዳንኤል ‹‹ እየገጠመን ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት የፖለቲካ ቀውሱ ወጤት ነው›› ሲሉ ስጋታቸውን አጋርተዋል። ‹‹ህገ መንግስቱን ጨምሮ የፖለቲካ አወቃቀራችንንና አደረጃጀታችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋላጭ ያደረጉ ሁኔታዎች ካሉ መፈተሸ ይጠይቃል።››

ባሳለፍነው ሳምንት በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ ወደ ሰማኒያ የሚጠጉ ዜጎች የሰብአዊ መብት ጥሰት በህይወት የመኖር መብታቸውን የተነጠቁበት መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ፤ በኦሮሚያ ክልል ፤ ድሬዳዋ እንዲሁም ሀረር ጨምሮ ውዝግብና አመጽ የተቀላቀለበት ነውጥ እንደታየባቸውም ተለይተዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ከተከፈተበት ግዜ ወዲህ በርካታ የሰብአዊ መብት መሻሻሎች የነበሩበት ቢሆንም በሌላ በኩል ውስብስብ ተግዳሮቶችን መኖራቸው የማይካድ ፤ ነገር ግን አሁን የተከሰተው አሳዛኝ ክስተት እጅግ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ የሚያደርገው የህግ የበላይነትን መገዳደር መገለጫ አድርጎታል ሲሉም መኮሚሽነሩ የጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ለሞት ከተዳረጉ ዜጎች ውስጥ አስር የሚሆኑት ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በነበረ ግብ ግብ ህይወታቸው ሲያልፍ ሌሎች ከ60 በላይ የሚሆኑት ግን ለህልፈት የተዳረጉት እጅግ ዘግናኝ በሆነ እና ጭካኔ በተሞላበት ግፍ መሆኑን ኮመ ሽኑ አረጋግጧል።

‹‹በአደባባይ፣ በመንገድና በመኖሪያቸው አካባቢዎች በዱላ፣ በስለት በድንጋይ እንዲሁም እንዲሁም በእሳት መቃጠል ለሞት ተዳርገዋል›› ሲሉ ኮሚሽነሩ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳትና የስነ-ልቦና ጥቃት ሰለባ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን የሃይማኖት ተቋማትን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ደግሞ ሌላኛው ያልተለመደ ነገር ግን በሰፊው የተስተዋለ ክስተት ነው።

የደረሰው ቀውስና አደጋ እጅግ አሳዛኝ ከመሆን ባለፈ የህግ የበላይነት ፈተና ውስጥ የወደቀበት እና መንግስት በድርጊቱ ተሳትፎ የነበራቸው ሁሉ አጥፊዎችም በህግ ፊት ተጠያቂ አደርጋለው ማለቱ ተገቢ ተግባርና ሃላፊነት መሆኑን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገልጿል።

የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ላይ የሚሰሩ የመንግስት ተቋሞች ፓሊስ ፤ አቃቤ ህግ ፤ ፍርድ ቤት ሂደት ስራቸውን እንዲሰሩ ማስቻል አንገብጋቢ ነው ያሉት ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

‹‹የምርመራው ስራ ግዜ የሚጠይቅ በሰልትና በጥንቃቄ መሰራት ያለበት በመሆኑ የመንግስት ፍትህ አስተዳደር አካላት ስራቸውን እንዲሰሩ እድልና ግዜ መስጠት ያስፈልጋል›› ሲሉ ዳንኤል ኮሚሽኑ ስለሚካሂደው ጥናት እና ይፋ ስለሚደረግበት ወቅት አብራርተዋል። ዜጎች ያላቸውን መረጃ ለወንጀል ፍትህ አስተዳደር አካላት እንዲሁም ወደ ኮሚሽኑ በመምጣት መረጃ እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

‹‹የምርመራ ስራው በወንጀሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የነበራቸውን አካላት ተጠያቂ ማድረግ አለበት›› ሲሉ ያሳስበሉ። ‹‹ነገር ግን በምርመራ ወቅት ንጹሃን ዜጎችን አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።››

አሁን በተፈጠረው ለውጥ ከማንነት ጋር ተያይዞ እየቀረቡ ያሉ ጥያቄዎች ‹‹ይህ አካባቢ የእኔ ነው›› የሚል እንደምታን የያዘ ሌሎች ከዚህ አካባቢ ሊወጡ ይገባል በሚል አስተሳሰብ እየተፈጠረ ያለ ችግር ነው ሲሉም ስለመነሾው ነገራሉ።

በተጨማሪም በክልሎች መካከል እና በክልሎች ውስጥ ለአስተዳደር ጉዳዮች የተቀመጡ የአስተዳደር ወሰኖችን ከጎረቤት አገር ጋር እንዳለ ወሰን በመቁጠር ሌላኛው የህብረተሰብ ክፍል ከዚህ ወዲያ የእሱ ድንበር ሊመጣ ይገባል አይገባም በሚል እየተፈጠረ ያለ የአስተዳደር ድንበሮችን መለያ ድንበሮች አድርጎ በመቁጠር እየተፈጠረ ያለ የሰብአዊ መብት ቀውስ ብዙዎችን ለሞት ፤ መፈናቀልና ንብረት መውደም እየዳረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የፌደራል አወቃቀር እና አስተዳደር እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ብዝሃነት ላለባቸው አገሮች ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ በትክክለኛውና በአግባቡ ቀርጾ ስራ ላይ ማዋል ከተቻለ አማራጭ የለውም ሲሉ ዳንኤል ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ አደረጃጀት በትክክለኛው መስፈርት የተዋቀረ አስተዳደር ባለመሆኑ በተወሰነ መልክ ለሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋላጭ ያደረገ መልክ ያለው በመሆኑ ይህን መመርመር የሚሻ እንደሆነም ያሳስባሉ።

በሌላ መልክ የህግ የበላይነትን መገዳደር እንዲሁም የስርዓት አልበኝነት አዝማሚያ ለሰብአዊ መብቶች መፈራረስ በር የከፈተ ያደረገ በመሆኑ የህግ የበላይነትን ማስከበር ከመንግስት የሚጠበቅ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት የሚታመን መሆኑን ገልጸዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 52 ጥቅምት 22 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com