10ቱ በዓለማችን በትዊተር ገጽ ብዙ ተከታይ ያላቸው ዝነኞች

Views: 339

ምንጭ:ትዊት ባይንደር (2019 እ.ኤ.አ.)

በዓለማችን ላይ በስፋት አገልግሎት እየሰጡ ካሉ ማኅበራዊ መገናኛ ዓውታሮች መካከል ትዊተር የተባለው ገጽ አንደኛው ነው። ትዊተር ለዓለም የተዋወቀውና ወደ አገልግሎት የገባው በ2006 (እ.ኤ.አ.) ነበር። የገጹ ተጠቃሚ ለሚጠቀማቸው ቃላት ገደብ ያለው ቢሆንም ተጠቃሚዎቹ ግን ጥቂት አይደሉም። ተጽዕኖ ፈጣሪ የተባሉ ሰዎችም፤ ለምሳሌ እንደ አሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራንፕ፣ ለዜና ምንጭ የሚሆኑ መረጃዎችን ሳይቀር በዚህ ገጽ ላይ ሲለጥፉ (ትዊት ሲያደርጉ) ይስተዋላል።

“ትዊት ባይንደር” የተባለ አውታር በቅርቡ ባወጣው አንድ መረጃ ታድያ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸውን ዝነኛ ሰዎች ሥም ዝርዝር ከነተከታዮቻው ብዛት አስፍሯል። በዚህም መሠረት አሜሪካዊቷ ድምጻዊት ኬቲ ፔሪ ብዙ ተከታይ ያላት በመሆን አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በዐሥርቱ ዝርዝር ውስጥ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ያለው የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሲሆኑ በዝርዝሩ የተገኙ ብቸኛው የፖለቲካ ሰው ናቸው። ይሁንና ሪፖርቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ ባራክ ኦባማ ከ109 ሚሊዮን በላይ ተከታይ በማግኘታቸው ኬቲ ፔሪን ቀድመዋታል።

ከዛ ባሻገር ብዙ ተከታይ ያላቸው በአብዛኛው የጥበብ ሙያ ውስጥ ያሉ መሆናቸውን መታዘብ ይቻላል፤ ይህም ምን ያህል ተጽዕኖ መፍጠር እንደቻሉ የሚያሳይ ነው። ከዚህም ባሻገር እግር ኳስ ተጫዋቹ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ የኤለን ሾው አዘጋጇ ኤለን እንዲሁም የተለያዩ የተቀረጹ ምስሎችን ለዕይታ በማቅረብ ተመራጭ የሆነው ዩ ትዩብ በዝርዝሩ ውስጥ ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያም የትዊተር ገጽ ብዙ ተጠቃሚ ያለው ነው። በዚህም መሠረት ዶክተር ቴዎድሮስ አድኀኖም ከ413 ሺሕ በላይ ተከታይ ሲኖራቸው ጃዋር መሐመድ በ126 ሺሕ እንዲሁም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከ110 ሺሕ በላይ ተከታይ እንዳላቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ የተከታዮቻቸው ቁጥር እየጨመረ ከመጡት መካከል ደግሞ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀዳሚው ናቸው፤ ከ67 ሺሕ በላይ ተከታይ አላቸው።

ቅጽ 1 ቁጥር 52 ጥቅምት 22 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com