ሳፋሪ ኮም በኢትዮጵያ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስተወቀ

Views: 959

ግዙፉ የኬኒያ ቴሌኮም ድርጅት ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር በምታደርገው እንቅስቃሴ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው አስተወቀ።

በዘርፉ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ካሳዩት 22 ድርጅቶች በተጨማሪ ሁለት ድርጅቶችን ለማሳተፍ መንግስት ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው የጠቀሰው ሳፋሪ ኮም እስከ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በዘርፉ ላይ የማፍሰስ አቅም አለኝ ብሏል።

መንግስት በያዝነው ወር ሁለት በጋራ ለመስራት ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶችን ለመለየት በሚያወጠው ጨረታ ላይ እንደሚሳተፍ የገለፀ ሲሆን ሂደቱን የሚመራው የገንዘብ ሚኒስቴርም በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች ተመሳሳይ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጹ ይታወሳል፡፡

ከ40 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ያሉት ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው አመትም 5.1 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የሞባይል ኔትወርክ አቅም ለመገንባት አቅዷል። በአጠቃላይ የደንበኞቹን ቁጥር ከ43.6 ሚሊዮን ወደ 50.4 ሚሊዮን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ሳውቋል።

ኩባንያው የቴሌ ሥርፀትን ከ44.5 በመቶ ወደ 50.5 በመቶ፣ ገቢውን ከ36.3 ቢሊዮን ብር ወደ 45.4 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ አቅዷል። ከውጭ አገልግሎቶች የሚያገኘውን ገቢ ከ98.3 ሚሊዮን ዶላር ወደ 138.3 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግ እንዳቀደ ተገልጿል። ኩባንያው ያሉትን አከፋፋዮች ብዛት ከ168 ወደ 206፣ የቸርቻሪዎችን ቁጥር ከ167 ሺህ ወደ 242 ሺህ እንደሚያሳድግ ገልጠፆ ነበር።

ቅጽ 1 ቁጥር 52 ጥቅምት 22 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com