የሳይበር ደኅንነት ግንዛቤ ማስበጫ ሳምንት ሊከበር ነው

Views: 489

በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አዘጋጅነት የሚካሔደው ሳይበር ደኅንነት ኤጀንሲ ከጥቅምት 24 እስከ 30 እንደሚከበር ታወቀ። ‹‹ትኩረት ለሳይበር ደኅንነት›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ኅብረተሰቡ ስለ ሳይበር ደኅንነት በቂ ሆነ ግንዛቤ እንዲኖረው ይረዳል ተብሎ እንደሚታሰብ ተገልጿል።

በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ግለሰቦች፣ የመንግሰትና የግል ንግድ ተቋማት በሚጠቀሟቸው ማናቸውም ዓይነት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጥቃቶችን እንዴት መከላከልና ተከስተው ሲገኙም በምን መልኩ መመከት እንደሚችሉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች፣ ወርክሾፖች፣ ጥናታዊ ፅሑፎች እና አውደርዕዮች ይካሄዳሉ።

በተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን በተከታታይ የሳይበር ደህንነት ሳምንትን የተመለከቱ ግንዛቤን የሚያሳድጉ የፓናል ውይይቶች፣ማስታወቂያዎች፣ ቃለመጠይቆች፣ ዜናዎች፣ ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፉ ወርክሾፕ፣ የተቋሙን ምርትና አገልግሉት የሚያሳዩ አውደርእይ እና መሰል መልዕክቶች ይስተናገዳሉ፡፡
የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ለተሳታፊዎችና ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንደሚሆኑ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com