ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን በቅናሽ ዋጋ የተጣራ ነዳጅ ማስገባት ልትጀምር ነው

Views: 479

ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን የተጣራ ነዳጅ በቅናሽ ዋጋ ማስገባት ልትጀምር እንደሆነ አስታወቀች። የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ኩዋንግ ቱትላም (ዶ/ር) እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በዋናነት ነዳጅ ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት እንደምታስገባ ገልፀው በቅርቡ ደግሞ ከደቡብ ሱዳን ማስመጣት እንደምትጀምር አስታውቀዋል ሲል ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

ኮዋንግ እንደገለፁት በቅናሽ ዋጋ የሚገባው የነዳጅ ምርት ከቅርበቱ ባሻገርም ኢትዮጵያ በዓመት ለምታስገባው 4 ሚሊዮን ቶን የተጣራ ነዳጅ የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ያሳያል ሲሉ አስታውቀዋል። እንደ ሚንስትር ዲኤታው ገለጻ ፓጋክ እና አዳር የተባሉ ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ማውጫ ስፍራዎች ከኢትዮጵያ ድንበር 200 ኪሎሜትር ብቻ መራቃቸው ተመራጭ እንደሚያደርገውም አስታውቀዋል።

ሚንስትር ዲኤታው አያይዘውም ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል በመላክ ላይ እንደምትገኝ ገልጸው፤ በቅርቡም ከደቡብ ሱዳን በተጨማሪ 400 ሜጋ ዋት ወደ ኬንያ ለመላክ መዘጋጀቷን አስታውቀዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com