10ቱ ብዙ ተጓዦች የጎበኟቸው አገራት

Views: 147

የመንቀሳቀሻ ወይም የትራንስፖርት አገልግሎት በስፋት ከተሰራጨበት ጊዜ ጀምሮ ሰዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ አዳዲስ ነገር የማየት ፍላጎት ተፈጥሮባቸዋል። በዚህም መሠረት ‘በአንድ ድንጋይ ኹለት ወፍ’ እንዲሉ አትርፎ ለመዝናናት ብዙዎች መጎብኘትን ወይም ጉዞ ማድረግን ይመርጣሉ። ለዚህም መዳረሻ ተብለው ወደሚታወቁ ታሪካዊ፣ ለዓይን ማራኪና አስደናቂ ወደ ሆኑ ስፍራዎች ይቀናሉ።

ወርልድ አትላስ የተባለ ድረ ገጽ የዓለም ቱሪዝም ድርጅትን ዘገባ ጠቅሶ፣ በ2018 ፈረንሳይ በዓለማችን ብዙ ጎብኚ ያስተናገደች አገር መሆኗን አስነብቧል። በፈረንሳይ በተለይም ብዙዎቹ የቱሪስት መስህቦች በሚገኙባት ፓሪስ እንደ ኤፍል ታወር ዓይነት እንኳን ደርሰውበት በምስል አይተው የሚያደንቁት ረጅም ማማ ከሌሎች መስህቦች ጋር ተደምሮ ለፈረንሳይ የጎብኚ ቁጥር መጨመር ድርሻውን ተወጥቷል። ፈረንሳይም በቱሪዝም መሪ እንድትሆን አስችሏታል።

በ2018 ስፔን 83 ሚሊዮን ጎብኚዎችን አስተናግዳ በኹለተኛነት ስትገኝ፣ ከጠቅላላ ዓመታዊ ምርት 11 በመቶውን ይኸው ቱሪዝም እንዲይዝላት አድርጋለች። አሜሪካ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ በበኩሏ የቱሪዝም ዘርፍን ገቢ ያስኘኛል ብላ ከቀዳሚ የገቢ ምንጮቿ ተርታ አስቀምጣዋለች።
በ10ቱ ዝርዝር የመጨረሻዋ ኢንግሊዝ ናት። ኢንግሊዝ በቱሪዝም መሠረተ ልማት ቀዳሚ ሊባል የሚችል ሥራ እንዲሁም በታሪክም ጥንታዊ ቅርሶች ያሏት ናት። ይሁንና በ2018 ወደ ኢንግሊዝ ያቀኑት ጎብኚዎች ብዛት 36 ሚሊዮን ብቻ ነው፤ ከቀዳሚቹ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ያነሰ ማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያስ? ኢትዮጵያ በታሪክም፣ በተፈጥሮም፣ በሰው ሠራሽ ቅርስም ከታደሉ ጥቂት የዓለም አገራት ተርታ ብትመደብም፣ በቱሪዝም ዘርፉ በዚህ ደረጃ ጎብኚ ከሚያስተናግዱ አገራት ጋር ስትነጻጸር የቤት ሥራው ምን ያህል እንደሚበዛ መገመት ቀላል ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 48 መስከረም 24 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com