መድን ፈንድ ሰው ገጭተው ባመለጡ አሽከርካሪዎች ምክንያት 9 ሚሊየን ብር ካሳ ከፈለ

Views: 418

የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ባሳለፍነው በጀት ዓመት የተሽከርካሪ አደጋ አድርሰው በተሰወሩ 350 ግለሰቦች ባደረሱት አደጋ ምክንያት 9 ሚሊየን የካሳ ክፍያ መክፈሉን አስታወቀ።

እስከ አሁንም ካሳ የተከፈለባቸው አሽከርካሪች በቁጥጥር ስር አለመዋላቸውን በመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጌታቸው አለማው ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።

በኢትዮጵያ የተሽከርካሪ አደጋ እየጨመረና ከፍተኛ የሆነ የሞትና የንብረት ጉዳት እያስከተለ ይገኛል። የበርካቶችን ህይወት አጥፍቷል፣ አካል አጉድሏል እንዲሁም ንብረት አውድሟል። ለችግሩ እጅግ አሳሳቢነት አንዱ ምክንያትም በአደጋው ተጋላጭ ለሆኑት ግለሰቦች እርዳታ ከመስጠት ወይም እርዳታ እንዲያገኙ እና ህይወታቸው እንዲተርፍ ከማድረግ ይልቅ ጉዳቱን አድርሰው የሚሰወሩ መሆናቸው ነው።

ከመስከረም 1 ጀምሮ ሶስተኛ ወገን የመድህን ሽፋን ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ለማጥናት በሁሉም ክልሎች የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ ይህን ተግባራዊ ያላደረገ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከተገኘ ከ3 እስከ 5 ሺህ የብር ቅጣት እና ለ2 ዓመት እስራት እንዲሁም ደግሞ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ሽፋን እዲኖራቸው ይደረጋል።

ሆኖም 5 መቶ 69 ሺህ 103 ተሽከርካሪዎች 3ኛ ወገን የመድን ሽፋን ያላቸው ሲሆኑ፣ 12 በመቶ የሚሆኑት የመድን ሽፋን የላቸውም ብለዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 48 መስከረም 24 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com