ለ 25 መንደሮች የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ለማቅረብ እና ለመትከል ጨረታ ተዘጋጀ

Views: 103

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለ25 መንደሮች የሚውል አነስተኛ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችን ለማቅረብና ለመትከል ግልፅ ጨረታ ይፋ አድርጓል። ከፀሐይ ኃይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚሆኑት መንደሮች የመጀመሪያዎቹን ሦስት ወራት መጠባበቂያ ጀነሬተር እና ባትሪ እንዲሁም ጥገና አገልግሎቶችንም እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።

ከዓለም ባንክ በተገኘ 375 ሚሊዮን ዶላር ብድር የተጀመረው የገጠር መንደሮችን በኤሌክትሪክ የማዳረስ መርሃ ግብር የተጀመረ ሲሆን የተያዘው መርሃ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በጀት እንደሚያስፈልግ ለማወቅ ተችሏል። ይህም መላውን የኢትዮጵያን አካባቢ በመጭዎቹ አምስት ዓመታት የኤሌክትሪክ ሽፋን ለማዳረስ የተያዘ በጀት ነው።

ጨረታውም እስከ ኅዳር 1 ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ የኢትዮጵያ ኤሌክሪክ ኃይል አስታውቋል

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com