የኢጋድ አባል አገራት የጋራ መግባባት ላይ መድረስ አልቻሉም

Views: 281

የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል አገራት ሐሙስ መስከረም 15/2012 በኡጋንዳ ኢንቴቤ ባደረጉት ውይይት ከግጦሽ መሬት ጋር በተያያዘ በቀጠናው ያሉ አገራት የቁም እንስሳት የመዘዋወር ነፃነትን በተመለከተ የተነሳውን ሃሳብ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ባለመቀበላቸው መግባባት ላይ ሳይደረስ ተለያይተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በኢጋድ በኩል ቀረበው የመግባቢያ ሰነድ የኹለቱን አገራት ጥቅም የማያስጠብቅ እና በርካታ ጥልቅ ውይይት የሚያስፈልገው እንደሆነ በመጥቀስ ከመፈረም ተቆጥበዋል። ስምምነቱን በሚመለከት በጅቡቲ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር አብዱላዚዝ መሐመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ፌደራላዊ መንግስት ስረዓት የምንከተል አገራት በመሆናችን የየክልሎቻችንን ርዕሰ መስተዳደሮች ማነጋገርና ጥልቅ ውይይት ማድረግ ይገባናል ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በኢጋድ አባል አገራት የአርብቶ አደርና የእንስሳት ልማት ዳይሬክተር ሶሎሞን ሙኑዋ ሲገልፁ፤ የመግባቢያ ሰነዱ በ32 አንቀፆች የተጠናቀረ መሆኑን አውስተው በአባል አገራት መካከል ያለውን ነፃ የእነስሳት ዝውውር በማረጋገጥ ያለውን የጋራ ሀብት በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል። አያይዘውም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያም በጉዳዮ ላይ በየግላቸው መክረው እንወስኑ የኹለት ወራት እድሜ እንደተሰጣቸው አስታውቀወዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com