10ቱ ከፍተኛ የካሎሪ መጠን የሚያገኙ ዜጎች ያሉባቸው አገራት

Views: 170

ምንጭ:የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት (UN FAO)

ካሎሪ ለሰው ልጅ ጤና አስፈላጊ ንጥረ ነገር ሲሆን ዋናው በልኩ ማግኘት እንደሆነ ጥናቶች ይናገራሉ። በተለያየ የእድሜ ደረጃ፣ በጾታ፣ በሰውነት ቅርጽ መሰረት እያንዳንዱ ሰው የተለያየ የጉልበት/ኃይል መጠን ይፈልጋል። ካሎሪም ይህን ኃይል የሚሰጠው ንጥረ ነገር ነው።

እንደ ሜዲካል ኒውስ ዘገባ፤ ጉልበት ወይም ኃይል ባለው ነገር ሁሉ ካሎሪ አለ። ለምሳሌ አንድ ኪሎ ግራም ከሰል ውስጥ 7 ሚሊዮን ካሎሪ ይገኛል ይላል። ታድያ ከምግብና ከሰው ልጅ ጋር በተገናኘ በአሜሪካ በተደረገ ጥናት አንድ ወንድ ቢያንስ 2700 ካሎሪ፤ ሴት ደግሞ 2200 ካሎሪ እንደሚያስፈልጋቸውም ዘገባው ያትታል።

ይህም ታድያ በአማካይ እንጂ ለሁሉም በዚህ ልክ ያስፈልጋል ማለት አይደለም። የጤና ሁኔታ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ መጠን፣ ክብደት፣ ቁመት እና የሰውነት ቅርጽ ናቸው መጠኑን የሚወስኑት።

በዚህ መሰረት ታድያ በተለያዩ አገራት ሰዎች የሚያገኙት የካሎሪ መጠን ሲታይ በአንደኝነት ቱርክ ቀጥሎ ደግሞ አሜሪካ ተቀምጠው ይገኛሉ። በእነዚህ አገራት ዜጎች የካሎሪ መጠናቸው ከፍተኛ የሆነና ኃይል የሚሰጡ ንጥረ ነገሮች በብዛት ያሉበትን የተመጣጠነ ምግብ ይመገባሉ ማለት ነው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት 2017 ባወጣው በዚህ የአገራት ዝርዝር ውስጥ ታድያ ከአፍሪካ ግብጽ ብቻዋን ከአስርቱ ዝርዝር ውስጥ ተገኝታለች። በዝርዝሩ ከተካተቱ 24 አገራት መካከል በ21ኛ ደረጃ በ2700 ካሎሪ ናይጄሪያ የተቀመጠች ሲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ አልተካተተችም።

ቅጽ 1 ቁጥር 46 መስከረም 10 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com