10ቱ በዓለማችን ሕዝብ በብዛት የያዙ አገራት

Views: 465

የሰው ልጅ በዝቶ ተባዝቶ ምድርን ሞልቷታል፤ አልፎም ወደ ህዋ መጥቆ ሌላ ለኑሮ ምቹ የሆኑ ስፍራዎችን እየፈለገ ይገኛል። ከዚህ የሕዝብ ብዛትም አገራት የየድርሻቸውን ይወስዳሉ። በ2017 በወጣው መረጃ መሰረት ታድያ አገራት በሕዝብ ብዛት ድርሻቸው ከአንድ እስከ ዐሥር ሲዘረዘሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ቻይና ተቀምጣ ትገኛለች።

በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢኮኖሚው ለውጥ አምጥታ ቁንጮዎቹ ተርታ የተቀመጠችው ቻይና የዓለምን ብዙ ሕዝብ ከመሸከሟ ባለፈ የሕዝቧ ብዛት እሴቷ የሆነላት ይመስላል። “ልጅ ሀብት ነው” የሚለው ብሂል የኢትዮጵያውያዊ ይሁን እንጂ የሕዝብ ብዛት ሀብት የሆናት ቻይና በተግባር ውጤቱ የታየባት ሆናለች።

ይህ ማለት ቻይና ከሕንድ ውጪ ያሉ ሰባት አገራት የያዧቸውን ሕዝቦች በአንድ ጠቅልላ የያዘች አገር ሆና ተመዝግባለች ማለት ነው፤ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017። ከቻይና ቀጥሎ ሕንደ ከፍተኛውን ደረጃ የያዘች ሲሆን ከኹለቱ ቀጥሎ የሚገኙ አገራት ከዓለም ሕዝብ የያዙት ድርሻ በእጅጉ የቀነሰ ሆኖ ይታያል።

በዐሥርቱ ዝርዝር መሠረትም ሜክሲኮና ሩስያ አነስተኛውን የሕዝብ መጠን ይዘዋል። የአፈሪካን ድርሻ ስናይ ናይጄሪያ 2.6 በመቶ የሚሆነውን የዓለምን ሕዝብ የያዘች ሲሆን ኢትዮጵያ በ1.4 በመቶ እንዲሁም ግብጽ በ1.3 በመቶ ድረሻቸውን ከዓለም ሕዝብ ይዘዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 45 መስከረም 3 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com