የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከልክ ያለፈ ሕገ ወጥነትን ለመቆጣጠር እየሰራ ነው

Views: 125

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ከልክ ያለፈ ሕገ ወጥነት ያመጣው ችግር እንደሆነና መንግስት ይህን ተግባር ለመቆጣጠር እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር እንዳወቅ አብጤ እንዳስታወቁት በአገሪቱ ዋነኛ የንግድ ማዕከል አዲስ አበባ መሆኗን ተከትሎ ክፍተኛ የሕገ ወጥ ተግባራት በንግዱ ዘርፍ እየተስተዋሉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። አያይዘውም ከተማ አስተዳደሩ ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ለሕገ ወጥ ተግባራቱ ዋነኛ ተዋናዮች ሕገ ወጥ ደላሎች በመሆናቸው ተዘረጋውን የተራዘመ መረብ በማያዳግም እርምጃ በመበጠስ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እየተሰራ እንደሆነ ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com