ዳሰሳ ዘማለዳ ማክሰኞ ጷግሜ 5/2011

Views: 109

1- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ለ7 መቶ 35 አባላት የማዕረግ እድገት ሰጠ። ከዚህ ውስጥ ዐስሩ ከመስመር መኮኖንንነት ወደ ከፍተኛ መኮንንነት የማዕረግ እድገት ያገኙ ናቸው።በተቋሙ ውስጥ ለ ረጅም ዓመታት ላገለገሉ እንዲሁም አገራቸውን እና ሕዝባቸውን አገልግለው ጡረታ ለወጡ 56 የቀድሞ አባላቶቹም የእውቅና ሰርተፍኬት ሰጥቷል።(ኤዜአ)

……………………………………………..

2-የእብድ ውሻ በሽታ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡በኢትዮጵያ በክረምት ወቅት የእብድ ውሻ በሽታ በስፋት እንደሚከሰት በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ዶ/ር ባዬ አሸናፊ ገልጸዋል።(ኤዜአ)

……………………………………………..

3-የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በአዲሱ ዓመት የግብር አከፋፈል ስርዓቱን ዲጂታል ሊያደርግ እንደሆነ አስታዉቋ። አዲሱ አሰራር የግብር ከፋዩን ጊዜ ከመቆጠብ ባሻገር የመንግስትን ገቢ በማሳደግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል ።ባለስልጣኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 18 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ ከ19 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉንን አስታውቋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………..

4-ኢትዮጵያ የውስጥ ሠላምን አስጠብቆ ለጎረቤት አገራት የሚተርፍ መከላከያ ሠራዊት ገንብታለች ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።የአገር መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ በሀረር ከተማ አዲሱን ዓመት ከተለያየ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር አክብሯል።(አብመድ)

……………………………………………..

5-የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሲሰራቸው የነበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቋል።ኮሚሽኑ በዋናነት ከወሰን አስተዳደር፣ ራስን በራስ ከማስተዳደርና ከማንነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ላይ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የውሳኔ ምክረ ሀሳቦችን ለማቅረብ ታስቦ የተቋቋመ እንደሆነ አስታዉቋል፡፡(አብመድ)

……………………………………………..

6- በጅማ ከተማ ቤተ ክርስትያን ተቃጠለ በሚል በተሰራጨ የሀሰት መረጃ ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር መረጋጋቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በትናንትናው ዕለት በጅማ ከተማ የሚገኘው የማርያም ቤተ ክርስትያን እና መስቀል ተቃጥሏል በሚል የቤተ ክርስትያን ደወል በመደወል እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያዎች እና በስልክ መረጃ በመለዋወጥ ግርግር ተፍጥሮ እንደነበር ተናግረዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………..

7-በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በአሁኑ ወቅት የሰፈነውን አንጻራዊ ሰላም ለማስጠበቅ የሕብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር  ርስቱ ይርዳው ጥሪ አቀረቡ። ወደኋላ የሚጎትቱ በተለይ አንድነታችንን እና አብሮነታችንን የሚሸረሽሩ አስተሳቦችን ለማስወገድ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………..

8  በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግ ማስተካከያ ሳይደረግበት ስራ ላይ እንዳይውል የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል። 65 የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው የጸደቀው ሕግ የመደራጀት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብትን የሚጥስ በመሆኑ በስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com