የነሐሴ ወር የኑሮ ውድነት መጠን የአመቱ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል

Views: 168

የነሐሴ ወር የኑሮ ውድነት መጠን የዓመቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል። የነሐሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 17.9 በመቶ መመዝገቡን ኤጀንሲው ባወጣው ዘገባ አመላክቷል። ካለፈው ወር ጋር ሲመሳከርም የ2 ነጥብ 4 በመቶ ልዩነት አሳይቷል።
የወሩ የምግብ ዋጋ ንረት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከርም በ23 በመቶ ማሻቀቡን ኤጀንሲው ካወጣው መረጃ ላይ ተመልክተናል፡፡

ጤፍ፣ ገብስ፣ ማሽላና በቆሎ በወሩ ያልተቋረጠ የዋጋ ጭማሪ የታየባቸው እህሎች ሆነው ሲመዘገቡ፣ ቀይ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የተደረገባቸው መሆናቸውን ጠቁሟል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦችም የ12 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንደተመዘገበባቸው ኤጀንሲው አውስቷል። በነሐሴ ወር የተመዘገበው የ17.9 በመቶ የዋጋ ግሽበት የአመቱ ከፍተኛ ጭማሪ ነውም ተብሏል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 44 ጳጉሜ 2 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com