10ቱ በአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች

Views: 167

ምንጭ:አይ ኤም ኤፍ (2018 እ.ኤ.አ)

የአፍሪካ ጥቅል አገራዊ ምርት ከባለፈው ዓመት ሉላዊ ጥቅል አገራዊ ምርት ከሆነው 89 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር 4 በመቶ ሲሆን ይህም 2016 (እ.ኤ.አ.) ከነበረው 2.1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። የአሕጉሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ጭማሪ ከሰሀራ በረሃ በታች የሚገኙ አገራት ዕድገት ባስመዘገቡ በሰፊው በመታገዙ ነው። ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጥቅል አገራዊ ምርቱ በ2019 ሦስት ነጥብ አራት በመቶ በ2020 ሦስት ነጥብ ስድስት በመቶ እንደሚያድግ ገምቶ ነበር። ከሰሀራ በረሃ በታች የሚገኙ አገራት ጥቅል አገራዊ ምርት በ2018 ደግሞ 2.371 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል።

የዓለም ባንክ በዓለም የምጣኔ ሀብታዊ ምልከታ በ2019 ከሰሀራ በረሃ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚ በ3.4 በመቶ እንደሚያድግ አመላክቶ ነበር። ሆኖም ግን የአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ማለትም ናይጄሪያ ደቡብ አፍሪካ አንጎላ ከክልሉ አማካኝ ዕድገት በታች ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ከ6 በመቶ በላይ እንደሚያድጉ ይጠበቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 43 ነሐሴ 25 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com