የካፒታል መሣሪያዎችን በኪራይ የሚያቀርብ ድርጅት ወደ ሥራ ገባ

Views: 126

ኢትዮ ሊዝ የተሰኘ ግዙፍ የገንዘብ አቅም የሚጠይቁ ማሽነሪዎችን በራሱ ገንዘብ እየገዛ ለተቋማት በኪራይ ውል የሚያቅረብ በግል ባለሀብቶች የሚመራ ድርጅት ተቋቁሞ ወደ ሥራ ሊገባ ነው። ኤ ኤ ኤፍ ሲ ከተሰኘ የአሜሪካን የገንዘብ ድርጅት በተገኘ 14 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ወደ ሥራ የገባ ሲሆን በአገራችን በዘረፉ የመጀምሪያው መሆኑ ተገልጿል።

ነሐሴ 2/2011 የብሔራዊ ባንክ ገዢውን ይናገር ደሴን (ዶ/ር) እንዲሁም የኢትዮ ሊዝ የቦርድ ሊቀመንበር ግርማ ዋቄን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል።

ድርጅቱ በአገር ውስጥ ለሕክምና፣ ለግብርና፣ ኀይል አቅርቦት እንዲሁም ለግንባታ ዘርፍ የሚውሉ መሣሪያዎችን አስመጥቶ ለተቋማት በረዥም ጊዜ የኪራይ ውል መስጠት ሲሆን ተቋማቱ መሣሪያዎቹን በጊዜ ሒደት የራሳችው የሚደርጉበትን አማራጭ አቅርቧል።

የኢትዮ ሊዝ የቦርድ ሊቀመንበር የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ግርማ ዋቄ ጥራት ያላቸውን የካፒታል ዕቃዎች በስፋት የሚፈለጉበት ሰዓት ላይ መገኘታቸውን ጠቅሰው፤ ዕቃዎችንም ለማስገባት የሚያጋጥመውን የውጭ ምንዛሪ ይቀርፋል ሲሉም አክለዋል። የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ እንደዚህ ዓይነት ተቋማት የውጪ ምንዛሬ ከማምጣትም በላይ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለተቋማት ዕድገት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልጸው ብሔራዊ ባንክ አሠራሩን ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚሠራ ገልጸዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 40 ነሐሴ 4 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com