ኢትዮ አሜሪካን ዶክተርስ ግሩፕ የ4.6 ሚሊየን ብር ሕክምና በነፃ እየሰጠ ነው

Views: 68

ኢትዮ አሚሪካን ዶክተርስ ግሩፕ የተሰኘ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ የሐኪሞች ቡድን የመገጣጠሚያ እና ተያያዥ የጡንቻ ችግሮች ላሉባቸው 23 ታካሚዎች ነፃ የሕክምና ዕርዳታ ከአቤት ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከሐምሌ 30/2011 ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል።

በዶክትር ክብረት ከበደ የሚመራ የሐኪሞች ቡድን ላለፉት ኹለት ሳምንታት ችግሩ ላለባቸው 15 ሕሙማን የቀዶ ጥገና ሕክምናውን የሰጠ ሲሆን ከስፖርታዊ ጉዳቶች ጋር በተገናኘ ሕመም ላለባቸው 8 አትሌቶች ዊሚ ዶጊ ሕክምናውን በማግኘት ላይ ይገኛሉ። ሕክምናው በነፍስ ወከፍ 200 ሺሕ ብር የሚያስወጣ ሲሆን ከሕክምና ቡድኑ ጋር የመጣ አርተሬክስ (arthrex) የተሰኘ የሕክምና መሣሪያዎች አምራች ድርጅት 500 ሺሕ ብር የሚገመት የቀዶ ጥገና የሕክምና መሣሪያ ለአቤት ሆስፒታል በስጦታ አበርክተዋል።

ኢትዮ አሜሪካን ዶክተርስ ግሩፕ በ110 ሚሊዮን ዶላር ዓለቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል በመገንባት ላይ ሲገኝ በቀጣይ የአገር ውስጥ ዶክተሮችን ለማብቃት ተከታታይ ድጋፍ እና ሥልጠና እንደሚሰጠጥ ዶክተር ክብረት ከበደ ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 40 ነሐሴ 4 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com