10ቱ ለኢንቬስትመንት ምቹ የሆኑ የአፍሪካ አገራት

Views: 127

ምንጭ: የግራንድ መርቸንት ባንክ የ2018 አመታዊ ሪፖርት

ግራንድ መርቸንት ባንክ የገንዘብ አስተዳደር፣ የኢንቨስትመንት ባንክ፣ የንግድ ልውውጥ፣ የሀብት አስተዳደር እና የማማከር አግልግሎት የሚሰጥ ባንክ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ላለፉት ሰባት ዓመታት በአፍሪካ የሚገኙ አገራትን የኢንቬስትመንት ምቹነትን በማጥናት ደረጃ እየሰጠ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በ2018 ባወጣው ስምንተኛው ሪፖርቱ በ2019 ለኢንቬስትመንት ምቹ ከሆኑ አገራት መካከል ኢትዮጵያን ከግብጽ፣ ሳውዝ አፍሪካና ሞሮኮ ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

ደረጃውን ለማውጣት በዋናነት የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴንና የምጣኔ ሀብት ከባቢን ከግምት ውስጥ ከትቷል። ሪፖርቱ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን ሲያሰላ የገበያ መጠንና የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነትን ያካተተ ሲሆን የኢኮኖሚ ከባቢ ላይ ደግሞ የዓለም ባንክ ንግድን የማሳለጥ መርሃ ግብር፣ የሔሪቴጅ ፋውንዴሽንን የኢኮኖሚ ነጻነት ዕድገት፣ የወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረምን ሉላዊ ፉክክር ሪፖርትንና የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናልን የሙስና አረዳድ መዘርዝር ውጤቶች ተጠቅሟል።

በዚህ ዓመት የተሠራው ጥናት የአብዛኛው የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ ችግር በሆነው መሰረተ ልማት ላይ ትኩረት ያደረገ በመሆኑ ሪፖርቱ አፍሪካ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ዕቅድ ላላቸው ባለሀብቶች ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል። ዜሮ የሚለው ውጤት ለኢንቬስትመንት ተመራጪ ያልሆኑ፣ ዐሥር ደግሞ በጣም ተመራጭ የሆኑ አገሮች የሚለውን ይወክላል።

ቅጽ 1 ቁጥር 37 ሐምሌ 13 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com