በሽፍቶች በደረሰ ጥቃት በቤኒሻንጉል 57 ሰዎች ተገደሉ

Views: 296

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የታጠቁ ሽፍቶች ባደረሱት ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ 57 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻዲል ሀሰን ለተለያዩ ሚዲያዎች እንደገለጹት፣ ጥቃቱ የደረሰው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ 11 ሰዓት ላይ ሲሆን፣ በጥቃቱ ወደ 17 ሰዎች መቁሰላቸውንና 44 ቤቶች በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በአማራ ክልል የሚኖሩ የጉሙዝ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ያኔም በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።

ጥቃት አድራሾቹ ከአማራ ክልል መምጣታቸውን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በቁጥጥር የዋለ መሣሪያና ሰው ቢኖርም ምን ያህል እንደሆነ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

በስፍራው አሁንም ሥጋት መኖሩን ለቢቢሲ የተናገሩት አሻድሊ ሀሰን ጉዳዩን ለመፍታት ከመከላከያና ከፌደራል የፀጥታ ኀይሎች ጋር እየሠሩ መሆኑን አክለው አስረድተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 34 ሰኔ 22 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com