የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት 165 ሚሊዮን ብር ክብክነት አዳነ

Views: 359

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከኃይል ስርጭት ጋር በተያያዘ በሚያጋጥም የኃይል ብክነት 165 ሚሊዮን 846 ሺሕ ብር ማዳኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። ብክነቱን ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን 123 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ለማዳን ታስቦ የነበረ ቢሆንም 165 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በማዳን የዕቅዱን 134 በመቶ አሳክቷል። ከብክነት የዳነው ገንዘብም ተስተካካይ የኃይል መጠኑ 248 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኪሎ ዋት እንደሆነ ታውቋል።

በስርጭት ረገድም በአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ግንባታና ማሻሻያ ፕሮጀክት 8 ነጥብ 6 በመቶ የተሳካ ሲሆን፤ 17 ነጥብ 8 በመቶ ለማሳካት ታቅዶ እንደነበር እና የዕቅዱንም 48 ነጥብ 1 በመቶ መሳካቱን ሚኒስቴሩ ለሕዝብ እንደራሴዎች ተናግሯል።

ቅጽ 1 ቁጥር 24 ሚያዚያ 12 ቀን 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com